Get Mystery Box with random crypto!

'መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::' /(ማቴ ፫:፫/) እንኳን አደረሰን!! | አለማመኔን እርዳው ጌታዬ #ማር 9፥24

"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"
/(ማቴ ፫:፫/)

እንኳን አደረሰን!!

ዝክረ ቅዱሳን ላልደረሳቸው እናድርስ እናስፋ ስለ ሃገራችን እንጸልይ ንስሃ እንግባ!!

"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::" /ማቴ ፫:፫/

ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!

ስለ ንስሃ

ከቅዱስ ሙሴ ጸሊም የምንማራቸው 7 ነገሮች።

፩, ቅዱስ አብረሃምን መምሰል( ፈጣሪውን ተመራምሮ አገኘ)::

፪, ዓለምንና የዓለምን ነገሮች መተው።

፫, የንስሃ ሕይወት( ንስሃን በትጋት መፈጸም)።

፬, መታዘዝ (የሚታዘዘውን ሳያጓድል መስራትን)።

፭, ለሌሎች መኖርን።

፮, በሰው አለመፍረድን።

፯, ትሕትናን።
እነዚህን እናስተውላቸው!!!

ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!

እናስተውል!!
1፡ ጥሩ ክርስትና ፈጥኖ የሚገኝ አይደለም፡፡ ትእግስትን ይጠይቃል፡፡
2፡ ሰይጣን እኛን ኃጢአት በማሠራት አይረካም፡፡ የሚፈልገው ተስፋ ማስቆረጥ ነው፡፡
3፡ በእምነት የሚደረግ የትኛውም ጸሎት መፍትሔ አለው፡፡
4፡ የበጎ ለውጥ እናት *ዓላማና ቁርጥ ውሳኔ* ናቸው

5 ነገሮችን በደንብ ያዙ።
1, አላማ

2 , እምነት

3, ጥረት

4 ጥንቃቄ

5 ጽናት
=>እነዚህን ያዟቸው ተጠቀሙባቸዉ ኑሯቸው።

ዝክረቅዱሳን (ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት)

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
https://t.me/zikirekdusn