Get Mystery Box with random crypto!

አገር የሚገነባ ሳይሆን፥ የሚያተራምስ ውሳኔ! ሀ) የአገሪቱ ምልክት የሆነን ተቋም በማጥቃት አገር | አቢሲኒያ - Times

አገር የሚገነባ ሳይሆን፥ የሚያተራምስ ውሳኔ!

ሀ) የአገሪቱ ምልክት የሆነን ተቋም በማጥቃት አገር አፍራሽ አፍራሽነቱን፥ አማራና አፋር ክልሎችን ወርሮ ሺሕዎችን በመግደል፣ መጠነ-ሰፊ ንብረት በማውደምና በመዝረፍ አገር አፍራሽነቱ የተረጋገጠው የወያኔ ሠራዊት ትጥቅ ሳይፈታ የአማራና የአፋር ልዩ ኃይሎችን ማፍረስ እነዚህ ክልሎች ደግም ለወረራና ጥቃት እንዲጋለጡ መፍቀድ ነው። በመሆኑም አገርን የሚገነባ ሳይሆን የሚያተራምስ ውሳኔ ነው!

ሁ) ኦነግ-ሸኔና ተባባሪዎቹ በየክልሉ እየገቡ ሕዝብን እያሸበሩ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል አማራውንና ሌሎችንም ወገኖች እየጨፈጨፉ ባሉበት ወቅት፥ እነዚህ የጥፋት ኃይሎች ትጥቅ ሳይፈቱ የየክልሎችን ልዩ ኃይሎች ማፍረስ ያለተከላከያ እንዲጠቁ የሚያደርግ ነው። ስለሆነም ውሳኔው አገርን የሚታደግ ሳይሆን ይበልጥ ትርምስ የሚፈጥር ነው።

ይህን የእብደት ውሳኔ የወሰኑ አካላት ያው እንደተለመደው "በለውጥ ጊዜ ሰው ይሞታል" እያሉ በሞታችን የሚሳለቁብን አካላት እንደሆኑ ግልጽ ነው። ስትጨርሱን ዝም ብለን አናይም ብለን መቃወምና መታገል የሚገባን እኛው ነን!

ጉዳዩ የክልል ልዩ ኃይሎች እንዲኖሩ የመፈለግ አይደለም። አጀንዳው እነዚህ ኃይሎች ከመፍረሳቸው በፊት አገር አፍራሾቹ የጥፋት ኃይሎች ትጥቅ ይፍቱ የሚል ነው!!!