Get Mystery Box with random crypto!

#Repost በቀጣይ ዩኒቨርሲቲ የምትገቡ የ ማህበራዊ ሳይንስ(social science) ተማሪዎ | Ac

#Repost

በቀጣይ ዩኒቨርሲቲ የምትገቡ የ ማህበራዊ ሳይንስ(social science) ተማሪዎች የ መጀመሪያው ሴሚስተር ላይ ስለምትወስዷቸው ኮርሶች መረጃ።

በ Daniel Th and Daniel Sh ተፅፎ በ Concise English(@Aconcise) ተዘጋጅቶ የቀረበ።

የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የመጀመሪያ አመት የመጀመሪያው ሴሚስተር ላይ የምትወስዷቸው ኮርሶች

Communicative English Skill I

Anthropology

Economics

Geography

Maths(Social)

Civics and Moral Education

Global Trends

Physical Fitness

አሁን ደግሞ ስለ እያንዳንዱ ኮርስ መጠነኛ የሆነ ገለፃ ወይም ጅንጀና እናድርግ።

Communicative English Skill I

ይህ ኮርስ የብዙ ተማሪዎችን ውጤት የሚያነሳ ነው እንግሊዝኛ ሞካሪ ከሆናችሁ። ነገር ግን የአምና ተማሪዎች ውጤታቸውን ዝቅ አድርጎባቸዋል። በዚህ ኮርስ በዋናነት የምትማሩት

Reading skill ( ልክ Entrance እንደተፈተናችሁ አይነት የ passage ጥያቄ ትፈተናላችሁ።)

Grammar( Active and pasive voice , conditional sentence, Modal Verbs etc ትማራላችሁ።) mid exam, final exam እና CoC exam ላይ passive and active voice እና conditional sentence ብዙ ጥያቄ ስለሚወጡ ትኩረት ሰጥታችሁ በማንበብ ተረዱት።)

Vocabulary - ከ አውዱ ተነስታችሁ የቃላቶችን ተመሳሳይ ና ተቃራኒ ትርጉም መፈለግ ነው። ብዙ ተማሪዎች ለመስራት ይቸገራሉ ፤ ፈተና ላይ በብዛት ይወጣል። ኮርሱ A+ tutorial class ላይ ግልፅ በሆነ መንገድ ስለሚሰጥ ተመዝግባችሁ ተማሩ።

Economics

የ Economics ትምህርት ፈተናዎች conceptual ናቸው። ስለዚህ Economics ን ስታነቡ አትሸምድዱ። በቻላችሁት መጠን ሳይንሱን ለመረዳት ሞክሩ ፡ ለዚህ ኮርስ እጅግ በጣም ጠቃሚ የሆነ ቲቶርያል ልጠቁማችሁ። በርግጠኝነት A+ ነው የምታመጡት። Fortino Academy ይባላል። በ አማርኛ እያብራራ ያስረዳል። እጅግ በጣም ሲበዛ ግልፅ ና ለፈተና የሚያዘጋጁ ትምህርቶች ይቀርቡበታል። You tube ላይ ገብታችሁ ተከታተሉት።

Geography

በዚህ ኮርስ የኢትዮጵያን ና የምስራቅ አፍሪካን ገፅታ ትማራላችሁ። ይህ ትምህርት አንዴ ተነቦ የሚተው አደለም በተፈጥሮው ይተናል ብል ይቀላኛል ስለዚህ ብትችሉ ስታነቡ Note ያዙ ቀጣይ ስትደግሙት Note ብቻ ማንበብ ነው የሚጠበቅባቹ ከ module ውጪ ፈተና አይወጣም PPT እንደ Apetizer ውሰዱ እንዳልኳቹ ስለሚረሳ ቶሎ ቶሎ ሳይበዛ ከልሱት አንዳንዴ Module ስታነቡት ደስ ላይል ሰለሚችል Note እየያዛቹ ዋና ዋና ነጥቡን አንብቡ :: አደራ ይህን ኮርስ እንዳትንቁት ከባድ የሚባል ና ብዙ ፍሬሾችን የሚያስቸግር ኮርስ ነው።

Maths (Social)

ከ መጠነኛ ለውጥ ( modification) ውጭ 11 እና 12 የተማራችሁት ነው። በይበልጥ ፈተና ሲውጣ Basic ነገር ነው የሚያወጡት Module ማንበብ ለዚ ግዜ በጣም ወሳኝ ነው Module በደምብ ሳታነቡ Reference እንዳገልጡ አደራ Defintion , Properties , Exercises ..... module ላይ ያለውን በደምብ ያዙ የሚሰጣቹ Course outline ላይ ያለውንም ነጥብ በደምብ ተመልከቱ ምን ላይ ማተኮር እንዳለባቹ ይረዳቹሀል::

Civics and Moral Education

ዩኒቨርሲቲ ላይ የሚሰጠው የ Civics and Moral Education ኮርስ ፤ Highschool ና pre paratory ከሚሰጠው ኮርስ ጋ በፍፁም አይገናኝም። ግቢ ላይ ያለው የ Civics ኮርስ ለተማሪዎች የሚያስቸግር ከባድ ኮርስ ነው። ይህ ኮርስ በተለይ ስለ Ethics ና Morality ምንነት በስፋት ያትታል። ከ Ethics ጋ የተያያዙ የ ሞራል ፍልስፍናዎችን ና ንድፈሀሳቦችን በስፋት ይዳስሳል። በተለይ ስለ Normative ና non-normative Ethics, Teleological Ethics, Ethical Egoism and psychological Egoism, Altruism, Utilitarianism, Quality over quantity Ethics, Quantity over quality Ethics, Act and Rule Utilitarianism, Virtue Ethics, Meta Ethics በጣም በስፋት ይዳስሳል። እንዲሁም ደግሞ ስለ state, government ና citizenship ምንነት በስፋት ያጠናል በተለይ ስለ pluralist state, capitalist state, Leviathan state, Patriarchal state, minimal state, developmental state,social-democratic state, collectivized state, totalitarian state, religious state ና ስለ Citizenship በተጨማሪም ስለ Constitution, Democracy ና Human Right በጣም በስፋት ያጠናል ። A+ Tutorial Class ላይ በጣም ደስ በሚል ለመረዳት ምቹ ና ግልፅ በሆነ ሁኔታ ስለሚሰጥ ተመዝግባችሁ ተማሩ።

Global Trends

ይህ ኮርስ ከስሙ እንደምትረዱት ፤ ፖለቲካዊ ቴክኖሎጂያዊ ና ኢኮኖሚያው አለም አቀፍ ጉዳዮችን ይዳስሳል። በተለይ አለም አቀፍ ግንኙነት(International relation) ሳይንሳዊ ምንነትን ይዳስሳል። ስለ አቀፍ ግንኙነት ንድፈ ሀሳቦችን ይዳስሳል በተለይ ስለ Liberalism, Realism , Marxism ና Constructivism የተባሉ የፖለቲካ ርዕዮቶችን ይዳስሳል። እንዲሁም ስለ Foreign Policy, National interest ና Globalization በሰፊው ይናገራል። ይህ ኮርስ ለተማሪዎች የሚከብድ ኮርስ ነው። A+ Tutorial Class ላይ በጣም ደስ በሚል ለመረዳት ምቹ ና ግልፅ በሆነ ሁኔታ ስለሚሰጥ ተመዝግባችሁ ተማሩ።

Anthropology

ለ theory ተማሪ ይህ ኮርስ ደስ የሚል ነው። በዋናነት የሚያጠና ስለ ሰው ልጅ አመጣጥ ፤ ስለ culture ፥ Ethinicity ፥ Social Norms ነው። A+ Tutorial Class ላይ በአሪፉ ስለሚሰጥ ተመዝግባችሁ ተማሩ።

Physical Fitness

ይህ ኮርስ ውጤት የለውም። ማለትም A, B+ ,C ምናምን ተብሎ Grade አይሰራለትም። pass or fail ነው የምትባሉት። ኳስ ሜዳ ወጥታችሁ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ነው የምትሰሩት ፡ ስለዚህ የስፖርት ትጥቅ ያስፈልጋችሗል።

በአብዛሀኛው ግቢ የ ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች first semester course እነዚህ ናቸው።

ማስታወሻ - አንዳንድ ኮርሶች ከ ግቢ ግቢ እንደሚለያዩ ግምት ውስጥ አስገቡ

Join and share

https://t.me/FRESH_2015
https://t.me/FRESH_2015