ገበሬው በጣም የሚወደው ፈረሱ ይታመምበትና ሀኪም አስጠርቶ ያስመረምረዋል ። ሀኪሙም ፈረሱ አርእጅቷል መድኃኒት እንስጠውና ከ3 ቀን በፊት ካልተሻለው ላንተም ሸክም ከሚሆን እንታገለዋለን ብሎት ሄደ ። ይህን ሲያወሩ ፍየል ሰምታ ኖሮ ለፈረሱ ያወረቱን ሁሉ እያዘነች ነገረችው ። በ3ተኛው ቀን ሀኪሙ መጣ ፈረሱም ለውጥ አላሳየም ይህን ጊዜ ሊገሉት ወሰኑ ጓደኛዬ አንተን ማጣት አልፈልግም ። ሳይገሉህ በፊት ሸክም አለመሆንህን ተነስተህ አሳያቸው ብላ እያለቀሰች ለመነችው በፍየሏ ግፊት እንደ ምንም ተነስቶ መሮጥ ጀመረ ። ገበሬው እና ሀኪሙ ያዩትን ማመን ገበሬ በፈረሱ መዳን ተደስቶ ፍየሏን አርዶ በላት ። ይህ የአለም መራር እውነት ነው ። መልካም ስራ ሰርታችሁ በምስጋና ፈንታ ውርደትን ትሸለማላችሁ ። ያም ቢሆን ግን ቅን ሰው ከመሆን አትቦዝኑ ። Share// #𝙢𝙪𝙧𝙞𝙙𝙮𝙣𝙖𝙩𝙪 SHARE:@ABEENAKEBEC SHARE:@ABEENAKEBEC 10.6K views𝕕𝕣𝕖𝕒𝕞𝕖𝕣, 03:22