Get Mystery Box with random crypto!

ሰሞኑን በሰሜን ወሎ ዞን ተከስቶ በነበረው የፀጥታ ችግር በውይይት መፈታቱ ተገለፀ ተከስቶ በነበረ | አቢሲኒያ - Times

ሰሞኑን በሰሜን ወሎ ዞን ተከስቶ በነበረው የፀጥታ ችግር በውይይት መፈታቱ ተገለፀ

ተከስቶ በነበረው የፀጥታ ችግር በሐይማኖት አባቶች፣ በአገር ሽማግሌዎች እና በዘወልድ ሽምግልና ስርዓት የሠላም ስምምነት ተደረገ። በሰላም ስምምነት ስነ ስርዓቱ ላይ የአገር መከላከያ ሠራዊት፣ የክልል፣ የዞን፣ የምስራቅ አማራ ፉኖ አመራሮች እና የአገር ሽማግሌዎች የሰላም ስምምነቱን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫውም በግጭት የሚፈታ አጀንዳ እንደሌለና ሁሉም ጉዳይ በሰላምና በመወያየት መፍታት እንደሚቻልና በተፈጠረው የፀጥታ ችግር በማዘናቸው ይቅርታም ጠይቀዋል ።

የፋኖ አደረጃጀት ህዝባዊና ከመንግሥት አደረጃጀት ውጭ በመሆኑ  መንግሥት ባስቀመጠለት አማራጭ በመጠቀም ህጋዊ ወደሆነው መንግስታዊ መዋቅር እንዲገባ ምቹ ሁኔታ በመንግስት እንደተፈጠረም በመግለጫው ተገልፇል ሲል የሰሜን ወሎ ኮሙኒኬሽን ነው የዘገበው።

@abisiniya_times