Get Mystery Box with random crypto!

እንደውሃ ኑር ይላሉ ጠቢባን ሲመክሩ፤ ውሃ በጉልበት የማያምን ነገር ግን ምንም ነገር የማያስቆመው | Amaraw

እንደውሃ ኑር ይላሉ ጠቢባን ሲመክሩ፤ ውሃ በጉልበት የማያምን ነገር ግን ምንም ነገር የማያስቆመው ድንቅ ነገር ነው፤ አንዲት ጠብታ ከቆይታ ብዛት ጣራ ትቀዳለች፤ በጉልበት ሳይሆን በትዕግስት፤ ወለል ላይ ውሃ ሲፈስ ውሃው የሚሄደው ወደ ተመቸው አቅጣጫ እንጂ እኔ በፈለግኩት ልሂድ ብሎ ሰጣ ገባ ውስጥ አይገባም፤ ለዚህም ነው ሃያል የሆነው።
ሰውነታችን ሰባ በመቶ ያህል ውሃ ነው፤ ሴሎቻችን ዘጠና በመቶ ውሃ ናቸው። ለዚህ ነው በትንሹም ቢሆን የውሃን ባህሪ ልንላበስ የሚገባን።
በመታገል ሳይሆን በመታገስ፤ እኛ ባልንበው ብቻ ሳይሆን ፤ ክፍት በሆነው መንግድ መጓዝ መቻል አለብን።
ውሃ ዝቅ ብሎ ስለሚጓዝ ምንም ነገር ሊደርስበት የማይችሉ ቦታዎች ላይ በቀላሉ ይደርሳል። ለሰው ሳይሆን ለተፈጥሮ መሸነፍ ጉልበተኛ ያደርጋል።

— ዶክተር ምህረት ደበበ
ውድ የአማራው ቻናልና የዜና ግሩፕ ቤተሰቦች እንዲት ሰነበታችሁ??? ለትንሽ ጊዜ ከናንተና ከሚዲያ እርቄ ስለነበር መረጃ መቀያየር አልቻልንም። አሁን ላይ ተፈጥረው የነበሩ ችግሮች በከፊልም ቢሆን ስለተፈቱ እንደተለመደው ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ከየአቅጣጫው ለማድረስና ከበፊቱ በተሻለ መንገድ በሁሉም የመገናኛ አውታሮች ማለትም:-
1ኛ በቴሌግራም ቻናል amaraw
2ኛ በቴሌግራም ግሩፕ ዜና ግሩፕ
3ኛ በፊስቡክ ፔጅ amaraw
4ኛ በዩቲዩብ ቻናል amaraw tube
5ኛ Instagram amarawtube1... amarawtube2
6ኛ Twitter @loti_man

በፈለጉትና በተመቸዎት የመገናኛ አማራጭ ይከታተሉን ስንል በአክብሮት እንጋብዝሃለን!!
amaraw Midea and news company
አማራው ሚዲያ

አማራነት ማንነት
ኢትዮጵያዊነት እውነት