Get Mystery Box with random crypto!

ማስጠንቀቅያ         ማሳሰብያ በቴሌግራም ትምህርት ላስተምራችሁ 1000 ብር ክፈሉ የሚ | መርጌታ የወሴፍ የባህል መዳሀኒት ቀማሚና ህክምና

ማስጠንቀቅያ
        ማሳሰብያ

በቴሌግራም ትምህርት ላስተምራችሁ 1000 ብር ክፈሉ የሚል መልእክት ከኔ ዘንዳ እንዳልሆነ ይታወቅልኝ።

እኔ የጥበብ ትምህርት ላስተምራችሁ ተመዝገቡ ብርም ክፈሉ የሚል ቃል እስካሁን ከአፌ አልወጣም።.

እንደዛ ያላችሁ ሰውም ካለ ውሸት ነው።

ምክንያቱም ውሸት ስለሆነ። ከተለያዩ ቻናሎች በመቆራረጥ እንዲሁም ኮፒ በማድረግ እየለጠፈ የአጋንንት ምስሐብ ላስተምራችሁ ወዘተ...የሚል ቀልደኛ ሰው መሆኑን እያያችሁ እንዴትስ ልታምኑት ቻላችሁ?ዝም ማለት ስለከበደኝ ነው።የተለያዩ ፌክ members በማጠራቀም ሰዎችን እንዲያምኑት የማድረግ ስራ በመስራት ብጥስጣሽ ብር የሚሰበስብ ጥበበኛ መሳይ ሰው በመበራከቱ መርምራችሁ እውነታውን ተረዱ።
ይህ ጥበብ የማስተማር የውሸት አጀንዳ ከአምስት በላይ የቴሌግራም ቻናል ያላቸው ሰዎች አሉ።እነሱንም መርምሯቸው።
እኔም ጋ ስህተት ካለ አርሙኝ ክፍተቴንም ድፈኑ ትክክለኛ ጥበብንም ለመማር ውሸተኛ ጥበበኛንም ለማጋለጥ ሞክሩ።

ከተታለላችሁም የእናንተው ጥፋት ነው። መርምሩ፣ አስተውሉ፣ አድራሻ ጠይቁ፣ ሕጋዊ እና ከማጭበርበር ውጭ እንደሆነም ተረዱ።
ብዙ ሰዎች በውስጥ መስመር እንደተታለሉ እንዲሁም መፍትሔ ፈልገው ብራቸውን የተበሉ ሰዎች ቤት ይቁጠራቸው።

እንዴት በሰው ጤና ይቀለዳል ምን ዓይነት አእምሮስ ቢኖራችሁ ነው።
የእውነት ይህን ደካማ ስራ የማጭበርበር ስራ የሚሰሩት ደግሞ ፣ጭራሽኑ የእውቀቱ ልምድ የሌላቸው፣ እንዲሁም በአፈ ታሪክ ስለ ጥበብ ሲሰሙ የኖሩ፣በቴሌግራም የሀሰት ንገድ ጀመሩ፣
ይቺ የጀመርኳት ጥበብን የማስረዳት እንዲሁም ንቃት የመፍጠር ዘዴ ቀዳዳ በመጠቀም የንፁሐን እንባ ማፍሰሳቸው የመቅሰፍቱ ተቋዳሽ ናቸው።

ተመለሱ የማጭበርበር ስራ በጥበብ ስም የምትነግዱ ሰዎች አይበጃችሁም። የሰዎች ልቅሶ እና ሀዘን ያጠቃችኃል። ሰው ቀልብ እንዳትገቡ!ባስ ሲል ደግሞ በሕግም የምትፈለጉ ይሆናል። አይቀርም እውነትን ብትይዙ ግን ሌላው ቢቀር የአእምሮ ዕረፍት ይኖራችኃል።

ተጠንቀቁ
እውነትን እናስቀድም።
ሀሰትና ማጭበርበርን እንጠየፍ።

መርጌታ የወሴፍ ነኚ።

የቀደምት አባቶቻችንን እውቀት እና ጥበብ ሳይበረዝ እንደወረደ ይቀርባል። የአያቶቻችን የእጽዋት ጥበብ፣ በህይወትዎ ላይ ለሚያጋጥሙ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው፣ ክፉ መናፍስትን እንዴት ማራቅ እንደምንችል፣ የብራና መጽሐፍት እና ጥቅማቸው በዚ ይዳሰሳሉ።

0924609673