Get Mystery Box with random crypto!

ጆዜ ሞሪንሆ ማንችስተር ዩናይትድ አንፊልድ ላይ በሊቨርፑል ስለደረሰበት የ7ለ0 ሽንፈት ተጠይቀው የ | Ahmed Habib Alzarkawi

ጆዜ ሞሪንሆ ማንችስተር ዩናይትድ አንፊልድ ላይ በሊቨርፑል ስለደረሰበት የ7ለ0 ሽንፈት ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ፦

"እነዚህ ውጤቶች የፕሮጀክቱ እና የመልሶ ግንባታው አንድ አካል ናቸው። ለኤሪክ ቴን ሀግ ምንም አይነት ምክር መስጠት አልፈልግም ምክንያቱም እሱ እራሱ ትልቅ አሰልጣኝ ነው። አሁን ያለው የቡድን ስብስብ እኔ ከነበርኩበት ጊዜ በአስር እጥፍ የተሻለ ነው ስለዚህ ትልልቅ ዋንጫዎችን ለማሸነፍ የተሻለ አቋም ላይ ይገኛል። ዩናይትድ በአሁኑ ሰአት የሚጎድለው ብቸኛ ነገር ጥራት ያለው አጥቂ ብቻ ነው ከዛ ውጪ ዩናይትድ በጣም አደገኛ ቡድን ነው ምናልባትም በአሁኑ ሰአት አለማችን ላይ ካሉ ምርጥ ሶስት ቡድኖች አንዱ ነው። አንድ ውጤት ምንም ነገር አይቀይርም በየትኛው ቡድን ላይ ሊከሰት ይችላል።" - ጆዜ ሞሪንሆ