Get Mystery Box with random crypto!

✞ላሓ ማርያም✞ ላሓ ማርያም ላሓ ማርያም ላሓ ማርያም (የማርያም ለቅሶ) ወዮልኝ ይህን ክፉ | አዳዲስ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙራት

✞ላሓ ማርያም✞

ላሓ ማርያም ላሓ ማርያም ላሓ ማርያም
(የማርያም ለቅሶ)

ወዮልኝ ይህን ክፉ ሥራ በአንተ ላይ ሲሠሩ
የሚያዩ ዓይኖች ምን ዓይኖች ናቸው
ወዮልኝ ይህን ክፉ ሥራ በአንተ ላይ ሲሠሩ
የሚያዩ ዓይኖች ምን ዓይኖች ናቸው
እያለች በልቧ አዝና ስታለቅስ
አንተ ግን ከበጎ በቀር በእነርሱ ክፋትን አላደረግክም

ሐሙሱን ሌሊት እየመራቸው ይሁዳ ስሞ አስያዘው
እየጎሰሙት እየተፉበት ትንቢት ተናገር ብለው
ጲላጦስ ፊት አቆሙት
ፈረዱበት እያሉ ይሙት
አዝ= = = = =
የአለበሱትን ቀይ ልብስ ገፈው ግምጃ አስታጠቁት
እጅ እና እግሮቹን በእንጨት መስቀል ላይ አሠሩት
አጥንቶቹ ሁሉ ተቆጠሩ
እጅ እና እግሩ ተቸነከሩ
አዝ= = = = =
የአቀዳጁትን የእሾህ አክሊሉ ራሱን ወጋው ቆሠለ
ደም በትከሻው ሲንጠፈጠፍ እናቱ እያየች እንዲሁ ዋለ
በጅራፉም በግርፋቱም
ሠውነቱ ሆነ ደም በደም

መዝሙር
ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮

╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯