Get Mystery Box with random crypto!

*ጠቋሚዋ ኮከብ* “እነሆም፥ በምሥራቅ ያዩት ኮከብ ሕፃኑ ባለበት ላይ መጥቶ እስኪቆም ድረስ ይመ | ACTS REVIVAL

*ጠቋሚዋ ኮከብ*

“እነሆም፥ በምሥራቅ ያዩት ኮከብ ሕፃኑ ባለበት ላይ መጥቶ እስኪቆም ድረስ ይመራቸው ነበር።”
— ማቴዎስ 2፥9
√እዚህ ክፍል ላይ የዚህ ኮከብ ዋነኛ ድርሻ እና የእርሱ ጠቋሚነት መጨረሻ ግቡ ኢየሱስ ያለበትን ስፍራ መጠቆም ነበር:: ኮከቡ ብዙ ተጉዞ ክርስቶስን ሲያገኝ ቆመ:: ክርስቶስ የመላው ብሉይኪዳን ፍለጋ ማብቂያ ነው:: የእርካታም ጥጉ ነው:: ኮከብ በጨለማ ብርሃንን ከሚሰጡ ብርሃናት መካከል አንዱ ነው:: መፅሐፍ ቅዱስ “እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም።” ማቴዎስ 5፥14 እንደሚል ለዚህች አለም ደግሞ ኢየሱስን የምናበራው የመዳን ብርሃን የበራልን ቅዱሳን ነን :: እኛም ቅዱሳን ልክ እነደዚህች ጠቋሚ ኮከብ ለጨለማው አለም ብርሃን የሆነውን ኢየሱስን ሁለንተናዊ በሆነ ኑሮ ለማብራትና ለማሳየት ተጠርተናል:: ኮከቡ ሰብአሰገሉን ኢየሱስ እስካለበት ቦታ እንደመራቸው እና ኢየሱስ ያለበት ቦታ እንደቆመ እኛም ከኢየሱስ ውጪ ላንጠቁም፣ ከኢየሱስ ውጪ ርዕስ ላይኖረን፣ ከኢየሱስ ውጪ ላናሳይ፣ከኢየሱስ ውጪ ላንኖር ይልቁን ሰዎች ሁሉ ይህ የመዳን ብርሃን የሆነው ኢየሱስ ጋር እንዲደርሱ የህይወትን መንገድ ልንጠቁማቸው ይገባናል። ምክንያቱም “በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው።”
— ኤፌሶን 1፥10
                         
                         Rahelwendwesen

@semayawitel
@semayawitel
@semayawitel
join$share