Get Mystery Box with random crypto!

የዮቶር ልጅ - አምባዬ ጌታነህ

የቴሌግራም ቻናል አርማ amba_ethiopia — የዮቶር ልጅ - አምባዬ ጌታነህ
የቴሌግራም ቻናል አርማ amba_ethiopia — የዮቶር ልጅ - አምባዬ ጌታነህ
የሰርጥ አድራሻ: @amba_ethiopia
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.22K
የሰርጥ መግለጫ

እኛ ከዮቶር፦
☞ የጥበብ ምሳሌን
☞ የአስተሳሰብ ውጤትን
☞ የፍልስፍና ዳራን
☞የአመራር ብቃትን
☞የአኗኗር ዘይቤን
ተምረናል!!!
ስለዚህ ሁላችንም የዮቶር ልጆች ነን ማለት ነው።
ለአስተያየት ና ሀሳብ via creater
@Adwa1888 [አምባዬ ጌታነህ]
YouTube
https://youtube.com/channel/UCTQKMrpvRybbd9C552bMVQQ

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-13 06:07:43
3.2K viewsአምባዬ ጌታነህ❶ , 03:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 06:56:17
3.3K viewsአምባዬ ጌታነህ❶ , 03:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 08:12:56 ስታወራኝ እነዛ ሁለት ንቦች በጭንቅላቷ ይዟዟራሉ። አንዳቸው አንዳቸውን ያሳድዱና። ትከሻዋ ላይ ይቀመጣሉ። ሁሌም በዙሪያዋ። የትም ብትሄድ በግራና በቀኝ አይለዩዋትም። አተኩሬ ሳያቸው ሰይፍ ይዘው የሚገለባበጡ፤ ባለስድስት ክንፍ ጠባቂ መላዕክቷ ይመስሉኛል።መቼም ንቦች በሚቀሰሙ ድንቅ አበቦች መሀል አይጠፉም። ናዲያ የመስከረሙን መጥባት ተከትላ የፈካች ደይ መስላለች። “እሽሽ” የማትላቸው ለምንድን ነው?"ስል ራሴን ጠየኩ። "ሰው እንደእኔ ካልሆነ በቀር ለምን የሚወደውን ያባርራል ?" አልኩ ከእንደገና ለራሴ። ቡና ቀዳችልኝ። የምትቀዳልኝ ቡና እንደ ፏፏቴ ቀስ ብሎ ሲወርድ የቡናው እንፋሎት ደግሞ በጭስ መልክ ወደ እኔ ይግተለተላል።ቡናው መሃል አረፋ የሰሩትን ክብባቶች እያመለከተችኝ “ይህ የመጪው ጊዜ ሲሳይህ ነው። ጥሩ ተስፋ አለው ጠጣ"አለችኝ ። ናዲያ እንዲህ አይነት አጉል አባባል አላምንም ተይኝ ብላትም “አልሰማ” ብላኛለች። ነገሮችን ሁሉ የምትጠልፍበት ትርጉም አታጣም። ቡናዋን ከማፍላት፤ ውጭ ሀሳብ ያለባት አትመስልም። ናዲያ የቀናት ሸክሜን የምትቀበለኝ ማረፊያዬ መተንፈሻዬ ግራር ናት። እሷ ጋር ስቀመጥ የሆንኩትን ና ያደረጉኝን ሁሉ እረሳዋለሁ። ጨዋታዋ አይጠገብም።የአስር ብር ቡናዬን ሶስት ጊዜ ልፌ ስነሳ" አራተኛውን ሳትጠጣ?" ትለኛለች። አራተኛው ደግሞ ምንድነው ስላት ናዲያ ቡና ትለኝና ትፍለቀለቃለች።ሳቋ ፍፁም የእውነት ነው ጥርሶቿ ችምችም ብለው ሲገለጡ የሕይወትን ጥዑምና አስደሳችነት የሚያውጁ መለከቶች ይመስላሉ። በለሆሳስ ፈገግ ብዬ " ናዲ አንቺም በስማቸው የሆነ ነገር እንደሚሰይሙትና እንደሚያሰይሙት ሆንሽ ማለት ነው?"አልኳት እየሳኩኝ " ኧረ ባክህ ምን ያንሰኛል ናዲያ እኮ ነኝ!! ሙያዬ ደግሞ ማንም ያወቀው ነው! ራሴን ካላንቆለጳጰስኩ ማን ያንቆለጳጵስልኛል!" አለች በፈገግታዋ በድጋሚ እየገረበችኝ። ሁሌም ስመለከታት ትገርመኛለች ራሷን በቆንጆ ተግባሮች ውስጥ ከቆንጆ አገላለፅ ጋር ታስቀምጣለች" ይሄው አቦል፣ቶና፣በረካንና አራተኛውን ናዲያ ቡናን ሳልጠጣ አትለቀኝም። ፍልቅልቅ ነች። ሳቋ በሀጥያት ብዛት የተዘጉ የገነት በሮችን ያስከፍታል። የቡና አፈላል ሳይንስን ከባህላዊ እስከዘመናዊው ድረስ ጥንቅቅ አድርጋ ታውቀዋለች። ለቡና የሚያስፈልጉትን ግብአት በሙሉ ካላሟላች ስራ አትጀምርም።የስራ ስነስርአቷ ያስደንቀኛል በአይነቱ የተለያዩ ጭሶች አሏት። "አንቺ ልጅ ግን ይሄን ከወሎ ጭስ ለማምጣት በሚል ሰበብ ወሎን በኢኮኖሚ የምትደጉሚውን ነገር አቁሚ! አሁን እውነት ጭስ ከወሎ ብቻ ነው የሚመጣው?" አልኩ ለመፍገግ የሚታገሉኝ ጥርሶቼን በከንፈሬ እየከደንኩ " ኧረ ተው አንተ ልጅ ባክህ" አለች ሌሎች ደንበኞቿን በአይነ ቁራኛ እየተመለከተች። "አሁን ካልታጣ ጭስ ምን የሚሉት ነው ሁሌ የወሎን ጭስና የአበጋርን እጣን ቡልቅልቅ የምታደርጊው?" አልኳት በድጋሚ ሳቀችና "ሞዛዛ ነህ እሺ! አሁን እኔን ለመናገር ፈልገህ ነው እንጅ ሀገራችን ውስጥ እንደ ወሎ ጭስ የሚሆን ጭስ የት ይገኝና ነው እንዲህ የምትለኝ! ደግሞስ ሁሉም ሰው የወሎን ጭስ በእግር በፈረስ ብሎ አይደል የሚፈልገው። እኔ ራሱ ወደ መርሳ ስሄድ ስንት ሰው ነው የወሎ ጭስ አምጭልኝ የሚለኝ"አለች "በቃ እሺ የሆነው ሆኗል ለሚቀጥለው ግን ከደቡቡም ከአፋሩም ከሱማሌውም ጭስ አምጥተሽ አጭሽልን"አልኳትና ስቄ ዝም ብዬ የያዝኳትን መፅሐፍ ገለጥ አደረኩ። " እኔን ሆን ብለህ ለማበሳጨት ነዋ እንዲህ የምትለው ሞዛዛ ነህ እሺ!" አለችና በአይኖቿ የፍቅር አስተያየት መግባኝ ስታልፍ "አቦ የዚችን ልጅ ግን ቡናዋን ነው ዓይኗን የምወድላት?"ብዬ ራሴን እየጠየኩ አራተኛ ቡናዬን ልፌ ሂሳብ ልከፍል ስል "እመ አምላክን እምቢ እንዳትለኝ ዛሬ እኔ ነኝ የምጋብዝህ"ብላ እጄን ያዘችው። አልተቃወምኳትም። አመስግኜ መንገዴን ስጀምር "መባዬ"ብላ ጠራቺኝ። ስሜን ሁሌ እንዲህ ነው የምትጠራው "ዬ" ን ካልጨመረች አቤት ብዬ የምዞርላት አይመስላትም።"ወይዬ"አልኋት ከስራ ስትወጣ የምነግርህ ነገር አለኝ እሺ እንዳትቀር" ብላኝ ወደ ስራዋ ተመለሰች። "ምን ይሻላታል ይቺ ነፃ የሆነች ልጅ ደግሞ ምን ልትለኝ ነው?"እያልኩ መንገዴን ጀመርሁ!!


"ናዲያ" ነሐሴ"፩" "በየዮቶር ልጅ-አምባዬ ጌታነህ" @Amba_Ethiopia ቻናል ላይ ትወለዳለች። ናዲያ ከወትሮዎቹ እህቶቿ "መቅደላዊት፣ኤሴቅ፣ናፊባ በባህሪም በጠባይም በልምድም የተለዬች ድርሰት ስለመሆኗ ፈጣሪዋ መመስከር ይችላል!!!!
ታዲያ ይችን እጅግ ውብ የሆነች ድርሰት ለብቻ ማንበብ ስስትነት ነውና ለወዳጅ ጓደኞቻችሁ ሼር በማድረግ አብራችሁ ትበሉ ዘንድ አሳስባለሁ!!

የወደዱትን የማጋራት ተፈጥሯዊ መንገድንም ወደ ንባብ መቀየር ያስፈልጋልና እነሆ መስፈንጠሪያ ሊንኳ
@Amba_Ethiopia
@Amba_Ethiopia
@Amba_Ethiopia

"ማስታዎሻ"
ከላይ በወጉ ላይ የተጠቀሰችው ናዲያ ከድርሰቱ ጋር ምንም አይነት ቁርኝት እንደሌላት ለማሳሰብ እወዳለሁና አንባቢ ሆይ ይቺኛዋ ናዲያ ሌላ እንደሆነች እንዲያውቅልኝ እሻለሁ!!

መልካም ቀን!

አምባዬ ጌታነህ ለአስተያዬት @Adwa1888
2.8K viewsአምባዬ ጌታነህ❶ , 05:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-26 05:10:18
3.6K viewsአምባዬ ጌታነህ❶ , 02:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 22:34:21 "ናፊባ"
ክፍል ~ ዘጠና ሥምንት~
በአምባዬ ጌታነህ @Adwa_1888
"ሰላም የሀገራችን ህዝቦች አሁን ላይ እየተፈጠረ ያለው ነገር ፍፁም ውሸትና የመንግስትን መዋቅር የሚንድ ሲሆን እነዚህን ሰዎች ደግሞ በቅርቡ ለህግ በማቅረብ የህግ የበላይነትን የምናስከብር ይሆናል። ስለዚህ ሰላም ወዳዱ ህዝባችን በማንም ስርአት አልበኛ ተግባር በመደናገጥ የእለት ተእለት ኑሯችሁን እንድትቀጥሉ እናሳስባለን" በመሆኑም የመንግስት ኮሚኒኬሽኑ መግለጫ አውጥቷል።የመንግስትን መግለጫ የተመለከቱ በርካታ ሰዎች በመንግስት ማላገጫ በበዛበት መግለጫ ተቆጥተዋል። አንዳንድ ጊዜ በመሪዎችና በህዝብ መሀል የሀሳብ ልህቀትና ከፍታ ሲገኝ ሁለቱም ይቃረናሉ። አንዳንድ ህዝብ መሪውን ትቶ ያልፋል።መሪ ሲያዘግም ህዝብ ሲፈጥን ትልቅ ችግር ይሆናል በመካከላቸው ጥልቅ ግድግዳ ይቆምና አሳር ይሆናል።
"ምን አይነት አይን አውጣነት ነው? እንደው ግን ህዝቡ የማይገባው ነው የሚመስላቸው? ከቶ ምን ያህል ሞኞች ቢሆኑ ነው?"አለ ኢንስፔክተር ሸዋንግዛው ቀጥታ መግለጫውን እየተመለከተ "ተዋቸው ሀጥያታቸው ሲበዛ ይሄው በመጨረሻ የሚያደርጉትን አሳጧቸው"አለ ፕሮፌሰር የሸበቱ ፂሞቹን በቀኝ እጁ እየነካካ " ፕሮፌሰር አለ አንድ ልጅ በፍጥነት ወደ ውስጥ እየገባ ከመፍጠኑ የተነሳ የሁለታቸውንም ንግግር ከቁብ ሳይቆጥር በንግግራቸው መሀል እየገባ "ምን ሆነህ ነው አርኪመደስ እስኪ መጀመሪያ ተረጋጋና ንገረን"አለ እንዲቀመጥ እየጋበዘው " አይደለም ፕሮፌሰር መቀመጥ "አሁን ትልቅ ችግር ተፈጥሯል " እስኪ አንተ ልጅ ካለወትሮህ ምንድን ነው እንደዚህ የሚያሸብርህ የተፈጠረውን ነገር እስኪ ንገረን "ፕሮፌሰር ግራ ተጋብተው በድጋሚ አረጋጉት "ፕሮፌሸር "ትንፋሹ ቁርጥ ቁርጥ እያለ "መስፍንና ሒዎት አስር ቤት ተገድለው ተገኙ"ብሎ ለመናገር ሲዳዳው የቆየውን ነገር በአንድ ጊዜ ዝርግፍ አደረገው። ኢንስፔክተር ሸዋንግዛው ከተቀመጠበት ተነሳና "ማለት" "እንግዲህ ሞተው ነው የተገኙት እንደ እኛ ጥርጣሬ የመሐረቤ ቅጥረኞች ይሆናሉ ብለን ነው ያሰብነው" አለ በርግጥ ቢሞቱም ባይሞቱም ህገወጦች ነበሩ። እንግዲህ ከእነሱ ጋር ባለመስማማታቸው ይሆናል!" አለ ፕሮፌሰር "የተለዬ የሚያውቁት ነገር ነበር እሱን ተናግረዋል ወይም ወይም ተናግረዋል ብለው ስለጠረጠሩ ብቻ እርምጃ ወስደውባቸዋል ማለት ነው። ይህ ደግሞ በእርግጠኝነት የነ መኃረቤ ስራ ነው የሚሆነው!አለ አርኪመደስ " "ቆይ ከእኛ ውጪ ይሄን ነገር ለማወቅ ማን እነመስፍን ጋር ሊሄድ ይችላል?" አለ ኢንስፔክተር ሸዋንግዛው ለብዙ ደቂቃ ከራሱ ጋር እየተነጋገረ ከቆዬ በኋላ "ፕሮፌሰሩና አርኪመደስ ተያዩ።
****
መስቀል ፍላወር ከወትሮው የሰዎች ግርግርታው ጨምሯል። መኩኖች በየረድፍ ተደርድረው ዙሪያ ገባውን ያሉት ፓርኪንግ የመኪና ማቆሚያዎቹ ተጨናንቀዋል። የአባቢው ሰዎች ይህን ያህል መኪና መብዛቱ ግራ እስኪያጋባባቸው ድረስ መኪኖቹ ላይ የስአት መቆጣጠርያ በማስቀመጥ ተጠምደዋል። በጣም ከመብዛታቸው የተነሳ ቲኬት ሳይደረግባቸው የቀሩ ሁሉ አሉ።እናም እንዲህ መሆኑ የአካባቢውን ሰዎች ራሱ የመንግስተሰ ባለስልጣናት በአካባቢው ያሉ እስኪመስል ድረስ የትራፊክ መጨናነቅ ተከስቷል። "እርምጃ ውሰዱ ስል ብቻ ትወስዳላችሁ ከዛ ውጪ በምንም አይነት መንገድ የፈለገ ነገር ቢኖር እንዳትጀምሩ።" በማለት አስጠንቅቋቸው ንግግሩን ሲጨርስ "ፊትለፊቱ ያለው ዓደይ ሞል ላይ በርካታ ሲቪል ሰዎች እንደ ጉንዳን ይርመሰመሳሉ። እናም በዚህ መሀል መረጃ ከተለዋወጡ በኋላ አካባቢው ላይ በርካታ የፌደራል ልዩ ሀይል ፖሊሶች ፈሰው ፍተሻ ማድረግ ጀመሩ። "በሉ አሁኑኑ ከአካባቢው መሠወር አለባችሁ"አለና ሁነቱን ከእርቀት ይመለከት ስለነበር አቅጣጫ በመስጠት ጠቆማቸው።
"ጥሩ ነገር ነው ያደረጋችሁት። ድራማው በትክክል ሰርቷል። ጥሩ ተዋንያን ነበራችሁ!"አለች መኃረቤ በስልክ ስክሪኗን ፊት ለፊት እየተመለከተች። "አዎ በሚገባ በመጀመሪያ ስንገባ ተጠራጥረን ነበር። ነገር ግን በዛም ስለምንል ምንም አልመሰለኝም ወደ ድርጊት ስንገባ ምንም አልመሰለኝም ነበር።ከዛ ግን ነገሮች እንደዛ ቀላል ሲሆኑ እፎይታ ተሰማኝ"አለ "አምበሶች አሁን በጣም ነው ያኮራችሁኝ። ዛሬ በጣም ትልቅ ረፍት ነው የሰጣችሁኝ"በማለት ላደረጉት ነገር እውቅና በመስጠት ነገሩን ቋጭታ በደስታ ፈገግ አለችና "ድራማዬን ላትችለው ዝም ብለህ ትነካካኛለህ"አለችና በድል አድራጊነት ፈገግ አለች።

@amba88
4.5K viewsአምባዬ ጌታነህ❶ , 19:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 05:12:17
3.4K viewsአምባዬ ጌታነህ❶ , 02:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 21:59:29 "ናፊባ"
ክፍል ~ ዘጠና ሠባት~
በአምባዬ ጌታነህ @Adwa_1888
"ቆይ ወዴት ነው የምትሄደው?" አለ መስፍን " እና እናንተ ጋር ማን ይታገላል። ራሳችሁን ነፃ ማድረግ ስትችሉ ምን እንደዚህ ያደርጋችኋል? አንዳንድ ጊዜ ሰዎች አንድ ነገር ለራሳቸው ጉዳይ ተብሎ እንደሚነገራቸው ማወቅ ይሳናቸዋል"አለ ኮስተር ብሎ "እሺ አሁይ ምን እናድርግ ሁሉንም የምናውቀውን ብንናገር ነፃ እንወጣለን?" "በደንብ ከደሙ ንፁህ ትሆናላችሁ። ምክንያቱም የዚህ ሴራ ዋና አክተር እናንተ እንዳልሆናችሁ እና ትዕዛዝ ፈፃሚዎች እንደሆናችሁ ካረጋገጠ ፍርድ ቤቱ ብዙ ማቅለያዎችን ያደርግላችኋል።ሌሎች ሌሎችም ነገሮችን ታገኛላችሁ ስለዚህ እናንተ ወስናችሁ የሚደረግላችሁን ነገር በማመን እንዲሁም የአቃቤ ህጉን ስራም በማቅለል ተጨማሪ ማቅለያዎችን ታገኛለህ ስለዚህ አሁን ብስለት የተሞላበት ውሳኔ እንድትወስኑ እፈልጋለሁ። አሁን ብዙም ጊዜ ስለሌለኝ የምታውቁትን ሁሉ ንገሩኝ!!" አለና ተቀመጠ። መስፍንና ሒዎት እርስ በእርስ እየተያዩ ከተቀመጡ በኋላ በድጋሚ አንቺ ጀምሪ አንተ ጀምር በሚል አስተያየት ይተያዩ ጀመር። ከተወሰኑ ደቂቃዎች መተያየት በኋላ መስፍን ማውራት ጀመረ። "በርግጥ እኛ ሁሉንም ነገር እናውቃለን።ነገር ግን አሁንም ቢሆን ምንም አይነት ማረጋገጫ የለንም።አንተስ እሷ እንደተወችን የምትፈልገውን ካገኘህ በኋላ ላለመተውህ ምን ማረጋገጫ ይኖረናል"አለ መስፍን መኃረቤ ያደረገችውን ላለመደገሙ ማስተማመኝ እንዲሰጠው በመሻት። "ልክ ነህ መተማመኛ የለህም። ነገር ግን አንድ እውነት ልንገርህ አንተ እውነቱን ተናገርክም አልተናገርክም መኃረቤ እያለቀላት ነው። አሁን ላይ መቼም ውጭ ላይ እየተካሄደ ስላለው ነገር እያወቃችሁ ያላችሁት ነገር የለም። እኔ እናንተን እያወራኋችሁ ባለሁበት ስአት ኢንስፔክተር ሸዋንግዛው በአሁኑ ስአት ከሙሉ ቤተሰቡ ጋር ተሰውሯል። ራሱ ይሰወር ሰዎች ይሰውሩት ምንም የሚታወቅ ነገር የለም። ነገር ግን በእርግጠኝነት ራሱ ነው የተሰወረው። ምክንያቱም አጋቾች ቢሆኑ ቢያንስ የወንድሙን ልጅ ይተዋት ነበር።ስለዚህ ተሕሚድም ሲሐምም ሁላቸውም አንድ ላይ መሰወራቸው ምን ያህል ኢንስፔክተር ሸዋንግዛው አስቦበት እያደረገ ያለ ነገር እንደሆነ ነው የሚታወቀው።ይህ ደግሞ የሚያሳየው የሆነ የማይታወቅ ምስጢራዊ ነገር እየተካሄደ እንደሆነ ነው። ስለዚህ አሁን እናንተ የምትሳሱትን ምስጢር እሱ ጎልጉሎ ያወጣዋል ነገር ግን እናንተ ብትተባበሩ ያው ጥቅሙ ለእናንተ ነው"በማለት በለሆሳስና ፈገግታ በተሞላበት አነጋገር አስገነዘባቸው። መስፍን ሆዱ ከወትሮው በተለዬ በፍርሀት ሲርድ ይሰማዋል። በመጨረሻም በመወሰን የሚያውቀውን ለመናገር ጉሮሮውን ጠራርጎ ንግግር ጀመረ። በፍርሃት ቃላቶቹን እያቆራረጠ አንድ በአንድ ይናገር ጀመር።
******
"ጥሩ ዜና ይዤልሻለሁ ወይዘሮዋ አሁን እንደሚመስለኝ የማትፈናፈኝበት ጊዜ ላይ ደርሰሻል። መቼም ስለወዳጅሽ የሰማሽ ይመስለኛል። ቀናቶች አልፈዋል። ይሄኔ አንድ ዋሻ ውስጥ ተደብቆ የመሞቻሽን ቀን እየቆጠረልሽ ነው። አሁን የምትተማመኝበት የስለላ ተቋም እስኪ ምን እንደሚያደርግልሽ እናያለን"ብሎ በረጅሙ ሳቀ። "እኔ አንድ ነገር ከመሆኔ በፊት ቃል የምገባልህ ነገር ቢኖር አንተን ገድዬህ እንደምሞት ነው።!" በረጅሙ ሳቅ ከሳቀ በኋላ "የት አግኝተሽኝ ነው? ይሄን ሁሉ ህልም የምታልሚው?" በዚህ ጨዋታ ላይ ተሸናፊዋ አንቺ ነሽ ብዬሽ ነበር ነገር ግን አንቺ ከቁብም አልቆጠርሺኝ። ግን ይሄው እውነታው ምን ያህል እንደሆነ እንደው አለቆችሽን ከማምለክ ቢቀርብሽ እና ትንሽም ቢሆን እውነቱን ሊሆን ይችላል ብለሽ ብትጠረጥሪ አሪፍ ነበር። ግን የማታ የማታ ይሄው የሰፈርሺው ቁና ተሰፈረልሽ። ሰው የዘራውን አይደል የሚያጭደው በአጉል እብሪትና ማን አለብኝነት የብዙዎችን የንፁሀንን ህይወት ቀጠፍሽ በመጠረሻም ይሄው" ብሎ ንግግሩን ጨርሶ ሊዘጋ ሲል "አይዞህ ጆሮ ጠቢዎችህን አሰወግጃቸዋለሁ አታስብ" አለች። " ማለት አንቺ አውሬ እነመስፍንን ምን አደረግሻቸው?" አለ። "ምን እንዳደረኳቸው ገሀነም ሄደህ ብትጠይቃቸው አይሻልም? "አለችውና የመልስ ምት የሆነውን ሳቋን ለቀቀችው። በንዴት አጠገቡ ያለውን ወንበር እያጋጨ "ግን ምን አይነት ፍጡር ብትሆኝ ነው በንፁሀን ደም እንዲህ የምትስቂው? ግን አንቺ የምር እህቴ ነሽ?" "አይ አይደለሁም በጭራሽ እኔና አንተ የአንዶ እናትና አባት ልጆች አይደለንሞ አንተ ወድቀህ ነው የተገኘኸው!" አለችና አሁንም በረጅም ሳቅ ጆሮው ላይ አቃጨለችበት። "ለማንኛውም ተረጋጋ በቅርቡ ደግሞ እንደ ፈጣሪ የምታየውን መርማሪህን ሞት ትሰማለህ!!" አለች። "የአንቺን ሞት እኔ ነኝ የማፋጥነው"አለና ስልኩን ዘግቶ በፍጥነት ሁሌም በዙሪያው የማዬጠፉትን አማካሪዎቹን ጠራና አንድ ነገር ማድረግ እንዳለባቸው በጥብቅ አሳስቧቸው በአስቸኳይ አቅጣጫ አስቀምጠው ወጡ።

@amba88
3.4K viewsአምባዬ ጌታነህ❶ , 18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 21:54:30 "ናፊባ"
ክፍል ~ ዘጠና ሥድሥት~
በአምባዬ ጌታነህ @Adwa_1888
"አሞራዎቹ አሁንም የወደቀ ሬሳ ባለበት ሁሉ ዝቅ ብለው መብረራቸውን ይቀጥላሉ። ማሰሳቸው አይቀርም። የእኛ ሚሽን ደግሞ ከምታስቡት በላይ የተጠናከረ እና እጅግ በረቀቀ ቴክኖሎጂ የታገዘ ነው" "ደግሜ የምነግራችሁ ምንም ቢሆን ከእኛ እጅ እንደማያመልጡ ነው። አሁን ከእናንተ የምፈልገው ቁርጠኝነትንና አስተውሎትን ነው። እስካሁን ከላይ እስከታች የመንግስት መዋቅሮች የሚያደርጉት ጠፍቷቸዋል። ምን ማድረግ እንዳለባቸው ቢነጋገሩም ነገር ግን ከዚህ ቀደም ሲያደርጉት እንደነበረው ያለምንም ስምምነት ነው እየተለያዩ የሚገኙት። ስለዚህ እናንተም እንደ ቀደመ ስረመችሁ ራሳችሁን በሚገባ በመደበቅ ስራችሁን መከውናችሁን ቀጥሉ። እነዚህ የምትመለከቷቸው ተፈጥሮዎች ነፃ መውጣት ይፈልጋሉ። ከህዝቡ አስተሳሰብ ባህል ወግ ጋር የሚዛመድ ለሕብረተሰቡ ቅርብ የሆነ መሪና መዋቅር ያስፈልጋቸዋል። በትክክል ህዝቡን ህዝቡን የሚሸት ጥሩ ማዕዛ ያለው አስተዳደር መወለድ ይኖርበታል። ለዚህ ደግሞ አሁን ትልቅ ዋጋ መክፈል ያስፈልጋል። ያለምንም ዋጋ ምንም ውጤት አይመጣም። ስለዋጋ መክፈል መቼም አሁን አላብራራላችሁም። አስተውሉ ይህ ሞተን እንኳ ልናሳካው የምንችል አላማ ነው። አላማችን ይቺን ሀገር ከሚያምሱ አውሮጳውያን እና ስግብግብ ኢትዮጵያውያን መጠበቅ ነው ለዚህም ደግሞ እኔም እናንተም ሀላፊነቱ ተሰጥቶናል። ስለዚህ ምንም ወደ ኋላ የሚያስብል ነገር የለም" በማለት ኮስተር ብሎ እጆቹን ጭብጥ እያደረገ ሁላቸውንም አይኖቹን እያጉረጠረጠ ተመለከታቸው። ኢንስፔክተር ሸዋንግዛው በፕሮፌሰሩ ጠንካራ ንግግር ፊቱ እየፈካ በፅሞና ይመለከተዋል። "የያዝነው ቢደፋ እንኳ ከአፈር የምንለቅመው ጠንካራ ህልም ነው። ታውቃላችሁ ከምን አይነት ሕይወት እንደመጣን?" ብሎ ንግግሩን በእንጥልጥል ጀምሮ ትቶ ኢንስፔክተር ሸዋንግዛውን ወደመድረኩ ጠርቶ ስለመሰርመራ ሳይንስ በተወሰነ መልኩ እንዲያብራራላቸው እድሉን ሰጠው።ኢንስፔክተር ሸዋንግዛው ለተሰጠው እድል አመስግኖ ንግግሩን ጀመረ።
******
"እናቱ ጉያ ቢገባ እንደሚስቱ ቢሞት ራሱ ከመቃብርም ቢሆን ልናስነሳው ይገባል!" አለ የደህንነት ምኒስቴሩ። "አለቃ የጠፋው እኮ ተራ ሰልጣኝ መርማሪ ወይም ፖሊስ አይደለም። በጠመም በሞያው የተካነና የተራቀቀ ኢንስፔክተር ነው። በዛ ላይ በርካታ ጉዳዮችን በጥልቀት የመረመረ ነው ስለዚህ ምንም በቀላሉ ባንመለከተው መልካም ነው።"አለ የመረጃና ደህነነቱ ቢሮ። ለበርካታ ጊዚያት የብዙዎች ነፍስ ሲጠፋ ምንም አይነት እንቅስቃሴ ለማድረግ ፍላጎት የሌለው ይህ የመረጃ ና ደህንነት ቢሮ አሁን ግን በ ኢንስፔክተር ሸዋንግዛው መጥፋት ጥርሱን በመንከስ አስፈላጊ ነው ያለውን ሀይል ሁሉ በመጠቀምና የመረጃ ኢንተለጀንሱን በመጠቀም እየፈለገው ይገኛል። ይህ ድርጊታቸውም ከዛው ከድርጅቱና የበታች የስራ አመራሮች እና ፖሊሶችን ሳይቀር ሳያሳዝናቸውና ሳያስከፋቸው እንዳልቀረ ከውስጥ ለውስጥ ውይይቶቻቸው ለመረዳት ተችሏል። ይህም ደግሞ ከማህበረሰቡ አዲስ ተቃውሞ እንደሚያስነሳ ግልፅ ነው። "ግን እንዴት እንደዚህ ሊሰወር ይችላል? ተሰውሮ ነው ወይስ ሰውረውት? ደግሞ አንድም ቤተሰብ አለመኖሩ ትንሽ ግር ያሰኛል!"እየተባባሉ የኢንስፔክተር ሸዋንግዛውን አጠፋፍ ሴራና ብልህነት የተሞላበት እንደሆነ ይነጋገራሉ። "እኔ ግን ይቅርታ አድርግልኝና ኢንስፔክተር ሸዋንግዛው የራሱ የሆነ ምስጢራዊ ቡድን እንዳለው ምንም ጥርጥር የለኝም። ለዛም ነው ሁሉንም ቤተሰቦችን ጭምር ያሸሻቸው። ስለዚህ ድብቅ የሆነ ስራ ቸሚሰራበት ወይም ደግሞ ማንም የማያውቀው የራሱ የሆነ መደበቂያ ዋሻ ሳይኖረው አይቀርም እኔ የምገምተው ይሄን ነው።ስለዚህ አዲስ አበባ ላይ ቅንጡ የሚባሉ አካባቢዎች ለይ ልዩ የሆነ ትኩረት ብናደርግ ይሻላል ባይ ነኝ። ስለዚህ በዚህ መልኩ አቅጣጫ አስቀምጠን ብንንቀሳቀስ ባይ ነኝ እኔ በበኩሌ"በማለት ተጨማሪ ሀሳብ ሰጠው።
***
"አሁን የምትይዘው የምትጨብጠው ነገር አጥታለች። ስለዚህ አሁን እኔ በግልፅ የምነግራችሁ እሷ ትታችኋለች። በዛ ላይ አሁን ውጪ ላይ ምን እየተካሄደ እንደሆነ አልገባችሁም ስለዚህ ምን ታደርጋላችሁ መሰላችሁ አሁን። እሷን ሙሉ ለሙሉ መወንጀል ይኖርባችኋል። የእውነቴን ነው የምላችሁ ከምነግራችሁ በላይ በአሁኑ ስአት ተስፋ የመቁረጥ ደረጃ ላይ ደርሳለች በመሆኑም እናንተ አሁን ራሳችሁ ላይ ነገሮችን የምታወርዱበት ሀላፊነታችሁን የምትቀንሱበት ነው። ስለዚህ በአስተውሎትና በብልጠት መወሰን የምትችሉበት ደረጃ ላይ ናችሁ። እንጂ አንድ ጊዜ ከታሰራችሁ በኋላ እንኳ ዘወር ብላ ተመልክታችሁ ታውቃለች? እ ? እና እንዴት ነው እሷ ያልተማመነችብችሁን የካደቻችሁን እናንተ የምታምኑት? እሽኪ ምን አይነት የመታመን ጥግ ቢኖራችሁ ይሆን እንደዚህ ለእሷ አሰንደ አለት ፅንት ያላችሁት? በነገራችሁ ላይ ልክ ናችሁ ይሄን ሳላደንቅላችሁ አላልፍም ነገር ግን ምን አለ መሰላችሁ የምትታመኑት በታመኑላችሁ መሰረት መሆን አለበት። እንጅ ያኛው የእናንተን ችግር መግባት ከነአካቴው በመርሳት የራሱን አለም እየኖረ ላለ ግለሰብ እንዲህ አብዝቶ ራስን እስከማሳለፍ ድረስ መስጠት ለእኔ ተገቢ አይደለም ባይ ነኝ" አለና የመስፍንን ትከሻ መታ መታ አድርጎ ሒዎትንም በአይኖቹ ገርመም አድርጎ ሰላምታ ሰጥቷቸው ተሰናብቶ ትቷቸው ሊወጣ ሲል....

@amba88
2.7K viewsአምባዬ ጌታነህ❶ , 18:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 20:48:34 "ናፊባ"
ክፍል ~ ዘጠና አምስት~
በአምባዬ ጌታነህ @Adwa_1888
***
"እና አሁን ምንድን ነው የምናደርገው?" ለመጀመሪያ ጊዜ ኢንስፔክተር ሸዋንግዛው ግራ በተጋባ አነጋገር ፕሮፌሰር እስጢፋኖስን ጠየቀው።" መርማሪ ኢንስፔክተር ሸዋንግዛው አሁን ማን እንደሆነ አውቀናል።ከማን ጋርም እንደምንፋለም እንደዛው ስለዚህ አሁን የምናደርገው ነገር ቢኖር መረጃዎችን መሰብሰብ ይሆናል በአሁኑ ሰዐት በከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ያሉ ይመስለኛል። ስለዚህ እሷን የማደን ስራ እንሰራለን። ትዕዛዟ ከሀገር ውጪ ይሁን አይሁን የምናቀው ነገር የለም። ያው ከተራ ግምት በቀር ስለዚህ መኃረቤን ፈልጎ የማግኘት የእኛ ስራ ይሆናል። ምስሏን ፈልጌ እኔ ውጪ ላይ በሲቪል መልክ ለሚንቀሳቀሱ ልጆቼ እልክላችኋለሁ።" "ምን አልባት እስር ቤት ያሉት መስፍንና ማሕሌትን ብንጠይቃቸው አንዳች ነገር እናገኝ ይሆን?" አለ ኢንስፔክተር ሸዋንግዛው "በሚገባ እናገኛለን ነገር ግን መጀመሪያ መንግስት አንተን በመጥለፍ ውስጥ ሊያገኝ የሚችለውን ጥቅም ማወቅ ይኖርብናል። በዚህ ሁኔታ ሆነህ ለምርመራ ወደየትኛውም አካባቢ ማምራትህ አደገኛ ሁኔታ ነው። ስለዚህ መረጋጋት ያስፈልጋል"ብሎ ትከሻውን መታ መታ አድርጎት ወጥቶ ወደሌላኛው ክፍል አመራ። ኢንስፔክተር ሸዋንግዛው እጁን ወደ ኋላው አጣምሮ አይኖቹን ፊት ለፊቱ ከተቀመጠች የኢትዮጵያ ካርታ ምስል ሰክቶ ለረጅም ደቂቃ ቆመ። በአለላ የተሰራችው የኢትዮጵያ ካርታ ከወየነጠጅ አለላ የተቀለመች ወንዛይፈሪ ጥለትን የተቀባች ድንቅ የአክርማ ውጤት ነች። የሰበዞቿ አቀላለም ለጉድ ነው። በእጅ የተሰራች ሳይሆን በሰብሊሜሽን በጠሰንቃቄ የተቀረፀ የሕትመት ውጤት ነው የሚመስለው። እይታው የውስጡን ነፀብራቅ በመስተጋባቱና የልቡ ዐይን ከዐይኑ ጋር ግንኙነት በመፍጠሩ ተመስጦ ይመለከት ጀመር።" የትም ሁኚ የትም ያለሽበት መጥቼ እንደ አይጥ ወጥመድ ሆኜ ነው የማንቅሽ"አለና ከንፈሩን በእልህ ነከሰ። "ሌላኛው የአእምሮው ክፍል ማለትም ከስሜታዊነት ወጣ ብሎ ደግሞ "ሸዋን ተረጋጋ ነገሮችን በእልህ ሳይሆን በብልሀት ነው ማንቀሳቀስ ያለብህ ስለዚህ አሁን የአስተዋይ ውሳኔዎች ያሹሀል"በማለት አሁናዊው አዋቂው የአእምሮው አካል የሆነው ሰው ምክረ ሀሳብ አቀረበለት።የሰው ልጅ ከራሱ ጋር ሲሟገት በሁለት ጎራ ይሰለፋል። አንደኛው የአስተዳደጋችን ውጤት የሆነው ማለትም ይሄ Subconscious የምንለው የአእመሯችን ክፍል ሲሆን ይህም በቤተሰቦቻችን አስተዳደግ የተቀረፀ ቅርፅ እንዲሁም በማህበረሰባችን አመለካከትና ወግ የታነፀ የአእምሯችንን ሰማንያ ስምንት(88%) ፐርሰንት የሚይዘው ሰውዬ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የአእምሯችንን አስራ ሁለት (12%)ፐርሰንት የሚቆጣጠረው አሁናዊ ማንነታችን ወይም እኛ ባነበብናቸውና ባመዛዘናቸው መሠረት የምንቆጣጠረው አእምሯችን conscious mind ይባላል። አሁን ለምሳሌ አብዝሀኛው ሰው የሚግባባው በዚህ የአእምሮ ክፍል ነው። እንጅ ድብቁ የአእምሯችን ክፍልማ program የተደረገበት መንገድ የተለያዬ በመሆኑ ለስምምነት አያደርሰንም።
ኢንስፔክተር ሸዋንግዛው ከራሱ ጋር ሀሳቦችን ወዲህና ወዲያ ከሸመነ በኋላ ከነበረበት ክፍል ወጥቶ ቀጥቶ ለእሱ ወደ ተዘጋጀለት ክፍል አመራ። ኤሌዘርና ብሩክታዊት በሀሴት እየተዝናኑ እየተጫወቱ ነው። ልጆቹን ትኩር ብሎ ሲያቸው አንጀቱ በሀዘኔታ ተላወሰ። ትላንት በፍርሃት ተውጠው የነበሩ ልጆች አሁን ፍፁም ደስተኛ ሆነው እየተጫወቱ መሆናቸውን ሲያይ እፎይ አለ። ተሕሚድና ሲሐም እጅ ለእጅ ተያይዘው አጠገብ ለአጠገብ ሆነው እየተጫወቱ የልባቸውን እያወሩ መሆኑን ሲመለከት ተሕሚድን ፈልጎት የነበረ ቢሆንም ጨዋታቸውን ላለማቋረጥ ተዋቸው። ሁላቸውም በተረጋጋ ሁኔታ ላይ እንዳሉ ከተረዳ በኋላ ተመልሶ ወደ ፕሮፌሰር እስጢፋኖስ ቢሮ ሄዶ አንድ ትልቅ ወረቀት አወረደና በካርታ መልክ ስራውን የሚሰራበት ንድፈ ሀሳብ አስቀመጠ።
"ሀገርን የማፍረስ ሜንታሊቲን እንዴት አገኙት? የፈለገ ምን ያህል መጥፎ ነገር ቢደረስበት የሰው ልጅ እንዴት የገዛ ሀገሩን ከሚያፈርስ ሰው ጋር ይዋዋላል? ምን ያህል መርዝ የሆነ ዘር በውስጧ ቢዘራ ነው?" የሚል ጥያቄ ራሱን እየጠየቀ እያለ የቢሮው በር ተንኳኳ "ይግቡ"አለ ኢንስፔክተር ሸዋንግዛው። ከውጪ ያለው ሰው በሩን ከፍቶ ሲገባ እርስ በእርስ ሲተያዩ "ኦ ኢንስፔክተር ሸዋንግዛው እንኳን ደህና መጣህ በጣም ነበር የምወድህ"አለ የአድናቆት ፈገግታ እየቸረው።ኢንስፔክተር ሸዋንግዛው የናፊባን ልዩ ምርመራ በሀሳቡ እያሰላሰለ ስለነበር በቀጥታ ወደ ጉዳዩ ጋር ንግግር ለመጀመር አልቻለም። " ስለ ሼክስፔሯ ተዋናይት ምን አይነት መረጃ ሰብስበሀል?" አለ ልጁ ሸዋንግዛውን በአድናቆት እየተመለከተ "እንደ እውነት ለመናገር ምንም ያገኘሁት ነገር የለም። ነገር ግን ማግኘቴ አይቀርም"አለ ከንፈሩን በእልህ እየነከሰ። " አውቃለሁ ኢንስፔክተር ፕሮፌሰር በአንተ እጅግ ይተማመናል።ሁሌም ከአይናችሁ እንዳይጠፋ ልጆቹንም በደንብ ተከታተሏቸው። ስራውን ላለመስራት የሚያስተጓጉለው አንዳች ነገር ሊኖር አይገባም' እያለ ሁልጊዜም ይነግረን ነበር። አሁን ስለመሐረቤ የእኛ የስለላ አባሎች የደረሱበት ነገር አለ። ምን መሰለህ አሁን ላይ ተከታዮቿ በአንድም በሌላም ምክንያት እየተለይዋት እንደሆነ እና ከእርሷ ጋር ፀብ የሆነ ድርጊቷን የሚቃወም ከሚጥሏት ሰዎች መካከልም ወንድሟ እንዳለ ደርሰውበታል።" "በጣም ጥሩና ወሳኝ መረጃ ነው የነገርከኝ መልካም ስለዚህ አሁን በዋናነት ማድረግ ያለብን ዓደይ ሞል ላይ የፍተሻ ትዕዛዝ ማፃፍ ነው!" ውይ ለካ ፖሊስ አይደለሁም"አለና ከእንደገና እጁን አገጩ ላይ አስደግፎ በዝምታ ተዋጠ።
"ይህ በጣም የሚገርም ነው። ህዝባዊ ተቃውሞ መሪ አያሻውም።መጎዳቱ መማረሩ በራሱ እንዲህ በልብ እንዲገናኙ አድርጓቸዋል። በርግጠኝነት መንግስት በአሁኑ ሰዐት ምንም ለማድረግ እያሰበ እንደሆን ለመገመት በጣም ነው የሚከብደው። ይህ ሀይል ማንም አያስቆመውም። አቢዮቱ በትክክል ጀምሯል። ህዝቡ በቃን ያለ ይመስላል"አለ አንድ ወጣት "በሚገባ እንጅ መንግስትም እኮ ከመጠን በላይ ተጨማለቀ። የሟቾችን ነፍስ እንደምንም አልቆጠራቸውም። አሁን ደግሞ ይባስ ብለው ኢንስፔክተሩን ያስሩታል? ይሄ እኮ በህዝብ ላይ እንደመቀለድ ነው። ፈፅሞ ንቀት የበዛበት ድርጊት ነው እንጅ አሁን ኢንስፔክተሩን ማፈን ምን የሚሉት ድርጊት ነው?"አለ "እኔ ግን የሆነ ጥርጣሬ ነገር አለኝ! ምን አልባት በመንግስት ላይ ተቃውሞ ያለውና ህዝቡን ስሜታዊ እንዲሆን የፈለገ ከመንግስት ውጪ ሌላ አካል ጠልፎት ቢሆንስ? ምክንያቱም ይሄን ነገር መንግስት በእርግጠኝነት ሳያስበው ይቀራል የሚል እምነት የለኝም። ምክንያቱም እሱን መንካት ውጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል ያውቀዋል እና ከዛ አንፃር መንግስት ያደርገዋል የሚል እምነት ብዙም የለኝም" "ምን አልባት ጥርጣሬህ እውነት ሊሆን ይችላል አላውቅም ግን ደግሞ አንተ የተሳሳትከው ይሄን ሁሉ ማገናዘብ የሚችል ሊደር እንደሌለን አለማወቅህ ነው። እያንዳንዳቸውን አመጣጦች እስኪ ወደ ኋላ መለስ ብለህ አስባቸው። በደንብ ውጤቱ ምን ያህል ወጋ እንደሚያስከፍል ቢያውቅ ኖሮማ ቀዶሞ ከስር ከስር ከመጀመሪያ ጥፋቶች እየተማረ ተገቢውን የሆነ ማስተካከያ እዬሰጠ ችግሮችን እየፈታ ይሄድ ነበር"አለ
@amba88
2.7K viewsአምባዬ ጌታነህ❶ , 17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 18:48:23
ሰው ውሎውን ነው የሚመስለው! ይህ የኔ ውሎ ነው።
@Adwa1888 ላይ ስለ እሁድ ውሏችሁ አስቀምጡልኝ።
2.9K viewsአምባዬ ጌታነህ❶ , 15:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ