Get Mystery Box with random crypto!

ተዋናይ ብሩስ ዊሊስ የመርሳት ህመም እንዳለበት ቤተሰቡ ተናገሩ ====================== | Ahmed Habib Alzarkawi

ተዋናይ ብሩስ ዊሊስ የመርሳት ህመም እንዳለበት ቤተሰቡ ተናገሩ
========================
የ67 አመቱ ተዋናይ ብሩስ ዊሊስ ከ3 አመት በፊት የመጨረሻ ፊልሙን ሲሰራ ቃለ ተውኔቱን መያዝ ስላልቻለ የፊልሙ ዳይሬክተር የሱን ፓርት እንደቀነሱለትና ብዙ ንግግር እንዳይኖረው እንዳደረጉ ተናግሮ ነበር። እንደዛም ሆኖ ቃለ ተውኔቱን እየረሳ ተቸገሩ። ተዋናዩ የመርሳት ህመም እንደጀመረው ግን የጠረጠረ አልነበረም።

ከአምና ጀምሮ ቃላት እየጠፉበት (Aphasia) አጋጥሞት ሀሳቡን መግለፅ ከብዶት ነበር። ለወትሮው ረጃጅም የፊልም ንግግሮችን በቃሉ ይይዝ የነበረው ተዋናይ አሁን ግን የእለት ተ እለት ቃላት እየጠፉበት "እ.....እ.....ይሄ ምንድነው የሚባለው....እ...እንትን" ማለት አብዝቷል።

ብዙ አይነት ምርመራ ተደርጎለት Fronto-temporal Dementia የሚባለው የመርሳት ህመም እንዳለበት ታውቋል። ይሄ አይነት የመርሳት ህመም የፊተኛውን የአእምሮ ክፍል በይበልጥ የሚያጠቃ ሲሆን ከትውስታ እክል (Memory deficits) በተጓዳኝ ከፍተኛ የስብእና ለውጥ (Personality disorder) ያስከትላል።

የብሩስ ዊሊስ ቤተሰብ ዜናውን ይፋ ያወጡት ስለ'መርሳት በሽታ' ግንዛቤ ይፈጥራል ብለው እንደሆነ ተናግረዋል።

የየእምሮ ህመም ከ5ሰዎች አንድ ሰው ላይ ይከሰታል። ሀብታም ደሀ፤ የተማረ ያልተማረ፤ ብሄር ወይም ሀይማኖት አይለይም።

ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው።