Get Mystery Box with random crypto!

የሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ AMN-ታህሳስ 07/2016 ዓ.ም በ17ኛው ሳምን | AMN-Addis Media Network

የሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ

AMN-ታህሳስ 07/2016 ዓ.ም

በ17ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተጠባቂ የነበረው እና ሊቨርፑልን ከማንቸስተር ዩናይትድን ያገናኘው የሳምንቱ ጨዋታ ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቅቋል።

አንፊልድ ላይ ማንቸስተር ዩናይትድን ያስተናገደው ሊቨርፑል ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል።

ውጤቱን ተከትሎ ሊቨርፑል ባደረጋቸው 17 ጨዋታዎች 38 ነጥብ በመሰብሰብ በሊጉ 2ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፤ 28 ነጥብ የሰበሰበው ማንቸስተር ዩናይትድ 7ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን አርሰናል በ39 ነጥብ መምራት ችሏል።