Get Mystery Box with random crypto!

Abu Muss'ab - አቡ ሙስዓብ

የቴሌግራም ቻናል አርማ abu_mussaab — Abu Muss'ab - አቡ ሙስዓብ A
የቴሌግራም ቻናል አርማ abu_mussaab — Abu Muss'ab - አቡ ሙስዓብ
የሰርጥ አድራሻ: @abu_mussaab
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 320
የሰርጥ መግለጫ

I am Student Of Comparative Religion.

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-10 00:30:38
"ሳሂህ" የምን ቃል ነው?

የዓረብኛው صحيح የሚለውን ቃል በአማርኛ Transliterate አድርጎ ለመጻፍ ከሆነ እስልምናን በመተቸት መጽሐፍ ጣፈ የተባለው ሰው ዓረብኛ #ማንበብ አይችልም ማለት ነው።
አለመቻሉስ አይገርምም ነበር ግና አረብኛ እችላለሁ፣ እስልምናን የተማርኩ ሙስሊም ነበርኩ፣ አስራ ምናምን አመት እስልምናን አጥንቻለው፣ ቅብርጥሴ የሚል ቀጣጣፊ የክርስትያን ሰባኪ

1. صحيح = ሰሒሕ
2. صاحيح = ሳሒሕ
ሁለቱ ቃላት በአረብኛ ሲነበቡ የተለያዩ መሆናቸውን መረዳት ሳይችል የአረብኛን ቃል ለማንበብ ከእንግሊዝኛ Transliterated "Sahih" መልሶ የእንግሊዝኛውን ቃል ወደ አማርኛ Transliterate አድርጎ ዙርያ ጥምጥም ሄዶ "ሳሒሕ" በማለት የእስልምና አዋቂ መስሎ ግን ደግሞ በእውነታው አረብኛ ማንበብ የማይችል መሆኑን ለረጅም አመታት ስሙ ላይ የለጠፈው ቃል ቅሌቱን የሚገልጥበትን ጀለፍ የመጥሐፍ ጠሐፊ እንዴት አያችሁት?

N.B: صاحيح = ሳሒሕ የሚለው ቃል ወፍ ዘራሽ እንጂ የአረብኛ ቃል አይደለም። አረብኛ አያውቀውም።

@Abu_Mussaab
35 viewsedited  21:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 08:35:22 በዱራሜው መስጅድና በጥቅሉ በገጠሩ የሀገራችን ክፍል ህዝባችንን ከአክፍሮተ ሀይላት በመከላከሉ ረገድ ኡስታዝ አቡ ሐይደር ስለሚሰራቸው ፕሮጀክቶች ከሀሩን ሚዲያ ጋር ያደረገውን ቆይታ ተከታተልኩት። በቆይታው በተለይ በገጠሩ ክፍል መሠራት ስላለባቸው ስራዎች አጽንኦት ሰጥቶ ተናግሯል። በግሉም የከተማ ዳዕዋ ከሞላ ጎደል እንዳቆመና ትኩረቱን ገጠር ላይ እንዳደረገ ገልጿል። የከተማው ሰው ከሶሻል ሚዲያ ጀምሮ እስከ ሳተላይት ቴሌቭዥን ድረስ በቂ አማራጮች ስላሉት ዳዕዋው ያልደረሰበት ቦታ ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚያስፈልግ መክሯል።
..
እውነት ለመናገር ኡስታዝን በቅርበት እንደማወቄ መናገር የምችለው ነገር ባለፉት ሶስት አመታት በገጠሩ የሰራቸው ስራዎች በቃላት የሚገለጹ አለመሆኑን ነው። በተፈጥሮው የሰራውን ማውራትና ያደረገው እንዲነገርለት ስለማይፈልግ እንጅ ለብዙ አካል አርአያ መሆን የሚችሉ ስራዎችን ሰርቷል። ኡስታዝ ዳዕዋየን ገጠር አድርጌያለሁ ሳይሆን ኑሮየን ገጠር አድርጌያለሁ ቢል ይቀለዋል። በስራዎቼ ዙሪያ ብዙ እንድል ስለማያስፈልግ በመጠኑ ይህንን ካልኩ የመጨረሻ መልዕክቴን ግን ላስተላልፍ፦
..
በገጠሩ ስለሚሰሩ የዳዕዋና የአክፍሮተ ሀይላት ስራዎች በሱ በኩል የያዛቸውን ፕሮጀክቶች መደገፍ እጅግ በጣም ብዙ ለውጥ የሚፈጥር እርምጃ ነው። ሁላችንም በአቅማችን ልክ በተለይም ከሰሞኑ በጀመረው በተለያዩ አካባቢዎች ኡስታዞችን የመቅጠር ስራ ላይ እንገዘው፤ አትጠራጠሩ በርካታ ፍሬዎችን ከአመታት በኃላ በአሏህ ﷻ ፍቃድ የምታዩበት ፕሮጀክት ነው።
..
ቪዲዮውን ለማየት




የኡስታዝ አቡ ሐይደር አካውንት፦

1. COMMERCIAL BANK OF ETHIOPIA
1000317507589
SADIK MOHAMMED AHMED

2. ABYSSINIA BANK
83047178
SADIK MOHAMMED AHMED

3. ኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ
1011300008645
SADIK MOHAMMED AHMED

ለበለጠ መረጃ በዚህ ስልክ መደወል ትችላላችሁ
0911103231
___
የሕያ ኢብኑ ኑህ
https://t.me/+A9f1rDgYDRYzYTY0
50 views05:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 21:21:17 ሰውን በእሳት አቃጥሎ የመግደል ህግ

ካሁን ቀደም በዚሁ ቻናላችን 'ኦርቶዶክሳዊ የመግደል ህግና ስርዓት' በሚል ርዕስ ኦርቶዶክስ ጠላት ነው ያለችውን አካል የደገፈና የተባበረ ሰውን መግደል እንደሚገባ መደንገጓን በማስረጃ እንዳስነበብናችሁ ይታወቃል። ለማስታወስ ሊንኩን ተጭነው ማንበብ ይችላሉ። https://t.me/Orthodox_Critic/93

እነሆ አሁን ደግሞ በዛው ተመሳሳይ ቅዱስ የኦርቶዶክስ ህግና ሥርዓት መጽሐፍ ላይ የሰው ልጅ በእሳት ተቃጥሎ መገደል እንደሚገባው የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን የደነገገችውን ህግ አብረን እንመለከታለን።

ኦርቶዶክስ በ14ኛው ክ/ዘመን እንዳዘጋጀችው በሚነገርላት የፍትሐ ነገሥስ መጽሐፏ የጌታቸውን ህይወት ሊያጠፉ የወደዱ ባሮች በእሳት ተቃጥለው መገደል እንዳለባቸው ትደነግጋለች።

"የጌታቸውን ህይወት ሊያጠፉ የሚወዱ ባሮችም ወደ እሳት ይጣሉ።"
ፍትሐ ነገሥት 47፥1704

ጥያቄዎቻችን

1) ጠላትን ሳይሆን ጠላትን የተባበረን ከመግደል እስከ ባርያን በእሳት አቃጥሎ መግደል በቅዱሳት መጽሐፍቷ የምትደነግግ ሃይማኖት ስለምንድነው ሁሌ እስልምናን እንደ ጭራቅ አቅርባ ራሷን ስለ ግድያ ሥርዓት ምንም እንደማታስተምር ሁሌ በቤተክርስትያን ሌላ እየሰበከች ይሄን እውነት የምትደብቀው?
2) ፍትሐ ነገሥት የተዘጋጀው ከ14ኛው ክ/ዘመን በኋላ ከሆነና በፍትኃ ነገሥት 'ባርያን' አስመልክቶ ህግ ከተደነገገ፥ በክርስትናው አለም ከ14ኛው ክ/ዘመን ጀምሮም ቢሆን Human Slavery እውቅና የተሰጠው መለኮታዊ መተዳደርያ ህግም የተቀመጠለት ነበር ማለት አይቻልም?
3) የሰውን ልጅ ስለጥፋቱ በእሳት አቃጥላችሁ ግደሉት የተባለው የባርያ ነፍስ ከሰው ስለማይቆጠር ነው ሌላ አይነት የአገዳደል መንገድ ያልተገለጸው ወይስ በኦርቶዶክስ የሰውን ነፍስ በእሳት አቃጥሎ መግደል የተለመደ Normal ነገር ስለሆነ ነው?

https://t.me/Orthodox_Critic
134 views18:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 21:21:17
98 views18:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 13:57:10 ማሻ አላህ፣ ባረከላህ የመሳሰሉ ዱዓዎች የቡዳ መዳኒቶች

ዘጋርዲያንስ ከ6 ቀናት በፊት ባለፈው ሳምንት እሁድ ባስነበበው ልጥፉ ለቅናትና የቅናት ውጤት ለሆነው አይነናስ(ብዳ) ልክፍት ነብዩ(ሰዐወ) መፍትሄ ነው ብለው ያስተማሩን ማሻ አላህ እና መሰል ዱዓዎች በሳይንስም ይህን መሰል መልካም ቃላት መጠቀም መፍትሄ እንደሆነ የባለ ታሪኳን Yasmina Floyer እና የሳይኮሎጂስቷ ዶ/ር Emma Hepburn የምስክርነት ቃላቸውን ዘርዝሮ አስቀምጧል።

Psychologist Dr. Emma Hepburn explains፦

“Language and emotion are intrinsically linked,”

“There is evidence that having more finely tuned emotion words to describe our feelings is beneficial to us. The language we use, to both ourselves and others, both verbally and written, can impact how we feel. Kind words can calm and regulate us, while harsh words can create a threat response.”

ሙሉውን አርቲክል በሚቀጥለው አስፈንጣሪ ያገኙታል
https://amp.theguardian.com/lifeandstyle/2022/jun/26/how-i-cope-with-feelings-of-envy-by-saying-the-arabic-word-mashallah-

@Abu_Mussaab
159 views10:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 21:36:23 አወወ የቀድሞው ቻናል ተዘግቶብኛል። አዳዲስ ጉዳዮችን እዚህ አዲሱ ቻናሌ ላይ ነው የምለጥፈው
t.me/religionandphylosophytogether
109 views18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 10:38:01 የኢየሱስ ሊበሰብስ የነበረ ሥጋው

በክርስትና ለኢየሱስ አምላክነት ማስረጃ ተደርገው ከሚቀርቡት አበይት ነጥቦች መካከል አንዱ ኢየሱስ ከሞተ በኋላ ሥጋው በዛው በስብሶ እንዳይቀረ ከቀናት በኋላ በትንሳኤው ዳግም ስጋ ለብሶ ከሞት መቀስቀሱ ነው ተብሎ ይታመናል።

~“ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና፤ ቅዱስህም መበስበስን እንዲያይ አታደርግም።”
— ሐዋርያት 2፥27 (አዲሱ መ.ት)

~"³⁵ ስለዚህ በሌላም ስፍራ፣ “ ‘ቅዱስህ መበስበስን እንዲያይ አትፈቅድም’ ይላል።
³⁶ “ዳዊት በራሱ ዘመን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ካገለገለ በኋላ አንቀላፍቶአል፤ ከአባቶቹም ጋር ተቀብሮ ሥጋው በስብሶአል።
³⁷ እግዚአብሔር ከሙታን ያስነሣው እርሱ ግን መበስበስን አላየም።"
— ሐዋርያት 13 (አዲሱ መ.ት)

ጥያዎች

፩. መለኮት የተዋሃደው ስጋ እንዴት በሞቱ ሊበሰብስ ይችል ነበረ ይባላል?

፪. ከሞቱ በኋላ እስከ ትንሳኤው ባሉ ቀናት መለኮቱ ስጋውን ተዋህዶ አብሮ ከነበረ፥ መለኮት የተዋሃደው ስጋ እንዴት ሊበሰብስ ነበረ ተብሎ ይወራል?

፫. ከሞቱ በኋላ እስከ ትንሳኤው ባሉ ቀናት መለኮቱ ስጋውን ተዋህዶ አብሮ ከነበረ፥ ያኔ አምላክ በማንነቱ አብ፣ መንፈስ ቅዱስ፣ ገነት የቆየችው የወልድ ነፍስ እና መሬት ስር የተቀበረው የወልድ ስጋ አንድ ላይ 4 ነው ማለት አይቻልም?
እግዚአብሔር በአንድ ወቅት አንድም፥ አራትም ነበረ ማለት ነው?

፬. ከሞቱ በኋላ እስከ ትንሳኤው ባሉ ቀናት መለኮቱ ስጋውን ተለይቶ ከነበረ የቆየው፥ በነኛ ቀናት የኢየሱስ ስጋው ምንም መለኮት የሌለበት ሊበሰብስ የሚችል ፍጡር ስጋ ነበር ማለት አይቻልም?

@Abu_Mussaab
297 views07:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 10:02:55 ኢትዮጵያ እና ግብጽ በባይብል

የኢትዮ ደጋፊ፦ ወዳጄ ነግሬሃለው ግብጽን አትደግፍ። ኢትዮጵያን የነካ እግዚአብሔር ነው የሚበቀልላት ይላል መጽሐፉ።

የግብጽ ደጋፊ፦ ምጥ ለናቷ አስተማረች አሉ። ጭራሽ አንተ ኢትዮጵያዊ ሆነህ የግብጽ ውለታ ተረስቶህ ለግብጽ ስለ ቅዱስ መጽሐፍ ልታስተምር ነው? ክርስትናን በኢትዮጵያ ያስፋፋችው ግብጽ እንደሆነች አትዘንጋ! በዚህ ደረጃም ግብጽን አትናቅ።

የኢትዮ ደጋፊ፦ እሱማ ልክ ነህ። ግንኮ ራሱ እግዚአብሔር ነው የተናገረው።
“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ግብጽን የሚደግፉ ይወድቃሉ፥ .. በእርስዋ ውስጥ በሰይፍ ይወድቃሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።”
— ሕዝቅኤል 30፥6

የግብጽ ደጋፊ፦ Ok እንደዛ ከሆነ አንተም ኢትዮጵያን መደገፍ የለብህም። እግዚአብሔር የኢትዮጵያም ጠላት ነው።

የኢትዮ ደጋፊ፦ እንዴት? ምን ማለትህ ነው?

የግብጽ ደጋፊ፦ በዛው ጥቅስ ቁ5 ላይ አንብበው፤ ኢትዮጵያም ከግብጽ ጋር በሰይፍ እንደምትወድቅ ሲናገር እንዲህ ይላል።
“ #ኢትዮጵያና ፉጥ ሉድም የተደባለቀም ሕዝብ ሁሉ ኩብም ቃል ኪዳንም የገባችው ምድር ልጆች #ከእነርሱ #ጋር #በሰይፍ #ይወድቃሉ።”
— ሕዝቅኤል 30፥5
ሌላም ልጨምርህ እዛው ላይ ከፍ ብለህ በቁጥር 4 እንዲህ ይላል።
“ሰይፍ በግብጽ ላይ ይመጣል፥ ሁከትም በኢትዮጵያ ይሆናል፤”
— ሕዝቅኤል 30፥4
እንዲሁም በቁጥር 9 ትንሽ ወረድ ስትል በኢትዮጵያውያን ላይ እንደ ግብጽ የሁከት ቀን እንደሚሆንባቸው ይናገራል።
“በዚያ ቀን መልእክተኞች ተዘልለው የሚኖሩትን #ኢትዮጵያውያንን ለማስፈራት ከፊቴ በመርከብ ይወጣሉ፤ #እንደ #ግብጽም ቀን #ሁከት ይሆንባቸዋል፤ እነሆ፥ ይመጣልና።”
— ሕዝቅኤል 30፥9

የኢትዮ ደጋፊ፦

የግብጽ ደጋፊ፦ በል አሁን ንገረኝ። ባይብል ላይ እግዚአብሔር ግብጽን አንኳሶ ኢትዮጵያን በማወደስ ከኢትዮጵያ ጎን እንደሚቆምና ግብጽን እንደሚያጠፋ ተናግሯል?

የኢትዮ ደጋፊ፦ አንተ ልክ ነህ እንደዛ አልተናገረም። ለማንም ሳይወግን እንደውም በዛ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ሁለቱንም ሀገራት እንደሚቀጣና እንደሚያጠፋ ነው የተናገረው። አመሰግናለሁ ወዳጄ

T.me/Abu_Mussaab
209 viewsedited  07:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-06 14:07:56 የህገ ዝንየት መሠረት በኦርቶዶክስ

ዝንየት ማለት ባጭሩ ጸያፍ ህልም ማለት ሲሆን አንድ ወንድ ተኝቶ መጥፎ ህልም በማየትም ይሁን ባለማየት ሳያውቀው በእንቅልፉ የዘር ፈሳሹ ሲፈሰው ማለት ነው። ሙስሊሞች 'ኢህቲላም' የምንለው በእንግሊዝኛ wet dream የሚባለው ነው።

የዝንየት ህግ በኦርቶዶክስ ቅዱሳት መጽሐፍት ታሪካዊ አመጣጥና መሠረት እንዳለው በተአምረ ማርያም መጽሐፍ ተአምር ቁጥር 58 ላይ ተጽፎ ይገኛል (የተአምር ቁጥሩ በአንዳንድ የተአምረ ማርያም መጽሐፍት እትሞች ሊለያይ ይችላል ለምሳሌ 41ኛ ተአምር ላይ የምታገኙባቸው ሁኔታዎች አሉ)።

ታሪኩ ላይ በአንድ ንጉስ በወርቅ፣ በብርና በሀር የተጌጠች በውስጧ በጣም ብዙ ለታቦቱ ተብሎ ንጉሱ የሰጠው ገንዘብ የተቀመጠባት በማርያም ስም ተሰይማ የተሰራች ቤተክርስቲያን ነበረች(በመሠረቱ አንድን መንፈሳዊ የአምላክ ቤት በጣም ውድ በሆኑ ስጋዊ ጌጦችና ገንዘቦች ማስዋብ ይቻላልን? የሚለው ጥያቄ በውስጥ አዋቂነት ይያዝልኝ)። በቤተክርስትያኗ ውስጥ ያለው በጣም ብዙ ገንዘብ ከመሆኑም የተነሳ ንጉሱ የማያውቀውና በቤተክርስትያን ዙርያ ያሉ የክርስትያን ልጆች የማያውቁት አንድም ሰው ወደዚያች ቤተክርስቲያን አይገባም ነበር።
የሚያገለግሏት ካህናት ሁሌ ቀንና ማታ እየተፈራረቁ ይጠብቋትም ነበር ይላል ታሪኩ።

ቀጥሎም፥ አንድ ቀን በቤተክርስቲያን ቅጽር ውስጥ ሌሊቱን ሙሉ ሲጠብቁ ካደሩት ካህናት መካከል አንዱ ካህን ዝንየት(wet dream) መታውና የስጋው ዘር ፈሰሰው። ከዛ የማርያም ተአምር ሲገለጥ ሰውየውና በዙርያው ያሉ ወንድሞቹም ማናቸውም ሳያውቁ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ መጥቶ ዝንየት የያዘውን ሰው እንደተኛ ከቤተክርስቲያን ቅጽር 80 ክንድ ያህል አርቆ ወስዶ አሳደረው። ሰውዬውም አድሮ እስኪነቃ ድረስ የት እንዳደረና ዝንየት እንዳገኘው እንኳን አላወቀም ነበር ይላል ታሪኩ።

ይህ ክስተት ከተከሰተ በኋላ ከንጉስና ከጳጳስ ዘንድ አዋጅ ነጋሪ ወጥቶ ማንም ቄስ፣ ዲያቆን፣ መነኩሴም ይሁን ምዕመን #ህልመ #ዝንየት #ያገኘው #ሰው #ወደ #ቤተክርስቲያን #ቅጽር #ጊቢ #የገባ #ባባታችን #በሐዋርያት #ቃል #የተወገዘ #ይሁን ተብሎ አዋጅ ተነገረ።

በምስሉም በቀይ የተከበበው ቁጥር 21 ላይ እንደምትመለከቱት ከዚህ ገጠመኝ ቀን በኋላ ቢሆን እንጂ ከዚህ በፊት እስከዚች ክስተት ጊዜ ድረስ ይህ ህግና አስተምህሮ ማለትም ዝንየት እዳ መሆኑንና እስከዚህ ገጠመኝ ድረስ የዝንየት ህግና ስርአት ስለማይታወቅ ዝንየት አይቶ ቤተክርስቲያን ከመግባት የተቆጠበ ሰው ኖሮ እንደማያውቅ በጥቅሉ በኦርቶዶክስ ስርአት የዝንየት እዳና ህግ እንደማይታወቅ በግልጽ ይናገራል።

ዝርዝሩን ተአምረ ማርያም መጽሐፍ ላይ ተአምር ቁጥር 58 ወይም 41 ላይ ይመልከቱ።

ጥያቄዎቻችን
1) ኢየሱስና ሐዋርያቱ ከኖሩበት 1ኛው ክ/ዘመን ጀምሮ ይህ የዝንየት ህግና ስርአት ምንም ሳይታወቅና ዝንየት የመታው ክርስትያን በተአምረ ማርያም የተጠቀሰው መቸቱ(መቼና የት) እንዲሁም በማን እንደሆነ የማይታወቀው ክስተት እስኪከሰትና በቅዱሳት መጽሐፍት ጸድቆ ለመላው ኦርቶዶክሳዊ ስርአቱ እስኪታወቅ ድረስ ለብዙ ማለትም ለአስራ ምናምን ክ/ዘመናት በቤተክርስትያን የዝንየት ህግ ሳይታወቅ ቆይቶ ተአማኒነቱ ማለትም መቼ፣የትና በማን? የሚሉትን ጥያቄዎችን በማይመልስ አንድ የኋላ ክስተት እንዴት ህግ ተደርጎ ሊጸድቅ ይችላል? ታሪኩ ላይ የባለ ታሪኩን ጨምሮ የማንም ስም እና ክስተቱ የተፈጸመበትን ጊዜ የሚገልጽ ምንም አይነት ማስረጃ አለመኖሩ በራሱ የታሪኩን ታማኝነትና ትክክለኛነት ጥያቄ ውስጥ ሊከተው አይችልም?
2) የዝንየት ስርአትና ህግ በብሉይ ኪዳን መጽሐፍት በኦ. ዘሌዋውያን እና በኦ.ዘዳ በተለያዩ ጥቅሶች ዝንየት የነካው ሰው የተቀደሰን ነገር እንዳይነካና ወደተቀደሰ ነገር እንዳይቀርብ ለ1 ቀን ከሰፈር ሁሉ ርቆ እንዲቆይ በግልጽ [“ከመካከላችሁ ሌሊት ዘር በማፍሰስ የረከሰ ሰው ቢኖር ከሰፈር ወጥቶ እዚያው ይቈይ።”—ዘዳግም 23፥10] ተብሎ ተነግሮ ሳለ፥ በኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ይህ ህግና ስርአት ለብዙ መቶ ክ/ዘመናት አይታወቅም ነበር ስትል ቤተክርስትያኒቱ የብሉይ ህግጋትን ባለማንበቧና ባለማወቋ ነው ወይስ ይህ የብሉይ ህግ በወንጌል ተሽሯል ብላ ስላመነች ነው?
3) የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን የብሉይ ኪዳኑ የዝንየት ህግና ስርአት ተሽሮ እንደነበር በማመኗ ከሆነ ለዘመናት ህጉን ያልፈጸመችው፥ ህገ ዝንየት በወንጌል ስለመሻሩ ቤተክርስትያን ማስረጃዋ ምንድነው?
4) ተሽሯል ቢባል ራሱ በኢየሱስና ሐዋርያቱ ወንጌል ለብዙ ዘመናት ተሽሮ የነበረን ህግና ስርአት ከዛ ሁሉ ጊዜ በኋላ መልሶ ህጉንና ስርአቱን የማጽደቅ ስልጣን ለአንድ ማንነቱና መቸቱ የማይታወቅ ካህንና ለገጠመኙ ሲባል እንዴት ሊሰጠው ይችላል?
5) በየትኛውም ዘመን ተአምር ተገለጠ፣ ገጠመኝ ታየ እየተባለ ለዛውም በግልጽ ማንነታቸው፣ መቼና የት እንደሆነ ባልታወቁ ግለሰቦች ምክንያት አዳዲስ ህግጋትና ስርአቶችን ወደ ቤተክርስቲያንና ክርስትና መጨመር በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ይቻላል?

https://t.me/Orthodox_Critic
185 views11:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-06 14:07:56
132 views11:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ