Get Mystery Box with random crypto!

አስቸኳይ የድጋፍ ጥሪ በሰጋጆች ድርቅ የተመታውን የዱራሜውን ቢላል መስጂድ ሁላችንም ለመታደግ እን | የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ

አስቸኳይ የድጋፍ ጥሪ

በሰጋጆች ድርቅ የተመታውን የዱራሜውን ቢላል መስጂድ ሁላችንም ለመታደግ እንረባረብ

አቡ ዳውድ ኡስማን

መዕክቱን አንብበው ሲጨርሱ ለሌሎችም ሼር ያድርጉት

በደቡብ ክልል በከምባታ ጠምባሮ ዞን በዱራሜ ከተማ በካሻ ቀበሌ አሮጌ ሰፈር የሚገኘው ቢላል መስጂድ አካባቢው የነበሩ ሙስሊሞች እንዲሁም የመስጂዱ ኢማም ሚስታቸው እና ልጃቸው ሳይቀር ከፍረው የመስጁዱ ሙዓዚን እና ኢማም የሆኑት ሼይኽ መሐመድ ኑር ብቻቸውን በመስጂዱ እየሰገዱ እንደሚገኙ መገለፁ ይታወሳል::

በዚህ ትልቅ መስጂድ ውስጥ ብቻቸውን አዛን እያወጡ ብቻቸውን ኢቃም ብለው እንደሚሰግዱ መገለፁን ተከትሎ ከፍተኛ ቁጭት እና ሀዘን በሁላችንም ላይ ተፈጥሯል::

መስጁዱ በእድሳት እጥረት በመጎዳቱ ዝናብም እያፈሰሰ እንደሚገኝ እንዲሁም ሌሎች እድሳቶችም እንደሚያስፈልገው ተገልፆ ነበር::

የአካባቢውን ሙስሊሙ ማህበረሰብ ወደ ዲናቸው እንዲመለሱ፣ ባዶ የሆነው መስጂድም በጀምዓ እንዲሞላ፣ የከፈሩትንም ለመመለስ ህዝበ ሙስሊሙ በአንድነት ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቦ ነበር::

ይህን አሳሳቢ ጉዳይ ቀድሞ መረጃው የደረሳቸው በደቡብ ክልል የአክፍሮት ሃይላትን የኩፍር ዘመቻ ለመመከት መሬት ላይ የወረዱ በርካታ ፕሬጀክቶችን፣ መስጂዶችን እና መድረሳዎችን እያሰሩ የሚገኙት ተወዳጁ ኡስታዛችን ኡስታዝ ሷዲቅ መሐመድ(አቡ ሐይደር) ይህንንም የዱራሜ መስጂድ ጉዳይ መፍትሄ እንዲያገኝ እየለፉ ይገኛሉ::

በዚህም መሰረት ይህን መስጂድ ለመታደግ እና የአክፍሮት ሃይላትን እንቅስቃሴ በመመከት የአካባቢውን ህዝበ ሙስሊም ወደ ዲኑ ለመመለስ ይቻል ዘንድ ሁሉም ህዝበ ሙስሊም ያቅሙን ያህል ድጋፍ የሚያደርግበት ሁኔታ ተመቻችቷል::

በኡስታዝ ሷዲቅ መሐመድ (አቡ ሃይደር ) አስተባባሪነት
በዱራሜ ከተማ በካሻ ቀበሌ አሮጌ ሰፈር የሚገኘው በዚሁ የቢላል መስጂድን ማዕከል የሚያደርግ እንቅስቃሴ ተጀምሯል::

በቀዳሚነት ለመስጂዱ ቋሚ ኡስታዝ መቅጠር እንዲሁም መስጂዱ በሚገኝበት በዱራሜ ከተማ በዱራሜ ዩኒቨርሲቲ ለሚገኙ የዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች በዚህ መስጁድ ላይ ታላቅ የዳዕዋ ኮንፍረንስ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል::

ይህ ኮንፍረንስ ከነሐሴ 13-15/2014 ለሶስት ቀናት ኢማሙ ብቻቸውን ሲሰግዱበት በነበረው ቢላል መስጂድ የሚሰጥ ይሆናል::

ይህ ታላቅ ኮንፍረስ ሙስሊም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ማዕከል በማድረግ በአካባቢው ያለውን የኩፍር ዘመቻ ለመመከት እና ሰዎች ወደ ዲናቸው እንዲመለሱ እንዲሁም የመስጁዱን ጀምዓ በማጠናከር ሰፊ ስራዎችን ለመስራት የሚያግዝ ነው::

አሁን ላይ የሁላችንንም ርብርብ እና ድጋፍ የሚሹ ወጪዎች ያሉ ሲሆን እነዚህም:-

1/ ቋሚ የኢማም ደሞዝ ክፍያ
2/ የመሰጂዱ አጥርን ማሳጠር
3/ መስጁዱ የጎደለውን ነገር ሁሉ ማሟላት እና
4/ ለታሰበው ታላቅ የዳዕዋ ኮንፍራንስ ወጪውን መሸፈን ይገኝበታል:

በአሁኑ ሰዓት ብቸኛ የነበሩትን ሼይኽ መሐመድኑርን የሚያግዝ በመስጁዱ በቋሚነት ሊያገልግል የሚችል ብቁ ኡስታዝ የተገኘ ሲሆን በዋናነት ኡስታዙም የመስጁዱ ኢማም በቋሚነት በመሆን እንዲያገለግል፣ ከዐሱር በኋላ ልጆችን እንዲያቀራ እንዲሁም ለካምፓሱ ተማሪዎች ኪታብ እንዲያቀራ ታስቧል::

እነዚህን አስቸኳይ ስራዎች በመስጂዱ ለመስራት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሃገር ውጪ ያላችሁ የበኩላችሁም ድጋፍ ታደርጉ ዘንድ በአላህ ስም እንጠይቃለን::

በተከሰተው ነገር ከንፈር መምጠት እና ማዘን ብቻ ሳይሆን የመፍትሄ ሃሳብ ሲቀርብም ሁላችንም በቻልነው ያህል ማገዝ ይጠበቅብናል:: መፍትሄው በአንድነት መሬት ላይ ሊወርድ የሚችል ስራ መስራት ስንችል ብቻ ነው::

ለተዘረዘሩት ወጪዎች ድጋፍ ማድረግ ለምትፈልጉ ሁሉ በኡስታዝ ሷዲቅ መሐመድ ስም በተከፈተው አካውንት ድጋፍ ማድረግ ትችላላችሁ

1. COMMERCIAL BANK OF ETHIOPIA
1000317507589
SADIK MOHAMMED AHMED

2. ABYSSINIA BANK
83047178
SADIK MOHAMMED AHMED

3. ኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ
1011300008645
SADIK MOHAMMED AHMED

ለበለጠ መረጃ በዚህ ስልክ መደወል ትችላላችሁ
0911103231

ይህን መልዕክት ሁላችንም ሼር በማድረግ እናዳርስ!