Get Mystery Box with random crypto!

እንኳን ደስ አለሽ የኔዋ የሆነ ድውው የሚል ድምፅ ተሰማና ክፍሉ በአንዴ ፀጥ አለ ከምቀመጥበት ጥ | AB Photography & graphic design

እንኳን ደስ አለሽ የኔዋ

የሆነ ድውው የሚል ድምፅ ተሰማና ክፍሉ በአንዴ ፀጥ አለ ከምቀመጥበት ጥግ መቀመጫ የተሰበሰቡትን ልጆች እያስረዳሁ ነበር የኔ ድምፅ ብቻ መሰማት ጀመረ ሁሉም ዞሩ ምንድነው ምንድነው አልን...

አብያ ወደቀችልህ አሉኝ ምንም አላልኩም እሷ እንደሆነች አወኩኝ ቶሎ ብዬ ወደሷ መሔድ ጀመርኩ እዛው ከወደቀችበት ሆና በሳቅ ፍርስስስ ትላለች እንባ በእንባ ሆናለች ጥቁር ዩኒፎርሟ እንዳለ አቧራ ሆኗል ቀይ ፊቷ በርበሬ መስሏል እስኪ ተነሽ ምንም አልሆንሽም ግን ብዬ አነሳኃት ደንግጬ ነበር ምንም አልሆነችም::

አሁንም ትስቃለች...ምን ሆነሽ ነው የወደቅሽው አልኳት ህህህህሂሂሂ እየሳቀች ዴስኩና ዴስኩን ተደግፌ ዥዋዥዌ ስጫወት አንድ እጄን አሟልጮኝ ነው አለችኝ ከልቧ እየሳቀች.........አንቺ ህፃን ብትሰበሪስ ኖሮ...እ.....እየተናደድኩኝ ነይ እሺ ቧንቧ ጋር እንሒድ አልኳት በአቧራ ያደፈ ልብሷን ልጠራርግ.............

እራኑ እብድ ልጅ ናት በጣም እብድ የምትባል

ሁሉም የሚወዳት ለሁሉም ታዛዥ ምታውቀውን ለማስረዳት ወደኃላ የማትል...ቅን ሰው ነች...መልካም ሰው ያላትን ከመስጠት ወደኃላ የማትል ቆንጅዬ አስተዋይ ጎበዝ ጠንካራ ሁሉንም በጥበብ የምታልፍ...ሴትነቷ ምንም ነገር ከማድረግ የማያግዳት ሁሉንም ነገር በስኬት የምታጠናቅቅ

አብረን አጥንተን ለፍተን ሁሌም አንደኛ ግን እሷ ነበረች የኔ ተወዳጇ አብያ ወላሂ ይሔን እራስህ ያስረዳኽኝን ነው ኤክስ የሆንከው ትለኛለች የማውቃት ሁለቱንም አመት ከክፍላችን አንድኛ ነው የወጣችው....እራኑ ትለያለች ሁሌም ነው የምትስቀው ካልሳቀች ክፍላችን ውሃ ያጣ አበባ ነው የሚመስለው ከስፖርት ስንገባ ዴክስ ላይ ትሮጣለች ሰዎችን ታበሽቃለች ብቻ ስንቱ ሁሉም ይወዳታል........

ክላስ ከቀረሁ ኩርፊያዋን አልችለውም እራኑ ለኔ ታናሽ እህቴ ነበርች ምትፈልገውን ሳታስፈቅደኝ ነው የምትወስደው ከከፋት እኔጋር ነው የምትመጣው...ያ ሳቂታ ፊት ሲከፉው ከማየት ሰማይ ቢደፋብኝ ይሻለኛል........

ሁለት አመት አንድ ክፍል ውስጥ አብረን ነው ያሳለፍነው..............ሳንለያይ.....

11...12.......ሌላ ትምህርት ቤት ብትገባም ቦታ አልወሰነንም አሁንም ያፍቅራችን አለ.......

ዩኒቨርስቲ መሔዷ እራስን ለመቻል ጥሩ እንደሆነ ተማምነን ነበር የሔደችው......ውጤት ግን አንደኛ ሆና እንድትመረቅ ቃል ተገባብተን ነበር የሸኝኃት..

ብዙ የዩኒቨርስቲ ገጠመኞቿን አልፋ ይኸው በሲቪል ኢንጂኔሪንግ ከሴቶች ዲፓርትመንት 2ሆና አጠናቃልኛለች የኔ ተወዳጅ እህቴ ራኑዬዬዬዬ ሩታዬዬዬዬዬ...

እንኳን ደስ አለሽ
ሁሌም እልሽ የለ እግዚአብሔር ከቅን ሰዎች ጋር ነው አሳክተሽዋል

ውጤቱ ለምን ሁለተኛ ሆነ ብዬ ስቀውጠው በሀገራችን የቦለጢቃ ችግር ይሔም በቂ እኮ ነው እንዴት ሆነን እንደተማርን እያወክ አለችኝ እውነታውን አምኜ ተቀብያለሁ.......

አንተነህ የምትድረኝ ትለኛለች ይቺ ስርዓት ያጣች ልጅ


ተወዳጇ