Get Mystery Box with random crypto!

ስለ ሱልጣን አሊሚራህ የሳዑዲ ንጉስ ፈሃድ የሰጡት ምስክርነት... በአንድ ወቅት ሱልጣን አሊ | Ahmed Habib Alzarkawi

ስለ ሱልጣን አሊሚራህ የሳዑዲ ንጉስ ፈሃድ የሰጡት ምስክርነት...

በአንድ ወቅት ሱልጣን አሊሚራህ በሳዑዲ ሪያድ ከተማ ከሳዑዲ ሰልጣን ማለትም ከመሊክ ፋይሰል ጋር በተገናኙ ጊዜ መሊክ ፋሃድ ለሱልጣን አሊሚራህ እንዲህ አሏቸው " ሱልጣን አሊሚራህ ሆይ! ከመሊክ ፈይሰል ጊዜ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ለብዙ አመታት ተመልክቾታለሁ። የአንተ ፊት አይቀየርም ሁሌ በኑር እንደተሞላ ነው። እባክዎትን ምስጢሩ ምን ይሁን ብሎ ጠየቃቸው። በዚህ ጊዜ ሱልጣኑ እንዲህ ብሎ መለሰላቸው። እኔ በባንክ ያጠራቀምኩት ገንዘብ የለኝም ። እንቅፍ የሚነሳኝ ድርጅት የለኝም። ስለዚህ የሚያሳስብኝ ከዱንያ ይልቅ የአኼራ ጉዳይ ስለሆነ ትዕዛዙን ለመፈፀም ብቻ ነው የሚተጋው ብሎ እንደመለሱላቸው በወቅቱ አብሮት የነበሩ ሠው ነገሩኝ። በዚህ ጊዜ የሳዑዲ ንጉስ መሊክ ፋሃድ እውነትህን ነው እኛ በሚያሳሰበን ብዙ ነገር ውስጥ ገብተን ነው እንዲህ ለመሆን ያልታደልነው ስሉ " መለሱላቸው። .====

=== ሌላኛው የሳኡዲ የዘመኑ ታዋቂ ባለሐብት ደግሞ " ገንዘብ አገኘን ነገር ግን ጤና አጣን " ብሎ ለሱልጣኑ መናገራቸውም ተሰምተዋል።
አዎ ሱልጣን አሊሚራህ ገንዘብ በእጃቸው ሳይነኩ ፣ ሳይቆጥሩ ነው የሞቱት። እንደ ኢትዮጵያ ንጉሶች ፣ እንደ ህወሓት መሪዎች ፣ እንደአፋር አመራሮች የሀገር ሀብት ፣ የህዝብ ሀብት በስልጣናቸው ተጠቅመው ከድሃ ጉሮሮ ነጥቀው ጎረቤት ሀገርና አውሮፓ ድረስ ይዘው አልሸሹም ። አልፎም በሚስቶቻቸው ፣ በልጆቻቸው ፣ በወንድሞቻቸው ስም ከህዝብ በነጠቁት ገንዘብ ሆቴልና ፈብሪካ ገንብተው ድንጋይ ላይ ድንጋይ ገንብረው ህንፃ አንፀው በታሪክም ሆነ በሚመሩት ህዝብ ዘንድ አልፎም ለህሊና ፍርድ አንገት ደፍተው ለቁጭት የሚዳረጉበት አንገት የሚያስደፋ ጥቁር ታሪክ አለስመዘገቡም። የአፋር ሱልጣን በምድሩ ቆይታቸው እንደተወደሱ ፣ እንደተከበሩ ከሚመሩት ህዝብ ጉሮሮ ነጥቀው አንዳች ህንፃና ፈብሪካ ሳይገነቡ ለገንዘብና ለሐብት ጀርባ እንደሰጡ እንደተጠየፉ ይህን ምድር ተሰናበቷት።

ሱልጣን አሊሚራህ ማለት በኢኮኖሚ በአለም በቱጃሮች ተርታ የምትሰለፈውን የሳዑድ አረቢያ ንጉስ መሊክ ፋሃድ ተማርኮባቸው የተደመመሙበት ስብዕና ተላብሰው የተወደዱ የጀግና ኢትዮጵያዊ ነበሩ። ሱልጣን አሊሚራህ እንዲህ አይነት ጀግና አባት ጀግና መሪ ነበሩ።

ምንጭ፦ የታሪክ ፀሃፊ Allo Yayo Abu Hisham