Get Mystery Box with random crypto!

መልዕክት ለዛ ሽልማት አዘጋጆች የተከበራችሁ የኪነጥበብ ቤተሰቦች እንዴት ከረማችሁ አምላክ ፈቅዶ | ዳሰሳ አዲስ-Access Addis

መልዕክት ለዛ ሽልማት አዘጋጆች
የተከበራችሁ የኪነጥበብ ቤተሰቦች እንዴት ከረማችሁ አምላክ ፈቅዶ ዘንድሮ በለዛ የሽልማት ስነ ስርዓት ልንገናኝ ነው። ዘንድሮም ታላላቆችን በስራቸው እናከብራለን።
በዚህ ዓመት የአመቱ ምርጥ አዲስ ድምጻዊ ምድብን ከዚህ ዓመት ሽልማት ጀምሮ በታላቁ የሙዚቃ አቀናባሪ ፣ዜማ ና ግጥም ደራሲ የኤልያስ መልካ መታሰቢያ ሽልማት እንዲሆን ወስነናል። እናም የሽልማቱ ዘርፍ በለዛ ሽልማት ላይ ሲጠራ ፦ የኤልያስ መልካ ሽልማት ፦ የአመቱ ምርጥ አዲስ ድምፃዊ ፦ ተብሎ ይጠራል ማለት ነው። ኤሊያስ መልካ የአገራችንን ምርጥ አዳዲስ ድምፃውያንን በማበቃቱ ሂደት ድርሻው የገዘፈ ነውና ለውሳኔያችን ገዢው ምክንያት ይሄው ነው። የመጀመሪያ አልበማቸውን እሡ ሰርቶላቸው ፈልጎ አግኝቷቸው ቀርጾ አውጥቷቸው የየራሳቸው ሙዚቃዊ ማንነት አላብሶ በስራቸው አንቱ ያስባላቸው ክብሩን ያወቁታልና የሃሳባችን ተጋሪዎች ናቸው ብለን እና ስባለን። እናንተስ የኪነ ጥበብ ቤተሰቦች ? ውሣኔያችንን እንዴት አግኝታችሁት ይሆን ? ለማናቸውም ድምፆችሁን ለምትወዱት የኪነጥበብ ስራና ጥበበኛ www.lezashow.com
በመግባት vote የሚለውን በመጫን ድምፆችሁን ሰጡ የኪነጥበብ ቤተሰብን አበርቱ :: ድምፅ መስጠት ሠኞ መጋቢት 12 ይጀመራል ::
የለዛ ሽልማት