Get Mystery Box with random crypto!

የቱርክ የጦር መርከብ በሞቃዲሾ ወደብ ከሁለት ወራት በፊት ከሶማሊያ ጋር የ10 አመት የወታደራዊ | Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

የቱርክ የጦር መርከብ በሞቃዲሾ ወደብ

ከሁለት ወራት በፊት ከሶማሊያ ጋር የ10 አመት የወታደራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትብብር ስምምነት የተፈራረመችው ቱርክ መርከቧን ወደ ሞቃዲሾ ልካለች።

በመርከቧ አቀባበል ላይ ንግግር ያደረጉት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ፥ ሀገራቱ የተፈራረሙት ስምምነት ሶማሊያ የባህር ግዛቷን በራሷ መቆጣጠር እንድትጀምር ያስችላታል ብለዋል።

ሞቃዲሾ እና አንካራ የወታደራዊ ትብብር ስምምነቱን የተፈራረሙት ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው ከተገለጸ በኋላ ነበር።

ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ በዚሁ ወቅት ከቱርክ ጋር የተደረሰው ስምምነት ከኢትዮጵያም ሆነ ከሌሎች ሀገራት ጋር ግንኙነትን የሚያሻክርና ጸብ የሚያጭር እንዳልሆነ መናገራቸው ይታወሳል።

የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ቲክቶክ: https://www.tiktok.com/@alainnewsamharic
X (ትዊተር): https://twitter.com/AlAinAmharic
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ድረገፅ: https://am.al-ain.com
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic