Get Mystery Box with random crypto!

የአልቃይዳ መሪ አይማን አል ዛዋሂሪ አፍጋኒስታን ውስጥ በአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት መገደ | Abel Birhanu የወይኗ ልጅ

የአልቃይዳ መሪ አይማን አል ዛዋሂሪ አፍጋኒስታን ውስጥ በአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት መገደሉን ዩናይትድ ስቴትስ አስታወቀች።የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የተሳካ ያሉት ይኽው ጥቃት የዩናይትድ ስቴትስ ጠላቶች ሁሉ ግልጽ መልዕክት ነው ሲሉ ዋሽንግተን ውስጥ ተናግረዋል ። የሀገራቸው የስለላ ድርጅት ሲአይ ኤ የኦሳማ ቢን ላደን ተተኪ የተባለውን አል ዛዋሂሪ በያዝነው በጎርጎሮሳዊው 2022 ካቡል አፍጋኒስታን ውስጥ እንዳለ እንደተደረሰበት እና ከሳምንት በፊት፣ በአል-ዛዋሂሪ ላይ "ርምጃ" እንዲወሰድ መፍቀዳቸውን የተናገሩት ባይደን ጥቃቱ መድረሱን ማረጋገጣቸውንም ገልጸዋል። « ከቤተሰቦቹ መካከል አንዳቸውም አልተጎዱም። በሰላማዊ ሰዎች ላይም ምንም ጉዳት አልደረሰም። አሁን ይህን ዜና ለአሜሪካ ህዝብ የማካፍለው የተልእኮውን ስኬት ከፈጸሙ የፀረ ሽብር ማህበረሰብ እና ከፍተኛ ጥረት ካደረጉ ቁልፍ አጋሮች ካረጋገጥኩ በኋላ ነው።»
ግብፅ ሀገር የተወለደው አል ዛዋሂሪ አይማን እጎአ መስከረም 11 ቀን 2001 ዓ ም ኒውዮርክ ዩናይትድ ስቴትስ ከተፈፀመው የሽብር ጥቃት ጀርባ እጁ እንዳለ ይታመናል። እንደ ዩናይትድ ስቴትስ ገልፃ ቢን ላደንን የተካው የአልቃይዳ መሪ የተገደለው እሁድ ጠዋትነው። 71 ዓመቱ ነበር። ዩናይትድ ስቴትስ በጥብቅ የምትፈልገውን ይህ ሰው ያለበትን ቦታ ለጠቆመ 25 ሚሊዮን ዶላር እንደምትሰጥ አስታውቃ ነበር።

# DW Amharic