Get Mystery Box with random crypto!

ለዶ/ር ሁንዴ አህመድ ልጅ የድጋፍ ጥሪ እንደሚታወቀው ወንድማችን ዶ/ር ሁንዴ አህመድ በጅማ ዩኒ | የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ

ለዶ/ር ሁንዴ አህመድ ልጅ የድጋፍ ጥሪ

እንደሚታወቀው ወንድማችን ዶ/ር ሁንዴ አህመድ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ህክምና ማዕከል የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስት  እና የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር የጅማ ቅርንጫፍ  ፕሬዝዳንት ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል።

ልክ እለተ ዓርብ ጥዋት ነበር ውድ ባለቤቱ ዘጠኝ ወራትን በሆዷ ታቅፋ የከረመችውን ወንድ ልጃቸውን በሰላም በመገላገሏ ደስታቸው ወደር የለሽ ነበር።  ታድያ ይህ ደስታቸው በደቂቃዎች ውስጥ ወደ ትካዜ ተቀየረ። የተወለደው ህፃን ትንፋሽ ያጥረውና መታገል ሲጀምር በተደረገለት ምርመራ በሚያሳዝን ሁኔታ በተፈጥሮ የሚከሰት የልብ ችግር “ Transposition of Great Arteries”  (የታላቅ ደም ወሳጅ ቧንቧዎች ቦታ መቀያየር) እንዳለበት ታወቀ።  ህክምናው ከፍተኛ ወጪ የሚፈልግ በየደረጃው የሚደረግ የልብ ቀዶ ጥገና በመሆኑ በአሁኑ ወቅት ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሪፈር ተደርግዋል። የመጀመሪያው ደረጃ  ቀዶ ጥገና ህክምና በኢትዮጵያ ውስጥ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የልብ ህክምና ማዕከል በመኖሩ እየተጠባበቁ ይገኛሉ። ሁለተኛው ቀዶ ጥገና ደግሞ በውጭ አገር የሚደረግ ይሆናል። ለቀዶ ጥገናው በአጠቃላይ አስራ አንድ ሺህ ዶላር($11000) ወይም አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሺህ ብር(1,100,000 ብር) ያስፈልጋል።
ይህንን ገንዘብ ለማሰባሰብ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል።  ታድያ  ውድ ልጃቸው ታክሞላቸው ድኖ ዳግም ደስታቸውን እንድናይ ሁላችንም በምንችለው አቅም ከጎናቸው እንድንቆም በትህትና እንጠይቃለን።

አካዎንት ቁጥር CBE 1000097223991 ሁንዴ አህመድ ዩያ
ለበለጠ መረጃ፡ ይደውሉልን
0919118817 (ዶ/ር ሁሴን ታሲ) እና 0916183436 (ዶ/ር አብደላ አሊ)
በየቀኑ ያለውን መረጃ ማሳወቁን እንቀጥላለን!

https://t.me/+0dIMrouBGpc3NDE0