Get Mystery Box with random crypto!

ህግ ይከበር….,,,, የመንደር የፖለቲካ አስተሳሰብ እና ቅዥት የህግ ገደብ ሊደረግለት ይገባል : | የጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ እውነተኛ ደጋፊዎች

ህግ ይከበር….,,,,

የመንደር የፖለቲካ አስተሳሰብ እና ቅዥት የህግ ገደብ ሊደረግለት ይገባል ::
የባልደራስ ቤተ መንግስትን የመውረር ህልም አመፅ እና ግጭት ባለበት ቦታ ሁሉ ጠፍቶ የማያቀው፣ ከፖለቲካ አስተሳሰብ ይልቅ በሀይማኖት መመሳሰልና በአንድ ጎሳ ላይ ለአደረጃጀቱ ቅድምያ ሰጥቶት እንደተዋቀረ በብዙዎቹ የሚገለፀው

በእድሜ ዘመኑም ግልፅ የሆነ ጉባኤ አድርጎ የማያቀው እና የአባላቶች ቁጥር እንኳን በውሉ የማይታወቀው ባልደራስ ፓርቲ ፌስቡክ ገፁን የፖለቲካ አቋም ለደጋፊዎች ከማሳወቅ ይልቅ በተራ እና በሀሰተኛ ዘገባዎች በሰበር ዜና ስያሜ በየእለቱ እያመረተ በማስተላለፍ ተጠምዶል ይህ አመፅ ወዳጁ ስብስብ ... በሲሪላንካ በቤተመንግስት ተቃውሞ እና ያሳዩት ድርጊቶች የሎተሪ እጣ የደረሰቸው እስኪመስል ድረስ ባልደራሶችን አስደስቷል፤ ይህ የደሰታ ምክንያታቸው ደሞ በዛ ሀገር የታየው አመፅ እና አግባብነት የሌለው ግርግር ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጣ ከመመኘት የመነጨ ነው::

ህዝቡ የነሱን በስልጣን ጥም የፈለቀን ብልሹ ሀሳቦችን ተቀብሎ እንዲያራምድ እና በዚህም ሀገርን በሚያጠፋ ድርጊቶች ምርኩዝ አርጎ 4 ኪሎን ለመግባት የሚያስችል አጋጣሚ ስለመሰላቸው ነው የምስራች ያህል አስደስቶቸው የዘገቡት። ራሱን “ለእውነተኛ ዲሞክራሲ” የሚል ስያሜ የሰጠው ይህ ስብስብ ያለምንም ይሉኝታ አመፆች እንዲፋፋሙ ጥሪ ሲያደረግ ሁሌም ይስተዋላል፤ በነዚህ አመፆች የሚመጣ ዲሞክራሲ ያውም እውነተኛ ዲሞክረሲ ከባልደረስ በቀረ የዲሞክራሲ ፈጣሪዎችም፣ ተንተኞችም አያውቁትም። ባልደራስ ፓርቲ ግን በዚህ ልክ ፅንፍ መውጣቱ ለማንም አካል የማይጠቅም ሀገር አፍራሽ ስብስብ መሆኑን ያረጋግጣል፤ ይህ ስርዓት አልበኝነት የሚያነግስ ጋጠ ወጥ ሀሳቡን ማሰራጨቱ በህግ ሁሉ ሊያሳግደው እንደሚገባም ሳንናገር ማለፍ አንፈልግም።