Get Mystery Box with random crypto!

አረፋ 1 ቀን ብቻ ቀረዉ ለየቲሞች ያቀድነዉ እቅዳችን ምንምኳን ስራ ቢሰራም ነገርግን የታቀደዉ | አል ሂዳያ የየቲሞች መርጃና በጎ አድራጎት ጀማአ 0993632424//0703136300አዲስ አበባ

አረፋ 1 ቀን ብቻ ቀረዉ

ለየቲሞች ያቀድነዉ እቅዳችን ምንምኳን ስራ ቢሰራም ነገርግን የታቀደዉ ትልቁ አላማችን ግማሹ አልተሳካም እስካሁን ድረስ ቃል ተገብቶላቸዉ ልብስ ያለበሱ የቲሞች አሉን። ምግብ ልናስገባላቸዉ ቃል የገባንላቸዉ ቤታቸዉ ሚላስሚቀመስ የሌላቸዉ ሰዎች አሉን። ጎዳና ተዳዳሪ ሆነዉ ፀሀይና ብርድ የተፈራረቀባቸዉ የሚኖሩ ሙስሊም ነፍሰጡር እናቶች አሉን። ነገር ግን ይሄንን ሁሉ ማድረግ አልተቻለም። ወላሂ በጣም ያሳዝናል አንድም ቀን ልሰራቸዉ ያሰብኳቸዉ ኸይር ስራዎቼ እቅዶቼ ይከሽፉብኛል ብዬ አስቤ አላቅም ነበረ። ለካስ ኸይርስራም ምቀኛ ይበዛበታል። ይሄንን ኸይርስራ እንዳልሰራ ከመጅሊስም ጭምር ጫና ፈጥሮብኛል። እና እንዳስብ ያደረገኝ አንድ ነገር አለ እሱም ደሞ በዚች ምድር የተቸገሩ ሰዎችን የሚረዳ ሰዉ ሳይሆን የጠፋዉ እነሱ እንዳይረዱ በመሀል ጣልቃ እየገቡ የሚረብሹ አካላቶችና በተቸገሩ ሰዎች ስም ገዘብ እየሰበሰቡ የሰዉ ሀቅ የሚበሉ የየቲም ገንዘብ የሚመገቡ አካላቶች ስለበዙ ነዉ።

ለነገሩ ይሄ ኸይር ስራኮ አሏህ ያገራለት ሰዉ ብቻ የሚሰራዉ ነዉ አሏህ ያላገራለት ሰዉ ግን ሺ ጊዜ እዉቀት ቢኖረዉና ዳኢ ቢሆን ተሰሚነት ቢኖረዉ ሀብታም ቢሆን ሰዉ ቢወደዉ። ምንም ትርጉም የለዉም ያዉ ቀልቡ ለኸይር ስራ የተዘጋች ናት ታስመስላለችጂ አትተገብረዉም ወሬ ላይጂ  ተግባር ላይ አይገኙም።

ብቻ አሏህዬ ለኸይር ስራ ሲሆን እጃቸዉን የሚዘረጉጂ። ኸይር ስራ ሲባሉ ከሚሸሹ ሰዎች አርቀኝ ጠብቀኝ። ያረቢ እኔስ የምሰቃየዉዐበወንጀሌ ነዉ እነዛ የቲም ህፃናት ግን በየትኛዉ ወንጀላቸዉ ነዉ የሚሰቃዩት ያአሏህ ፈረጃዉን አንጣልንጂ ዝም አትበለን

አል ሂዳያ የየቲሞች መርጃና በጎ አድራጎት ጀማአ።ሰደቃ ወጀልን ታብሳለች ረሱል (ﷺ)
https://t.me/ALHIDIYAWOCH