Get Mystery Box with random crypto!

✞ዕቀብ ሕዝባ✞ ፍቅር ጠፍቶ ከትውልዱ በጸብ ሲኖር አንዱ ከአንዱ ተጨንቃለች ኢትዮጲያ ስትል ስማት | አዳዲስ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙራት

✞ዕቀብ ሕዝባ✞

ፍቅር ጠፍቶ ከትውልዱ
በጸብ ሲኖር አንዱ ከአንዱ
ተጨንቃለች ኢትዮጲያ
ስትል ስማት ሃሌ ሉያ
ዕቀብ ሕዝባ ወሃይማኖታ
ለሃገሪትነ ኢትዮጲያ
እግዚኦ መሃረነ ክርስቶስ(፪)
ጠዋት ማታ በኪዳኑ
ስትጠራህ በሊጦኑ
የውዳሴ የማኅሌት
ልመናዋን አምላክን ስማት
ዕቀብ ሕዝባ ወሠራዊታ
ለሃገሪትነ ኢትዮጲያ
እግዚኦ መሃረነ ክርስቶስ(፪)
የቅዱሳን መኖሪያ ደብር
ብዙ ኪዳን ያላት አገር
እጇን ለአንተ ስትዘረጋ
አታሳጣት ክብር ጸጋ
ዕቀብ ሕዝባ ወሃይማኖታ
ለሃገሪትነ ኢትዮጲያ
እግዚኦ መሃረነ ክርስቶስ(፪)
አትተወን አትናቀን
በይቅርታህ ተመልከተን
ጌታ ሆይ እይ ግፋችንን
ስለ ድንግል ተለመነን
ዕቀብ ሕዝባ ወሠራዊታ
ለሃገሪትነ ኢትዮጲያ
እግዚኦ መሃረነ ክርስቶስ(፪)

መዝሙር
ፋሲካ መኮንን