Get Mystery Box with random crypto!

ሼይኽ መሐመድ አል አሙዲ 106 በሬዎችን እና 100በግ እና ፍየሎችን ለኡዱሂያ ድጋፍ አደረጉ ኢ | Ustaz abubeker ahmed/ኡስታዝ አቡበከር አህመድ

ሼይኽ መሐመድ አል አሙዲ 106 በሬዎችን እና 100በግ እና ፍየሎችን ለኡዱሂያ ድጋፍ አደረጉ

ኢትዮጵያዊው ባለሃብት ሼይኽ መሐመድ ሁሴን አሊ አል አሙዲ ለመጪው የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል በወሎ በተለያዩ አካባቢዎች በችግር ላይ ላሉ እና በአዲስ አበባ ከተማም ለሚገኙ አቅመ ደካሞች የሚከፋፈል 106 በሬዎችን እና 100 በግ እና ፍየሎችን ለኡዱሂያ ድጋፍ አድርገዋል::

ሼይኽ መሀመድ አል አሙዲ ለኡዲሂያ እንዲሆን በማሰብ ድጋፍ ያደረጓቸው በሬዎች ፣በጎች እና ፍየሎች በወሎ በችግር ላይ ለሚገኙ ወገኖች እና በአዲስ አበባ ለሚገኙ አቅመ ደካሞችም በተለያዩ መስጂዶች እና ተቋማት በኩል እንዲከፋፈል ተደርጓል::

ሼይኽ መሐመድ አላህ መልካም ስራቸውን እንዲቀበላቸው ፣ለሃገራቸውም እንዲያበቃቸው ሁላችንም በዱኣ እናስታውሳቸው!

በዚህ በተከበሩ ቀናቶች እና ለመጪው የአረፋ በአል በችግር ላይ ያሉ ወገኖቻችንን በሰደቃ ልናስታውሳቸው ይገባል::

ለሃገራችንም ሰላም እና መረጋጋት ከልብ ዱኣ ማድረግ አንዘንጋ