Get Mystery Box with random crypto!

ዣቪ በአል ሳድ የተጠቀመውን ሶፍትዌር መጠቀም ይጀምራል ይህም የጨዋታውን ታክቲካዊ ገጽታ የሚያግዝ | አዶላ ስፖርት

ዣቪ በአል ሳድ የተጠቀመውን ሶፍትዌር መጠቀም ይጀምራል ይህም የጨዋታውን ታክቲካዊ ገጽታ የሚያግዝ ትልቅ መረጃን ለመተንተን የሚያስችል ነው፤

ፕሮግራሙ የተዘጋጀው በጆአን ቪላ፣ የዣቪ አማካሪ እና በኩባንያው ኮግኒያ ነው።

ሶፍትዌሩ ታክቲካዊ ሁኔታዎችን አውቶማቲካሊ ለመለየት ያስችላል።

ሶፍትዌሩ በአንድ ጨዋታ ወቅት ሁሉንም ታክቲካዊ ሁኔታዎችን በአውቶማቲካል ለመለየት ያስችላል፡- ብልጫ፣ ቦታዎች፣ አለመመጣጠን እና ሁሉንም ነገር።

ይህም አሰልጣኞች በጋራ ብቻ ሳይሆን በግልም ለመስራት እና ለማሻሻል መሰረት እንዲኖራቸው ያስችላል።።

ጆአን ላፖርታ እና ቦርዱ ኮማንን የሚተካ ዘመናዊ አሰልጣኝ ይፈልጉ ነበር እና ዣቪ መስፈርቱን የሚያሟላ መሆኑን ከወዲሁ ግልፅ አድርጓል።

የኮግኒያ አዲስ ሶፍትዌር ማካተቱም ምሳሌ ነው። ፔፕ እና ኤንሪኬም በቅርቡ ሊጠቀሙበት ይችላሉ።

ቪላሪያል በስፔን ውስጥ ከተጠቀሙት የመጀመሪያ ቡድኖች አንዱ ነው!