Get Mystery Box with random crypto!

የአሹራ ፆም ሙሐረም 10 ነብዩላህ ሙሳ(ዓ.ሰ) ከአንባገነኑ የፊርዓውን ጭቆና ነፃ የወጡበት ቀን ነ | ❤️ የስነ–ልቦና ምክር (የተውበት እባዎች😭😭]

የአሹራ ፆም
ሙሐረም 10 ነብዩላህ ሙሳ(ዓ.ሰ) ከአንባገነኑ የፊርዓውን ጭቆና ነፃ የወጡበት ቀን ነው::
ይህን ቀን አንድ ቀን ቀደም ተብሎ ሙሐረም 9 አልያ ሙሐረም 11ን በማስከተል መፆም
ይወደዳል::
የፊታችን እሁድ የሙሀረም ወር ዘጠነኛው ቀን ነው - ረሱል ስለ አሹራ ፆም ሲናገሩ "ምናልባት
ለሚቀጥለው አመት በህይወት ከቆየሁ ዘጠነኛውንም እፆማለሁ ብለዋል (ሶሒሁ ሙስሊም
1134)
ሙሐረም 10 የአሹራ ቀን ዕለተ ሰኞ ነው:: ይህን ቀን መፆም የአላህ መልዕክተኛ(ሰዓወ)
"የአንድ አመት ወንጀል ያስምራል ብዬ በአላህ ላይ ተስፋ አደርጋለው ብለዋል (ሶሒሁ
ሙስሊም 1163)
ቤተሰባችንንም ሌላውንም ይህን መልዕክት እናስታውስ
የስነ–ልቦና ምክር ለሙስሊሙ ኡማ
@Abdulhakemohammed
@Abdulhakemohammed