Get Mystery Box with random crypto!

ትዝ ይልሽ እንደሆን አንድ አርገው የሰሩን እነዛ ቀናቶች ይታወስሽ እንደው ፍቅርን ያቋደሱን ትና | የአዲብ ግጥሞች እና ምልከታዎች

ትዝ ይልሽ እንደሆን
አንድ አርገው የሰሩን እነዛ ቀናቶች
ይታወስሽ እንደው
ፍቅርን ያቋደሱን ትናንሽ በአቶች

ከፍቅራችን ዋንጫ
ወይኑን ተጎንጭተው ጥለውን ከነፉ
ትዝታ ላይ ቀረ
መለየት የናደው የፍቅራችን ዳፉ

ዛሬም እንደትላንት
በትዝታ ብቻ እንድሮን ፈርዶብን
ገና ነው እያልን
መሄዱ ላይ ቀረን ሰአቱ ረፍዶብን

አዲብ
@Tufaw_muhe

@Am_in_love
@Am_in_love
@Am_in_love