Get Mystery Box with random crypto!

በቤት ውስጥ መወሰድ ያለባቸው የኤሌክትሪክ አደጋ ጥንቃቄዎች:- =============== ፩. የተላ | Amen Electrical Technology Official®

በቤት ውስጥ መወሰድ ያለባቸው የኤሌክትሪክ አደጋ ጥንቃቄዎች:-
===============
፩. የተላጡ ወይም ሊበጠሱ ያሉ ፓወር ኬብሎችን፣ቻርጀሮችን ወ.ዘ.ተ. መቀየር ወይም እንደ አስፈላጊነቱ በ ኢንሱሌተር መሸፈን አስፈላጊ ነው።
፪. ኤሌክትሪካል ሶኬቶችን ወይም ማከፋፈያዎችን ከአቅማቸው በላይ እንዲሰሩ አለማድረግ።
ኤሌክትሪክ ሶኬቶች ሲሰሩ መያዝ የሚችሉት የከረንት መጠን አለ ለምሳሌ ቤት ውስጥ የምንጠቀምባቸው ኖርማል ሶኬቶች መሸከም የሚችሉት እስከ 16 አምፔር ነው።
በተመሳሳይ ሰዓት ብዙ እቃ ብንሰካ እቃዎቹ የሚፈልጉትን የከረንት መጠን ማግኘት አይችሉም በዛ ላይ እሳት ሊፈጥር ይችላል።
፫. በኤሌክትሪክ የሚሰሩ እቃዎችን፣ሶኬቶችን፣ማከፋፈያዎችን፣ ቻርጀሮችን ወ.ዘ.ተ. ከውሃ ማራቅ ምክንያቱም ቆሻሻ ውሃ ኤሌክትሪክ ያስተላልፋል።
ድንገት በውሃ ከረጠቡም ከመጠቀማችን በፊት የምንሰራበትን ቦታም ሆነ እቃዎችን ማድረቅ አለብን።
፬. ህፃናን ከኤሌክትሪክ አደጋ መጠበቅ:-
ህፃናት አጠገባቸው ባገኙት ነገር መጫወት ይወዳሉ። ስለዚህ የኤሌክትሪክ እቃዎችን ከህፃናት ማራቅ ና ክትትል ማድረግ አስፈላጊ ነው።
፭. በተቻለ መጠን ማከፋፈያዎችን አለመጠቀም:-
ማከፋፈያዎች መሸከም የሚችሉት የከረንት መጠን የተለያየ ነው።
በብዛት በቤታችን ውስጥ የሚገኙት ትንሺ ከረንት ለሚፈልጉ ለምሳሌ:- ስልክ ወይም ላፕቶፕ ቻርጅ ለማድረግ በቂ ሲሆኑ ለሌሎች ማሽኖች እንደ ልብስ ማጠቢያ፣ስቶቭ ለመሳሰሉ ከፍተኛ ከረንት ለሚፈልጉ እንጠቀማቸዋለን። በዚህ ጊዜ ከፍተኛ ሙቀት ይፈጥሩና ይቃጠላሉ። እሳት እስከመፍጠርም ይደርሳሉ።
በተቻለ መጠን ማከፋፈያ ከምንጠቀም ሶኬት አሰርቶ መጠቀም አስፈላጊ ነው።
፮. በእርጥብ እጅ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ እቃዎችን አለመንካት:-
ከዚህ በፊት እንዳየነው የሰውነት ደረቅ ቆዳ (dry skine)የኤሌክትሪክ ፍሰት የመቃወም አቅሙ/ሪዚስታንስ 100,000 ኦም ሲሆን እርጥብ ቆዳ ወይም በውሃ የረጠበ ቆዳ ደግሞ ኤሌክትሪክ ፍሰት የመቃወም አቅሙ ወደ 1000 ኦም ይቀንሳል።
ኤሌክትሪክ ደግሞ ቆዳችን አልፎ መግባት ከቻለ ዉስጠኛው የሰውነት ክፍላችን የኤሌክትሪክ ፍሰት የመቃወም አቅሙ(300ኦም) ደካማ ነው።
ስለዚህ እጃችን ሳናደርቅ ማንኛውንም በኤሌክትሪክ የሚሰራ እቃን ከመንካት መቆጠብ አለብን።
፯. አፖል ስንቀይር ጥንቃቄ ማድረግ:-
አብዛኞቻችን የመብራት አፖል ሲቃጠልብን እጃችን ላይ ያለዉን ወይም ለመግዛት ሂደን የሰጡንን ገዝተን እንቀይራለን። ይሄ አግባብ አይደለም ከኤሌክትሪክ ፌክስቸሩ ዋት በላይ የሆነ አፖል ከቀየርን ፌክስቸሩ ላይ ከፍተኛ ሙቀት ይፈጥራል ከፍ ሲልም አምፖሉም ሆነ ፌክስቸሩ ይቃጠላል። ባጭሩ አምፖል ስንቀይር የአፖሉ ዋት ከፌክስቸሩ ዋት እኩል መሆን ወይም ማነስ ይኖርበታል። ፌክስቸሩ ከአንድ በላይ አምፖል የሚዎስድ ከሆነ የአፖሎች ዋት ድምር ከፌክስቸሩ ዋት መብለጥ የለበትም። ነገር ግንየዋቱ መጠን ቴክስቸሩ ላይ ካልተጠቀሰ የአፖሉ ዋት ለኢንካድሰንት ላምፕ ከ 60 ዋት፣ለCFL-ኮምፓክት ፍሎረሰንት ላምፕ ከ 12 ዋት እና ለLED-ላይት ኢሚቲንግ ዳይወድ ከ 10 ዋት መብለጥ የለበትም።
አምፖል ስንቀይር በሚገባ መታሰር አለበት ይህ ካልሆነ ግን ፍንዳታና እሳት ሊፈጥር ይችላል።
ሌላው ደግሞ ስለ አምፖሎች ለምን ቶሎ ቶሎ ይቃጠላሉ? ምን አይነት አምፖል ይሻላል? የሚሉ ጥያቄዎች ይነሳሉ። ሌላ ሰፊ ፕሮግራም ይኖረናል ለጊዜው ግን ስለተለያዩ የአምፖል አይነቶች፣የሚጠቀሙት የሀይል መጠንናየሚሰጡት የብርሃን መጠን ቆጥሎ ያለው ፎቶ ላይ ይመልከቱ።
፰. ለሁሉም የቤተሰብ አባላት ግንዛቤ መፍጠር:-
ዋናው ብሬከር ወይም ቆጣሪ የት ጋ እንዳለ እና እንዴት ማብራትና ማጥፋት እንዳለባቸው ሁሉም የቤተሰቡ አባል ማወቅ አለባቸው። ድንገት አደጋ ቢፈጠር ቤት ዉስጥ ያለ ሰው ማንንም ሳይጠይቅ ማጥፋት ይኖርበታል።
አፖል ስንቀይርም ሆነ ሌሎች የኤሌክትሪክ ስራዎችን ስንሰራ መብራቱን ማጥፈትና ኤሌክትሪክ መከላከያ እንደ ጓንት፣ሴፍቲ ጫማና ሌሎችን መጠቅም። መብራት እንዳይለቁብን እየሰራን መሆኑን ለሁሉም የቤተሰብ አባል ማሳወቅ ተገቢ ነው።
ብረት ነክ መሰላል የምንጠቀም ከሆነ መሰላሉን ስናንቀሳቅስ ከኤሌክትሪክ መስመር ጋ እንዳይገናኝ ጥንቃቄ ማድረግ።
፱. በሙያው በሰለጠኑ ሰወች ማሰራትና የባለሙያውን ትክክለኛነት ማረጋገጥ:-
ህይወታችን ከኤሌክትሪክ ጋ የተቆራኘ ነው። ስለዚህ ሁሉም ሰው ስለኤሌክትሪክ መሰረታዊ እውቀት ሊኖረው ይገባል። ቀላልና ራሳችን ልንሰራቸው የሚገቡ ነገሮችን መለየትና መስራት አለብን ነገር ግን እራሳችን ለአደጋ የሚያጋልጡ ነገሮችን በሙያው በሰለጠኑ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ማሰራቱ ተገቢ ነው።
የምናሰራቸውን ሰወች የሙያ ሁኒታ፣ ፈቃድ፣ፈቃዱን የሰጠውን አካል ማወቅ ይኖርብናል። ምክንያቱም :-
አደጋ ቢፈጠር ስራውን የሰራውም ያሰራዉም ሁለቱም ወንጀለኞች ናቸው።
ኤሌክትሪክ ምንም ቢደረግ ሉፕ እስከሰራ ድረስ ለጊዜው ኤሌክትሪክ ያስተላልፋል። ነገር ግን ብዙ ታሳቢ መደረግ ያለባቸው ህጎች፣መመሪያዎችና ስታንዳርዶች አሉ። እነዚህን ካላሟላ ወይም ካልጠበቀ ወዲያዉኑ ይበላሻል አደጋም ሊፈጥር ይችላል። እቃወቻችንም ሊይቃጠሉብን ይችላሉ። ስለዚህ የሚሰሩልን ሰወች የሙያ ሁኔታ ማወቅ ይኖርብናል።   
ሌላው ዋናውና በሀገራችን ያልተለመደው ቅድመ/መከላከል ጥገና/prevantive maintenance የምንለው ነው። ይህ አሁን ላይ አንዳንድ ቤቶች (ሆቴሎች፣ድርጅቶች፣አንዳንድ መኖሪያ ቤቶች ወዘተ) ላይ  እየተሰራ ሲሆን በጣም ጠቃሚና ብዙ እቃወችን ከብልሽት የሚታደግ ነው። ብልሽት ከማስተናገዱ በፊት መጠገን ያለብት እንዲጠገንና መቀየር ያለበት እንዲቀየር ያስችላል። የንብረትም ሆነ የህይዎት አደጋ ሳያስከትል ቀድሞ ምላሽ ለመስጠት ዋነኛ መፍትሄ ነው። ስለዚህ ቋሚ ሙያተኛ ይዞ በሆነ የጊዜ ልዩነት ቸክ አፕ እንዲያርግልን ማድረግ አዋጭ ነው።
ሌላው ከጅምሩ የሚያምር ህንፃ ልሰራ አስበን ኤሌክትሪኩንና የሳኒታሪ/ቧንቧ ስራዉ ላይ ግድ የለሾች ነን። በዚህም የተነሳ ስንት ነገር ወጪ አርገን የሰራነው ቤት አንድ አመት እንኳን ሳይሞላው ኤሌክትሪክ ገመድ በዉጭ በኩል ተሰርቶና ተልጣጥፎ እናያልን። ስለዚህ ከጅምሩ ትኩረት ሊሰትምጠው ይገባል።
የመጨረሻው ደግሞ ወጪ ላለማውጣት ሲባል ስታንዳርዱን ሳይጠብቅ ቤታችን ዉስጥ ባለው ነገር እንዲሰራ የሚያስገድዱ ግለሰቦች አሉ። ይሄ አግባብ አይደለም ሙያው በሚፈቅደው መልኩ መሰራት አለበት ይህ ካልሆነ የከፋ አደጋ ያስከትላል።
ሌሎችም አሉ ለጊዜው ግን እነዚህ በቂ ናቸው ።

#አዲሱን_የYouTube_Channel ሊንኩን በመጫን #Subscribe እያደረጉ የበለጠ እንድንሰራ ያበርቱን

https://www.youtube.com/channel/UCAdqgLHZGPPay3oBXmfC6Vw
#ማንኛውንም_የኤሌክትሪክ_ስራ_ማሰራትና_መሰልጠን_የምትፈልጉ_ድርጅቶችና_ግለሰቦች_በነዚህ_ስልክ_ቁጥሮች_ያገኙናል
    
  0911585854
  0991156969
         
"ለሌሎች ለውጥ ምክንያት እንሁን "
#ለወዳጅዎም_ያጋሩ
#እናመሰግናለን