Get Mystery Box with random crypto!

'ጋዜጠኛ ጌትነት አሻግሬ በአማራ ጠሉ ስርዓት የአማራን ህዝብ በደል ማጋለጥና መዘገብ አሳዳጅን የሚ | አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

"ጋዜጠኛ ጌትነት አሻግሬ
በአማራ ጠሉ ስርዓት የአማራን ህዝብ በደል ማጋለጥና መዘገብ አሳዳጅን የሚያበረክት ነገር ነውና ይሄው እጣ ወድቆበት ከሰሞኑ ወደ እስር ተወርውሯል።"

ጋዜጠኛ እና መምህርት መስከረም አበራ

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
መጋቢት 22 ቀን 2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ሸዋ

ጌትነት አሻግሬ ይባላል፣ወንድማችን ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ በመሰረተው "የአማራ ድምፅ" በተሰኘው ሚዲያ ላይ በጋዜጠኝነት ይሰራል።

ጌች በአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ማለቂያ የለሽ የመከራ ዶፍ በየጉራንጉሩ እየገባ የሚዘግብ፣ የአማራ ህዝብ ዘር ተኮር ጥቃት የሚያንገበግበው ድንቅ ጋዜጠኛ ነው!

ጌትነት ወለጋ ተወልዶ ያደገ ኦሮምኛ አቀላጥፎ የሚናገር አማራ ነው።

በመሆኑም የአማራውን ዘር ተኮር ጥቃት በወሬ ሳይሆን በህይወቱ ያየ ልጅ ነው።

የአማራውን መከራ ለማጋለጥ ደከመኝ ሰለቸኝ የማይለውም ለዚሁ ይመስለኛል።

ጌች የአማራ ህዝብን በደል ለማጋለጥ ጋራ ሸንተረር የሚባዝን፣ህይወቱን ለአደጋ አጋልጦ እጅግ አደገኛ ቦታዎች ሳይቀር እየገባ የሚዘግብ፣ትልቅ ተስፋ የሚጣልበት ጋዜጠኛ ነው።

የዚህ ወንድማችን ለወገን እንግልት የመንገብገብ "energy" ምነው ለሁሉም አማራ "Apply to all" ማለት ቢቻል ብዬ ተመኝቼ አቃለሁ። በዚህ ላይ ፀባዩ ድንቅ ነው።

ሰው አክባሪ፣ታዛዥ፣ለጋራ አላማ ለመስራት የሚያስፈልጉ ግላዊ ባህሪያትን የተላበሰ ልጅ ነው።

በአማራ ጠሉ ስርዓት የአማራን ህዝብ በደል ማጋለጥና መዘገብ አሳዳጅን የሚያበረክት ነገር ነውና ጌችም ይሄው እጣ ወድቆበት ከሰሞኑ ወደ እስር ተወርውሯል።

ሆኖም የስራውን ያህል አላወቅነውምና "ይፈታ!" የሚሉ ድምፆች አይሰሙም።

የጌችን ስራዎች ለማየት የሚፈልግ ሁሉ የአማራ ድምፅ ሚዲያን "You Tube" እና ቴሌግራም ገብቶ መጎብኘት ነው።

ልጁ "ይፈታ!" ማለት የሚያንስበት ባለውለታ መሆኑን ወዲያው ይረዳል።