Get Mystery Box with random crypto!

የክቡር ዶክተር አርቲስት ዓሊ ቢራ መታሰቢያ ሐውልት በአዲስ አበባ ተመረቀ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ | AMN-Addis Media Network

የክቡር ዶክተር አርቲስት ዓሊ ቢራ መታሰቢያ ሐውልት በአዲስ አበባ ተመረቀ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኤ ኤም ኤን) ሰኔ 18/2015 ዓ.ም

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ሀይሌ ጋርመንት ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ወደ ገላን በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው አደባባይ ሀውልቱ የተገነባ ሲሆን አደባባዩም በስሙ ተሰይሟል።

ሀውልቱን የመረቁት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ አርቲስት ዓሊ ቢራ በስራዎቹ ስለአንድነት፣ አብሮነት፣ ፍቅር፣ ሰላምና ፍትህ በማቀንቀን ዘመን የሚሻገር አሻራ ትቶ አልፏል ብለዋል፡፡

የመታሰቢያ ሃውልቱ ይህን የአርቲስቱን በጎ ስራ የሚዘክር መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡

ሀውልቱ አሊ ቢራ ስለ አንድነት እና የሀገር ፍቅር እና ክብር በሙዚቃዎቹ ያስተላለፈውን ትምህርት ያሁኑ ትውልድ እንዲተገብረው ማስታወሻ የሚሆን ነውም ብለዋል።

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የፌደራል እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች የአሊ ቢራ ቤተሰቦች የሞያ አጋሮች እና አድናቂዎች ተገኝተዋል።

ከምረቃ ሥነ ሥርዓቱ በኋላም የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ተከናውኗል።

በሰብስቤ ባዩ