Get Mystery Box with random crypto!

በህክምና ስህተት 1አመት ከ8 ወር በአልጋ ላይ እየተሰቃየ ያለ ወንድማችንን እናግዝ ወጣት ታ | 🇪🇹ALL IN ONE SHOP🇪🇹 🇪🇹ሁሉንም በአንድ ሱቅ🇪🇹

በህክምና ስህተት 1አመት ከ8 ወር በአልጋ ላይ እየተሰቃየ ያለ ወንድማችንን እናግዝ

ወጣት ታደሰ ገ/ማርያም ድንቅ ብቃት ያለው ተወዛዋዥ የስራ ባልደረቦቹ የሚመሰክሩለት መድረክ ላይ በፈጠራ ችሎታው፣ ጉልበቱን ሳይሰስት ለሚለግሰው ባህላዊ አጨፋፈር ከሚደነቁ ተወዛዋዦች መካከል አንዱ ነው።

ቤተሰብ መስርቶ ገና ሀ ብሎ መኖር ሲጀምር አልጋ ላይ አስቀሩት

ልጠይቀው ሄጄ በአይን ካየሁት ሰአት ጀምሮ ውስጤ ተረበሸ ያ የማቀው ተጫዋች ሙያውን አክባሪ ጓደኛዬን አልጋ ላይ መብላት ሳይችል ፤መናገር ሳይችል የወለዳትን ልጅ የአባትነት ፍቅሩን እያጣጣመ ባለበት ሰአት ነው ለአልጋ የበቃው ሳየው በጣም አዘንኩ ነገ በእኔ ነው

በስቃይ የሚገኘውን ታደሰ ገ/ማርያምን ልንረዳው ልንጮህለት ይገባል ስንቶች ናቸው እንደ ቀልድ
አመመኝ ብለው ገብተው የሚቀጠፉት አቅም ስለሌላቸው ብቻ እውነት በውስጣቸው ኖሮ ተበድለው የሚኖሩ ቤት ይቁጠረው

የውጪ ህክምና እርዳታ የሚለግሰው ግለሰብ ወይንም ድርጅት ቢገኝ ቢታከም ታዴ መዳን ይችላል ሰው ነንና ነገን ምን እንደምንሆን መውደቂያችን ምን እንደሆነ አናቀውምና በተቻለን አቅም እንረባረብለት።

ታዴ የሚመገበው በአፍንጫው በተገጠመለት የመመገቢያ ቱቦ ነው ስቃዩን አስቡት

ሰው እንዴት በሰላም ልታከም ብሎ ገብቶ ሲወጣ ሳይናገር ሳይራመድ አልጋ ቁራኛ አርገውት ይመልሱታል እውነት ግን በመንግስት ሆስፒታሎች በአብዛኛው ተለማማጅ ሀኪሞች ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ነብስ እንደቀልድ መጫወትስ ተገቢ ነው???

በተመሳሳይ በወጣት ቢኒያም ላይ በደረሰው የሞራል ስብራት አካል ጉዳተኛ ተብሎ አንድ ትልቅ የህክምና ተቋም ከትምህርት ገበታህ ተሰናብተሀል ሲል ምን ያክል በህክምና ተቋማት ውስጡ ችግር እንዳለ የሚያሳይ ሲሆን በተጨማሪም የህክምና ስህተቱም ላይ ተጠያቂነት እንደሌለ እንዲህ ነገሮች በሰፊው በየሚዲያ ሲሽከረከር ብቻ መፍትሄ የሚሰጠው ከሆነ የመናገር አቅም የሌላቸውስ ማን ህመማቸውን ይረዳ

መልእክት በመፃፍ ሀሳብ አስተያየት መስጠት ለምትፈልጉ አናግሩን

ፈጣሪ ከከፋ ህመም ይጠብቃችሁ እያልኩ እሰናበታለሁ መልካም ጊዜ።



https://fb.watch/eiuWIyMGhP/