Get Mystery Box with random crypto!

#አማኑኤል_ተመስገን አማን በአማን(፬) አማኑኤል ተመስገን  ለዚህ ፍቅርህ ምን ልክፈልህ (፪) | አዳዲስ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙራት

#አማኑኤል_ተመስገን

አማን በአማን(፬)
አማኑኤል ተመስገን 
ለዚህ ፍቅርህ ምን ልክፈልህ (፪)

ድብቁን ኃጢአት አንተ ብትገልጸው
ይቅር ብለኸኝ ባትሸፋፍነው
እንደ ሰው በቀል ቢኖር ጌታ
ለኔ ኃጢአትስ የለውም ቦታ
#አዝ
በየደቂቃው ኃጢአት ስሰራ
ስሰርቅ ስበድል አንተን ሳልፈራ
አንተ ግን ፊትህ ምንም ቢቀየም
በቁጣህ በትር አልገረፍከኝም
#አዝ
ምህረትህን ልከህ አድነኝ ዛሬ
ታክቶኛልና በኃጢአት መኖሬ
አለም በኃጢአት እየሳበችኝ
በጽድቅ ደስታ መኖር አቃተኝ
#አዝ
የኃጢአት ጉዞ ጣፋጭ ቢመስልም
ውጤቱ መሮ ፍጹም አይጥምም
እንደ በደሌ ስላልከፈልከኝ
ተመስገን እንጂ ሌላ ምን አለኝ

✥┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈✥
✣ ✢ ✥┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈✥