Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዛሬው እለት ሀምሌ 01/ 2014 የወጣውን የ 20/80 እና 40/ | የጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ እውነተኛ ደጋፊዎች

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዛሬው እለት ሀምሌ 01/ 2014 የወጣውን የ 20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
በመግለጫውም ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፤ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው ፤ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት የአጣሪ ቡድን መሪ አቶ በሀይሉ አዱኛ መግለጫውን በጋራ ሰጥተዋል፡፡

በዚህ መግለጫ የከተማ አስተዳደሩ ከኢንሳ፤ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፤ እንዲሁም ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አጣሪ ቡድን እንዲቋቋም ተደርጎ ወደ ማጣራት ስራ በመግባት ሲጣራ ቆይቶ በዛሬው እለት በጋዜጣዊ መግለጫው ይፋ ተደርጓል፡፡

ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ያነሷቸው ነጥቦች ከዚህ እንደሚከተሉት ናቸው፡-

በጋዜጣዊ መግለጫው ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደገለፁት የጋራ መኖርያ ቤት እጣ በማውጣት ሂደት ባጋጠመን ችግር ህዝቡንም ከተማ አስተዳደሩንም ያሳዘነ ድርጊት መፈፀሙን አንስተዋል፡፡

በዚህ አንገብጋቢ ጉዳይ ላይ ህብረተሰቡ በትእግስት በመጠበቅ እንዲሁም የጀመርነውን ጥረት ከጎናችን በመቆም ላሳየው ጥረት ከልብ እናመሰግናለን ብለዋል፡፡

ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ለህዝባችን ቃል በገባነው መሰረት ችግር ቢያጋጥም እንኳን በቀጥታ ኦዲት እናደርጋለን ብለን በገለፅነው መሰረት ጥቆማ ስለደረሰ ጊዜ ሳንሰጥ በሚመለከታቸው አካላት የማጣራት ስራ እንዲጀመር አስደርገናል፡፡

የቴክኖሎጂ ውንብድና አጋጥሞናል፡ አመራር የመራው ውንብዳ ነው፡፡ በዚህ ሂደት የቤት ስርቆት ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ ፍላጎት ጭምር መግለፅ ይቻላል ብለዋል፡፡
 የዚህ ስራ ሌላው አላማ መንግስት ህዝብን ማገልገል ብቃት የለውም የሚል ገፅታ ለመፍጠርና ህብረተሰቡ በመንግስት ላይ እንዲያምፅ ለማድረግ በማሰብ ነው በማለት ከንቲባ አዳነች ገልፀዋል፡፡

በዚህ ሂደት ችግር እንዳጋጠመን ማጣራት መጀመራችን ህዝብን ሃብት መታደግ እንድንችል አድርጎናል፡፡ ህዝቡን መታደግ ችለናል፡፡

ህብረተሰቡም መብቱን ለማስጠበቅ ያደረግነውን ጥረት ተረድቶናል፡፡ እኛም ድሃውን ማህበረሰብ መታደግ በመቻላችን ያስደስተናል፡፡

የቀረበልን ሪፖርት በሚገባ ሲስተሙ ተቆጣጣሪ ጭምር እንዳለውና አስተማማኝ እንደነበረ ነበር፡፡ ይህንንም ለማመን ምክንያቶች ነበሩ፡፡ ምክንያቱም ከዚህ በፊት በዚህ ቡድን የለሙና ጥቅም ላይ የዋሉ ሲስተሞች ነበሩ፡፡

ማረጋገጫ ለማግኘት የተሄደበትና ተቋም ለተቋም የተደረጉ ግንኙነቶችም ችግር ነበረባቸው፡፡ ሰዎች ለሰዎች የተደረጉ ግንኙነቶች አይነት የተደረጉ ግንኙነቶችም መመልከት ተችሏል፡፡

ኢንሳ ማረጋገጫ ሰጥቶ እንደነበርም በወቅቱ ተገልፆ ነበር ነገር ግን ህጋዊ በሆነ ደብዳቤ ኢንሳ ያረጋገጠው እንዳለሆነ ታይቷል፡፡

ዳታው በሰዎች አጅ ለአምስት ቀን ያህል መቆየቱና ይህም የተከናወነው በሃላፊዎች ትእዛዝ እንደነበር ገልፀዋል

ነገር ግን የምዝገባው ዳታውን በቴሌግራም ጭምር ሲላላኩ እንደነበር በኋላ በምርመራ መታወቁን

በሂደቱም እጣ ቁጠባ ያቋረጡ ሰዎች ፤ቁጠባቸውን ከረሱበት ቦታ ጭምር እጣ እንዲወጣላቸው መደረጉን

የማጣራት ሂደቱን እጣ የወጣ እለት ከሰዓታት በኋላ መጀመሩን ከንቲባ አዳነች ገልፀዋል፡፡

ይህ የማጣራት ሂደት ኢንሳ አራት ባለሙያዎች መወከሉንና ከዚህ በተጨማሪም ከሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም ከብሄራዊ ደህንነት የተዋቀረ ኮሚቴ በኢንሳ አስተባባሪነት ስራውን ሲሰራ መቆየቱን ገልፀዋል፡፡

ቴክኖሎጂዎች ለመጠቀም ያደረግነውን ጥረት ወደፊትም አጠናክረን እንቀጥላለን፤ ቴክኖሎጂዎችን የሚያለማው ሰው ቢሆንም ወደፊት በረቀቀ የሙያ ስልት እጣ አወጣጡን ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን እናድርጋለን

እዚህ በግልፅ ማንሳት የምንፈልገው በወቅቱ የተሰጠን ማብራርያ ከእውነቱ የራቀ መሆኑን በባለሙያዎች ጭምር ተረጋግጧል፡፡

ባለሙያዎችና አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ እንዲሁም አንድ ሃላፊና አንድ ምክትል ሃላፊ ከሃላፊነታቸው ተነስተዋል፡፡

ሌሎች እርምጃዎች እንደ ሚዛኑ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ አሁንም ቆራጥ አቋሙ ህዝቡን መብት ማስከበረት መሆኑን ይህንን ቤት ለህዝብ ለማቅረብ ከ21 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ጭምር የጎደለውን መሰረተ ልማት በሟሟላት ለህዝብ ማድረሱን

በፍትሃዊነት ህዝብን ሃብት ለማድረስና የኋላ የኮንዶሚኒየም መጥፎ ታሪክን ላለመድገም ከፍተኛ ፍላጎት ነበረን፡፡ አሁንም ይቀጥላል፡፡

አሁንም ተቋም ግንባታ አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡

ስለሆነም በዚህ ሁሉ ችግር እና ሂደት የወጣን እጣ ተዓማኒነት ስለሌለው እጣው ሙሉ ለሙሉ ውድቅ እንዲሆን አድርገናል፡፡

የቴሌግራም ቻናል https://t.me/abdisira
የፌስ ቡክ ግሩኘ https://facebook.com/groups/1214264802267291/