Get Mystery Box with random crypto!

ኤርትራ ዳግም ወደ ኢጋድ ተመለሰች ኤርትራ ከ16 ዓመታት በኋላ ዳግም የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት | Ahmed Habib Alzarkawi

ኤርትራ ዳግም ወደ ኢጋድ ተመለሰች

ኤርትራ ከ16 ዓመታት በኋላ ዳግም የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (IGAD) መድረክን መቀላቀሏን ይፋ አደረገች ። ኤርትራ የኢጋድ አባልነቷን ያቋረጠችው እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር በ2007 ዓ.ም ነበር ። የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስትር የማነ ገብረ መስቀል ኤርትራ የኢጋድ አባልነትዋን መቀጠሏን ትናንት በይፋዊ የትዊተር የመገናኛ አውታር ገጻቸው ጽፈዋል።

ኤርትራ በመድረኩ የአባልነቷ እንቅስቃሴዋን ዳግም ማስቀጠሏን እና ጅቡቲ በተካሄደው በ14ተኛው የኢጋድ መደበኛ ጉባኤ ላይ መካፈሏንም አክለዋል ። አቶ የማነ ኤርትራ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችበትን ምክንያት ባይገልጹም፣ ከሌሎች የኢጋድ አባል ሃገራት መቀላቀልና በአካባቢው ሰላምና መረጋጋት እንዲስፈን ለማገዝ መፈለጓን ጠቅሰዋል። የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን ስምንት አባላት ሲኖሩት፦ እነሱም ኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኡጋንዳ እና ዳግም የተመለሰችው ኤርትራ ናቸው ። ኤርትራ ከ16 ዓመታት በፊት ከኢጋድ ራሷን ያገለለችው የኢትዮጵያ ወታደሮች ሶማሊያ መግባታቸውን በመቃወም ነበር ።