Get Mystery Box with random crypto!

ውድ የአሐዱ ባንክ ቤተሰቦች፣ ባንካችንን በቅርቡ ደማቅ እና ይፋዊ በሆነ መልኩ ተመርቆ ወደ ስራ መ | አሐዱ፡ባንክ / Ahadu Bank S.C.

ውድ የአሐዱ ባንክ ቤተሰቦች፣
ባንካችንን በቅርቡ ደማቅ እና ይፋዊ በሆነ መልኩ ተመርቆ ወደ ስራ መግባቱ ይታውሳል፡፡ ይህንንም ተከትሎ በባንኩ ስም በተከፈቱ የሀሰት ማህበራዊ ገፆች ስለባንካችን የሀሰት መረጃዎች እንዳሉ ለመረዳት ችለናል፡፡ከዚህም መካከል አሐዱ ባንክ ለደንበኞቸች የቤት ሽልማት የሚስገኝ የእጣ ፕሮግራም ማዘጋጀቱን የሚገልፅ መልዕክት አንዱ ነው፡፡ በዚህም መሰረት ክቡራን የባንካችን ባለአክሲዮኖች እና ቤተሰቦች፣ ይህ መረጃ ፍጹም ሀሰት መሆኑን በባንካችን በኩል የተዘጋጀ ምንም አይነት የሽልማት ወይም የእጣ ፕሮግራም እንደሌለ በማክበር እየገለፅን የባንካችን ይፋዊ የማህበራዊ ገጾች የሚከተሉት ናቸው፦
•https://t.me/ahadubanket TELEGRAM
•https://twitter.com/Ahadu_bank TWITTER
•https://www.instagram.com/ahadu.bank/ INSTAGRAM
ወደፊትም ከተመሳሳይ የሀሰት መረጃዎች ራሳችሁን እንድትጠብቁ እያሳሰብን በዚህ ረገድ አስፈላጊውን እርምጃ የምናከናውን መሆኑን እንገልጻለን፡፡
አሐዱ ባንክ
ከብዙዎች ለብዙዎች