Get Mystery Box with random crypto!

15 ጊዜ 1ኛ ክፍልን የደገመው ናይጄሪያዊ ተማሪ..!!! 15 አመታትን አንድ ክፍል ውስጥ ለዛውም | AHADU

15 ጊዜ 1ኛ ክፍልን የደገመው ናይጄሪያዊ ተማሪ..!!!

15 አመታትን አንድ ክፍል ውስጥ ለዛውም 1ኛ ክፍልን ሲደጋግም ከርሟል ጆሴፍ የተሰኘው ናይጄሪያዊ ተማሪ፡፡

አንደኛ ክፍል ብቻ 15 አመታትትን አሳልፏል፡፡

ወላጅ እናቱ እንደምትለው ከ15 አመታት በኋላም ቢሆን ለጆሴፍ ትምህርት ቤት ማርፈድ አይታሰብም ቀድሞ ከክፈል መውጣትም እንዲሁ፡፡ ቢሆንም ግን በየአመቱ መጨረሻ ከተማሪዎች ሁሉ የመጨረሻውን ደረጃ ያመጣል፡፡

የቁመት እድገት ውስንነት ያለበት ጆሴፍ አሁን 20 አመቱን ደፍኗል ነገር ግን 1ኛ ክፍል ነው፡፡

መምህራኑ ጆሴፍን አትፍረዱበት የመርሳት ችግር ስላለበት ነው ይላሉ፡፡ አሁን የተነገረውን ከደቂቃዎች በኋላ ከናካቴው ይረሳዋል ፡፡

ናይጄሪያዊው ጆሴፍ ግን የፈጀውን ጊዜ ይፍጅ አንድ ቀን ሁሉንም አሳካዋለሁ አንደውም #የሃገሪቱ_ፕሬዝዳንት የመሆን ህልሜንም አሳካለሁ ይላል፡፡

@Ahadu_Goh