Get Mystery Box with random crypto!

ምን ያህል አትችልም የሚሉ ቃላትን ተሸክመሀል ? ይቅርብህ ፣ አይሆንም ፣ አትችለውም ፣ አይሳካ | 🦋የህይወት ሳይኮሎጂ🦋

ምን ያህል አትችልም የሚሉ ቃላትን ተሸክመሀል ?

ይቅርብህ ፣ አይሆንም ፣ አትችለውም ፣ አይሳካልህም ፣ አትመጥኚም፣ አይገባሸም ፣ ላንቺ አይሆንም የሚሉ ቃላቶች ምን ያህል ከመንገድሽ መድረስ ከተመኘሽበት አሽሽተውሻል? ዛሬ አለም ያደነቃቸው ጀግንነታቸው ያስደነገጠን ምን አይነት ጥበብ ነው ብለን የተደመምንባቸው ሰዎች ልክ ሲጀምሩ ሁሉም ተቃውሟቸው እንደነበርስ ምን ያህል ሰምተናል?

ስኬት ማደግ አዲስ መንገድ መሞከር ለብዙዎች እብደት ነው ስለዚህ የማይሆን ነገር እንደሆነ ይነግሩናል ሆነው ስላላዩት ማሳካት ስላልቻሉ ሌላው እንዲያሳካው አይፈቅዱም ! ምክንያቱም ማንም ሰው መበለጥ አይፈልግም ስለዚህ እንዳትበልጣቸው እንደተሸነፍክ ይነግሩሀል ፣ እንዳታሸንፋቸው የተሸነፍክ እንደሆንክ አድርገው ከመንገድህ ያቆሙሃል ።

ወገኔ ብልጥ ሁን እንጂ ንቃ ራስህን እየው ካንተ በላይ አንተን የሚያውቅህ ማነው? ካንተ በላይ ችሎታህን ሊነግርህ የሚችለው ማነው? ለምን ራስህን ማንነትህን አቅምህን አሳልፈህ ትሰጣለህ? ትችላለህ ትችያለሽ!

joun us @adviceeeeee
◉◉◉◉◎◎ ●●◉◉◉◉
Join & share

@wintay