Get Mystery Box with random crypto!

✞እያለፈ ነው ዘመኔ✞ እያለፈ ነው ዘመኔ ትእዛዙን ሳልፈጽም ወየው ለእኔ(፪) በጠራኝ ጊዜ ምን | አዳዲስ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙራት

✞እያለፈ ነው ዘመኔ✞

እያለፈ ነው ዘመኔ ትእዛዙን ሳልፈጽም
ወየው ለእኔ(፪)
በጠራኝ ጊዜ ምን እላለሁ
ና ብሎ ወደእኔ(፪)

በወጣትነቴ ሳልሠራ እያየሁ አለፈኝ
ብዙ አዝመራ(፪)
ከእንግዲህ በመሥራት ጌታ ሆይ
ልኑር ከአንተ ጋራ(፪)

የማስብበት በየለእቱ ንጹሕ ልብን
ስጠኝ አቤቱ(፪)
ከትእዛዝህ ውጪ በመሆን
እዳልቀር በከንቱ(፪)

እንደየሥራው ለመስጠት
በግርማ መንግሥቱ ሲመጣ(፪)
ማን ይሆን የሚቆም ከፊቱ
ፊተናን የወጣ(፪)

እንዳያስቷችሁ ተጠንቀቁ
እየተማራችሁ ከቃሉ(፪)
ይመጣሉና በእርሱ ስም
አምላክ ነን የሚሉ(፪)

ትእግሥትን በመያዝ ሁላችሁ
እስከመጨረሻው ጠንክሩ(፪)
ያን ጊዜ ይሆናል በእርሱ ዘንድ
የማዳን ተግባሩ(፪)

"በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ"
መክ፲፪፥፩
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
mazemur_getemoche
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯