Get Mystery Box with random crypto!

በ10 አመቱ በአባቱ ካሜራ ነበር ቀረፃ የተለማመደው ፤ ትምህርት ላይ ግን ብዙም አነበረም ፤ በትክ | AHADU

በ10 አመቱ በአባቱ ካሜራ ነበር ቀረፃ የተለማመደው ፤ ትምህርት ላይ ግን ብዙም አነበረም ፤ በትክክል ማንበብ እንኳን ከብዶት ነበር ፤ 18 አመቱ ላይ ረጅም የሆኑ ፊልሞችን ያለማንም እርዳታ መስራት ችሎ ነበር ፡፡ ግን አንድህልም ነበረው በደቡብ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ገብቶ የፊልም አሰራር ጥበብን መማር ፤ ግን ለዩኒቨርስቲው አትመጥንም ብለው እንዳይማር ከለከሉት ! ልቡ ተሰበረ አዘነ ግን አርፎ አልተቀመጠም ለህልሙ ሮጠ ለፋ ብዙ ጣረ ፤ በዛን ጊዜ በወቅቱ የተሰሩትን ፊልሞች ሁሉ አይቶ ለመጨረስ ሞከረ ፤ የዩንቨርሳል ስቱዲዮ ዘበኞችን አልፎ ፊልሞች የሚሰሩበትን ጥበብ ተደብቆ ያይ ነበር ፤ በመጨረሻም ዩንቨርሳል (Universal studio) ጉጉቱን አይቶ በነፃ ቀጠረው ፡፡

ይሄ ሰው ለሚወደው ነገር ብዙ ዋጋ ከፍሏል ! አሁን የአለማችን ከፍተኛው ተከፋይ የፊልም #ዳይሬክተር ነው ! የሚገርመው ከዛ ሁሉ ውጣ ውረድ ቡሃላ እዚ ደረጃ ከደረሰ ቡሃላ አትማርም አላስተምርህም ብሎ የከለከለው ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ሊሰጠው ሲል ለዩኒቨርስቲው አትመጥንም ብሎ ያባረረኝ የበላይ መምህር ከፈረመበት ብቻ ነው ሽልማቱን የምቀበለው ብሎ ነበር መቼስ Jurassic Park ፣ Indiana Jones ፣ Transformers ፊልሞችን የማያውቅ የለም

ይሄ ሰው የአለማችን ታዋቂው የፊልም ዳይሬክተር #ስቴቨን_ስፒልበርግ ነው

እኛስ ግን ምንድነው ማሳካት የምንፈልገው ?

@Ahadu_goh
@Ahadu_goh