Get Mystery Box with random crypto!

እስጢፋኖስ ፀጋና ሀይልን ተሞልቶ ድንቅን ሰራ በህዝቡ መሀል ተገኝቶ ፃፎች ቀርበው እንዲፈርዱበት ያ | አዳዲስ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙራት

እስጢፋኖስ ፀጋና ሀይልን ተሞልቶ
ድንቅን ሰራ በህዝቡ መሀል ተገኝቶ
ፃፎች ቀርበው እንዲፈርዱበት ያዙት
(እንደ መልአክ ፊቱ እያበራ አዩት)፪

አዝ....

እውነት በተናገረ
ቃሉን በመሰከረ
የሚቃወሙት በዙ
ሊወግሩት ድንጋይ ያዙ

አዝ....

ህገ ኦሪት አልሻረም
ታሪክ አላዛነፈም
በሀሰት ተመስክሮ
ሊገደል ሄደ ታስሮ

አዝ....
በ አይሁድ መጠላቱ
ወደ ሞት መገፋቱ
ይሄ ነበር አላማው
የ ሰማይ ጌታን አየው

አዝ...

ቀዳሜ ሰማዕት ነው
መከራ ያልበገረው
የ ናዝሬቱ እየሱስ
የ ሸለመው ሁለቱን ልብስ

እስጢፋኖስ ፀጋና ሀይልን ተሞልቶ
ድንቅን ሰራ በህዝቡ መሀል ተገኝቶ
ፃፎች ቀርበው እንዲፈርዱበት ያዙት
(እንደ መልአክ ፊቱ እያበራ አዩት)፪