Get Mystery Box with random crypto!

የትብብር ጥያቄ 270,000 ብር ብቻ ''እኛ መስማት የተሳናቸው ሙስሊሞች ዙርያ የምንሰራ | የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ

የትብብር ጥያቄ

270,000 ብር ብቻ

''እኛ መስማት የተሳናቸው ሙስሊሞች ዙርያ የምንሰራ ኢማን የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ልማት ድርጅት እንባላለን። ከማህበራት ማደራጃ ፍቃድ ያለን ህጋዊ ተቋም ነን።

ህዳር 19 ላይ አለም አቀፍ የመስማት የተሳናቸው ሙስሊሞች ኮንፈረንስ ጋምቢያ ላይ እንድንሳተፍ የጥሪ ደብዳቤ ተልኮልናለን። ስብሰባው ለመላው ኢትዮጵያዊ ሙስሊም መስማት የተሳናው ይጠቅማል ብለንም እናምናለን። ግን አሁን እኛ የደርሶ መልስ የአየር ጉዞ ቲኬት ለመክፈል አቅሙ የለንም። የምንሄደው 3 ሰዎች ነን።

ለያንዳንዳችን ከ80 እስከ 90ሺህ ብር ወይም ለ3ታችን 270ሺህ ብር ገደማ ይጠበቅብናል። የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት የትብብር ደብዳቤ ፅፎልናል። እባካችሁ በኮንፈረንሱ ላይ እንድንሳተፍ ለአላህ ብላቹ ተባበሩን ይላሉ'' መልዕክታቸው።

ሁላችንም ብንተባበራቸው ቀላል ገንዘብ ናት። መስማት የተሳናቸውን፣ አይነ ስውራንን የመሳሰሉ ወገኖቻችንን በእምነታቸው እንዲጠነክሩ ማገዝ የሁላችንም ግዴታ ነው።

ከታች ባሉ አካውንቶች ድጋፍ በማድረግ እናግዛቸው።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት
1000461347936
IMAN ETHIO DEAF DEVT ORGA (IEDDO)

ሒጅራ ባንክ
1002450020001
IMAN ETHIO DEAF DEVT ORGA (IEDDO)

ዘምዘም ባንክ
0009389910301
IMAN ETHIO DEAF DEVT ORGAN