Get Mystery Box with random crypto!

በ1 ቀን ፆም የ2 ዓመት ወንጀል የእዝነቱ ነብይ ነብዩ ሙሐመድﷺ በተከበረው ሓዲ | የሰለፊያ ዳዕዋ በወላይታ

በ1 ቀን ፆም የ2 ዓመት ወንጀል


የእዝነቱ ነብይ ነብዩ ሙሐመድﷺ በተከበረው ሓዲሳቸው እንዲህ ይላሉ፦
 «صيام يوم عرفة، أحتَسِب على الله أن يكفِّر السنة التي قبله والسنة التي بعده»
«የዓረፋ ቀን ፆም አላህ ዘንድ ያለፈው ዓመትና የሚመጣውን ዓመት ወንጀልን እንደ ሚምርልኝ አስባለሁ (እከጅላለሁ)።»

ላ ኢላሃ ኢለላህ
የአንድ ቀን ፆም የሁለት ዓመት ወንጀል ያስምራል

እንደው ምን ዓይነት እድለ ቢስ ሰው ነው ይህንን ፆም የሚያስመልጠው

ሁላችንም እንፁም፤
ሁላችንም ቤተሰቦቻችንን እናስታውስ፤
ሁላችንም ይህንን መልዕክት ወደ ሌሎች ሼር እናድርግ

ተደዋወሉ
ተዋወሱ
ሁላችሁም ፁሙ

እውነቱን ለመናገር በነገው ቀን መፆም እየቻለ የሚበላ ሙስሊም ማየት ከነውርም በላይ ነውር ነው።


ማሳሰቢያ
«የዓረፋ ቀን» ማለት ከዒድ በፊት ያለው የዙል_ሒጃ 9ኛው ቀን ነው። ሐጅ የሚያደርጉ ሰዎች "ዓረፋ" በሚባለው ቦታ ስለ ሚቆሙ ነው "የዓረፋ ቀን" የተባለው

አላህ ይወፍቀን

ሐምዱ ቋንጤ ከፉርቃን ሰማይ ስር

t.me/hamdquante/4545
ـــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــ
አጠቃላይ ፕሮግራሞቻችን በሶሻል ሚዲያ ለመከታተል:-

በ Telegram~Channel
https://t.me/joinchat/PxPlMEUUkI0Q0MIx

በ Facebook~page
https://www.facebook.com/Al.Furqan.Islamic.Studio