Get Mystery Box with random crypto!

Addis Admass

የቴሌግራም ቻናል አርማ adissadmas — Addis Admass A
የቴሌግራም ቻናል አርማ adissadmas — Addis Admass
የሰርጥ አድራሻ: @adissadmas
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.88K
የሰርጥ መግለጫ

የአዲስ አድማስ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
=====
አዲስ አድማስ https://bit.ly/2V1zyZQ
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2V0I6jx
ትዊተር↠ https://bit.ly/33fDhaP
ቴሌግራም↠ https://bit.ly/2JgeCvG
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3q2hXiv
የእርስዎና የቤተሰብዎ

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 16:42:49
የገጣሚና ደራሲ ነቢይ መኮንን 3 መጻሕፍት ሰኞ ይመረቃሉ

*ምረቃውን በተመለከተ በኢትዮጵያ መዛግብትና ቤተ መጻህፍት ኤጀንሲ መግለጫ እየተሰጠ ነው
531 views13:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 12:10:14
የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ክፍያን በቴሌብር መፈጸም የሚያስቾል አሠራር ተጀመረ
ኢትዮ ቴሌኮም ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ጋር የአገልግሎት ክፍያዎችን በቴሌብር ለመፈጸም የሚያስችል ስምምነት ዛሬ በሸራተን አዲስ ፈጸመ
የውል ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ፍሬህይወት ታምሩና የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አማረ ናቸው:
798 views09:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 10:40:05
የገጣሚና ደራሲ ነቢይ መኮንን 3 መጻሕፍት ሰኞ ይመረቃሉ
803 views07:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 10:38:53 የገጣሚና ደራሲ ነቢይ መኮንን 3 መጻሕፍት ሰኞ ይመረቃሉ

*ዛሬ ከሰዓት በኋላ ስለምርቃቱ መግለጫ ይሰጣል

የተወዳጇ አዲስ አድማስ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የሆነው አንጋፋው ደራሲ፣ ገጣሚና ተርጓሚ ነቢይ መኮንን ሦስት መጻሕፍት የፊታችን ሰኞ ይመረቃሉ፡፡

መጻሕፍቶቹም፡- ነገም ሌላ ቀን ነው፣ የመጨረሻው ንግግር እና የእኛ ሰው በአሜሪካ የተሰኙት ሲሆኑ ፤ ታላላቅ የኪነጥበብ ባለሞያዎች ሥራዎቻቸውን በሚያቀርቡበት መድረክ ነው የምርቃት ሥነሥርዓቱ የሚከናወነው ተብሏል፡፡

ሰኞ ነሐሴ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ቦሌ በሚገኘው ፍሬንድሺፕ ኢንተርናሽናል ሆቴል በሚዘጋጀው ልዩ የምረቃ ሥነሥርዓት ላይ አንጋፋዎቹ አርቲስት አበበ ባልቻ ፣ አርቲስት ተፈሪ አለሙ ፣ ወግ አዋቂው በሃይሉ ገብረመድህን ፣ አርቲስት ጌትነት እንየውን ጨምሮ ሌሎችም የኪነጥበብ ባለሞያዎች ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል።

የምረቃ ሥነሥርዓቱ መደበኛ የመግቢያ ዋጋ 300 ብር ሲሆን ከነጻ ኮክቴል እራት ጋር ለVlP 1000 ብር መሆኑ ታውቋል፡፡

በዕለቱ ከሚመረቁት መጻህፍት መካከል አንዱ የሆነው ነገም ሌላ ቀን ነው፣ ዝነኛው የአሜሪካ ክላሲክ መጻሐፍ Gone With The Wind ትርጉም ሁለተኛ ክፍል መጽሐፍ ሲሆን ገጣሚ ነቢይ መኮንን በደርግ ዘመን በእስር ላይ እንዳለ በሲጋራ መጠቅለያ ወረቀቶች ላይ በድብቅ የተረጎመው እንደሆነ ይታወቃል፡፡

መጽሐፍቶቹን በጠይም መጻሕፍት /አራት ኪሎ ቅድስት ሥላሴ ሕንፃ አንደኛ ፎቅ /ላይ ማግኘት ይቻላል ተብሏል፡፡

የምረቃ ሥነሥርዓቱን አስመልክቶ ገጣሚ ነቢይ መኮንንና የፕሮግራሙ አዘጋጆች ዛሬ ከሰዓት በኋላ መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከ20 ዓመታት በላይ የዘለቀችውን ሳምንታዊ አዲስ አድማስ ጋዜጣ ከመሰረቱት አንዱ የሆነውና አሁንም በዋና አዘጋጅነት እየሰራ የሚገኘው ነቢይ መኮንን፣ ከዚህ ቀደም ሁለት የግጥም መድበሎችን ያሳተመ ሲሆን ናትናኤል ጠቢቡ የተሰኘውን ጨምሮ ሌሎች ተውኔቶችንም ለመድረክ ማብቃቱ ይታወሳል፡፡
826 views07:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 12:28:18
የጎሕ ቤቶች ባንክ መስራችና የቦርድ አባል የሆኑት ዶ/ር ኢ/ር ውብሸት ዠቅአለ ለ10ኛው የበጎ ሰው ሽልማት በመታጨታቸው የባንኩ የቦርድና የሥራ አመራር አባላት እንዲሁም መላው ሰራተኞች የተሰማንን ልባዊ ደስታና ክብር እየገለፅን መልካም ዕድልን እንመኝልዎታለን!

ጎሕ ቤቶች ባንክ
822 viewsedited  09:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 17:14:15

1.0K views14:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 23:44:08
ለውድ ደንበኞቻችን
የእጣ ማውጣት መርሃግብሩ ወደ መስከረም 10 የተዘዋወረ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡
በአካል መምጣት ለምትፈልጉ አድራሻችን: ከአትላስ ወደ ዉሃ ልማት በሚወስደዉ መንገድ 400 ሜትር ገባ ብሎ ዮሊ ሆቴል ፊት ለፊት እና ስቴድየም የሀ ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ በመምጣት መረጃ ማግኘት እንዲሀ‍ኡም መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ
0948059608 / 0948059610
0948059611 / 0948059612
0948059613 / 0948059614
0948059617 / 0948059618
በተጨማሪ በቴሌግራም አድራሻችን https://t.me/gojobh ወይም @Gmarktradingplc ሊያገኙን ይችላሉ።
1.2K views20:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 23:25:39
1.1K views20:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 23:20:14
ፈረስ ትራንስፖርት የ365,974 ብር የገንዘብ
ድጋፍ ለልብ ሕሙማን አበርክቷል!

የገንዘብ ድጋፉ የፈረስ ቤተሰቦች አገልግሎቱን በመጠቀም ያሰባሰቡትን የፈረስ ማይልስ ለአንድ ዓመት ያህል መተግበሪያውን በመጠቀም የለገሱት ሲሆን፣ ይህንንም ድጋፍ ፈረስ ትራንስፖርት በዛሬው ዕለት በራዲሰን ብሉ ሆቴል ባዘጋጀው የማስረከቢያ መርሀግብር ላይ የድርጅቱ የበጎ ፈቃድ አምባሳደር አርቲስት መሠረት መብራቴ እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት አበርክቷል።
ፈረስ ከልብ ሕሙማን በተጨማሪ ለሌሎች የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ግለሰቦችም የገንዘብ ድጋፉን ያበረከተ ሲሆን በአጠቃላይ ከአንድ ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል።
የፈረስ ትራንስፖርት መተግበሪያን በመጠቀም ይህንን ድጋፍ ላበረከቱ ልባም ኢትዮጵያውያን ብሎም ይህንን አማራጭ በማዘጋጀት የበጎ አድራጎቶች አጋር መሆኑን ያስመሰከረውን ፈረስ ትራንስፖርት የልብ ሕሙማን ማዕከል አመስግኗል፡፡
1.0K views20:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 19:20:43 የነገር ጥግ
አንድ ጊዜ ሽማግሌ ባህታዊና ወጣት ባህታዊ አብረው ይጓዛሉ፡፡ አንድ የወንዝ ዳርቻ ጋ ሲደርሱ ድልድዩ ተሰብሮ ያገኙታል፡፡ በወንዙ ውስጥ ማቋረጥ ነበረባቸው - ባህታውያኑ፡፡
አንዲት ቆንጆ ኮረዳ፣ በድልድዩ መፍረስ ምክንያት ወንዙን ማቋረጥ ተቸግራ ቆማለች፡፡ ሽማግሌው ባህታዊ ቆንጆዋን ኮረዳ በጀርባቸው አዝለው ያሻግሯት ዘንድ ጠየቋት፡፡ ኮረዳዋ ፈቃደኛ ሆነች፡፡
ወጣቱ ባህታዊ በአዛውንቱ ተግባር በእጅጉ ደንግጦ፣ ከሴቶች ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንደማይፈቀድ እያወቁ እንዴት ሴት ይሸከማሉ? ብሎ አሰበ፡፡ ነገር ግን ሃሳቡን ለማንም ትንፍሽ አላለም፡፡
ሽማግሌው ባህታዊ ኮረዳይቱን ተሸክመው ወንዙን ሲያቋርጡ፣ ወጣቱ ደስተኛ ባይሆንም፣ ይከተላቸው ነበር፡፡ ወንዙን ካቋረጡ በኋላም፣ አዛውንቱ ኮረዳይቱን አወረዷትና፣ ሁሉም መንገዳቸውን ቀጠሉ፡፡
ሁለቱ ባህታውያን ብዙ ማይል ርቀት አብረው ሲጓዙ፣ ወጣቱ በሽማግሌው ባህታዊ ተግባር ብክን ብሎ ነበር፡፡ በጭንቅላቱም ሲወነጅላቸው ቆይቷል፡፡ ውስጥ ውስጡን ሲብሰለሰል በመቆየቱ ንዴቱ ፍሟል፡፡
ሆኖም ግን ለብዙ ሰዓት በዝምታ አሳለፈ፡፡ በመጨረሻ ግን ሁሉም ነገር ከቁጥጥሩ በላይ ሆነበት፡፡ እናም በንዴት አዛውንቱን ተናገራቸው፡-
እንዴት ራስዎትን የበቃሁ ባህታዊ ነኝ ብለው ይናገራሉ? ባህታውያን ሴት አጠገብ ድርሽ ማለት እንደሌለባቸው ሲያስተምሩ ቆይተው፣ ያውም ቆንጆ ኮረዳ ተሸክመው ወንዝ ሲሻገሩ በዓይኔ በብሌኑ አየሁኝ፡፡ ያስተማሩኝ ሁሉ የይምሰል ነው ማለት ነው! አለ ወጣቱ፡፡
ሽማግሌው ባህታዊ በነገሩ ግርም ብሏቸው፤
ቆንጆይቷን ኮረዳ ከወንዙ ዳርቻ ላይ ካወረድኳት ብዙ ሰዓት ቆየሁኝ፡፡ አንተ ግን እዚህ ድረስ ተሸክመሀት መጣህ! አሉት፡፡
***

ነገር የማብረድና የትዕግስት ጽናቱን ይስጠን!!
1.1K views16:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ