Get Mystery Box with random crypto!

የሰሞኑ ጉንፋን! የሰሞኑ ጉንፋን ለየት የሚያረገው ግን ከፍተኛ ትኩሳት እና ጠንከር ያለ ሳል አለ | ኤቢ ዲሽ እና የኤሌክትሮኒክስ ጥገና

የሰሞኑ ጉንፋን!

የሰሞኑ ጉንፋን ለየት የሚያረገው ግን ከፍተኛ ትኩሳት እና ጠንከር ያለ ሳል አለው በተጨማሪም እነዝህ ምልክቶች ይታዩበታል፡፡

• ብርድ ብርድ ማለት
• የመገጣጠሚያ ህመም
• የጀርባ ህመም
• የጡንቻ ህመም
• ምግብ ፍላጎት መቀነስ
• ኃይለኛ ራስ ምታት
• ፍዝዝ ማለት

ምክንያቱ ምን ሊሆን ይችላል ?

ጉንፋን ዋና መንስኤዎቹ በትንፋሽ በሳል እና በማስነጠስ የሚተላለፉ ቫይረሶች ናቸው። ለምሳሌ÷ ኮሮና ቫይረስ ፣ራይኖ ቫይረስ፣ ኢንፍሉዌንዛ አዴኖ ቫይረስ እና የመሳሰሉት ጉንፋንን ሊያመጡ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ የሰሞኑ ጉንፋን ኮሮና ይሁን አይሁን የሚታወቀው በምርመራ ብቻ ነው። ስለዚህ ምን እናድርግ?

• የመከላከያ መንገዶቹን ይተግብሩ
• ሁሌም የአፍ እና አፍንጫዎን ይሽፍኑ
• የእጅ እና አካል ንክኪ ይቀንሱ
• ሰዉ የሚሰበብበት ቦታ አይገኙ
• ስያስሉ እና ሲያስነጥሱ አፍ እና አፍንጫዎን በክንድዎ/በጨርቅ ይሸፍኑ
• መንግስት በነፃ ያቀረበውን የኮሮና ክትባትን ይውሰዱ

ለልጆች እና ህፃናት የቤት ዉስጥ ሕክምናው ምንድነው?

• ለብ ያለ ዉሃ ዉስጥ ትንሽ ጨው አርጎ አፍንጫቸው ቀዳዳ ዉስጥ 2 ጠብታ ማድረግ በመቀጠልየአፍንጫ ቀዳዳዎችን በመምጠጫ ማጽዳት
• ትኩሳትን የሚቀንስ መድሃኒት መጠቀም ፣
• ትኩስ ትኩስ ነገሮችን ማጠጣት
• ተጨማሪ ምግቦችን በደንብ መመገብ
• የሕፃኑን ክፍል በደንብ ማፅዳት ማናፈስ
• ቤቱን በውሀ እንፋሎት ማጠን
• ንፍጥ እና ትኩሳት በጣም አስፈላጊ ፈሳሾችን እና ንጥረ ነገሮችን ይዘው ስለሚወጡ ተጨማሪ ፈሳሽ ነገሮችን ማግኘት ይኖርባቸዋል።

ለታዳጊ ህፃናት እና ለአዋቂዎችስ የቤት ዉስጥ ሕክምናው ምንድነው ?

• ከላይ ከተዘረዘሩት በተጨማሪ ራስን በአንድ ክፍል ማግለል
• ትኩስ ፈሳሽ ነገሮችን ደጋግሞ መውሰድ
• ነጭ ሽንኩርት ማር እና ዝንጅብል መጠቀም
• በቂ እረፍት ማድረግ
• የትኩሳት እና ራስ ምታት ማስታገሻ መውሰድ
• እነዚህን መፍትሄዎ እያረጋችሁ ምንም ለውጥ ከሌለው እና ሳሉ የመባስ ትኩሳቱ የመጨመር ባህሪ ካለው ወይም ትንፋሽ የማጠር ምልክት በህፃንም ሆነ በአዋቂ ላይ ካለ በአፋጣኝ ሆስፒታል መሄድ ያስፈልጋል፡፡

ዶ/ር ፋሲል መንበረ
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ረዳት ፕሮፌሰር እና የሕጻናት ስፔሻሊስት ሐኪም

Credit : ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ