Get Mystery Box with random crypto!

ለዛሬ ሪሴቨር ስንገዛ ማወቅ ስላለብን ነገሮች በትንሹ እናያለን! በገበያ ላይ ብዙ አይነት ሪሴቨሮ | ♦አቡላ ዲሽ

ለዛሬ ሪሴቨር ስንገዛ ማወቅ ስላለብን ነገሮች በትንሹ እናያለን!

በገበያ ላይ ብዙ አይነት ሪሴቨሮች አሉ
አብዛኛዎቹ AVC ( H.264 ) ሲሆኑ የተወሰኑት HEVC (H.265 ) ናቸው!

AVC ( H.264 ) ምንድነው?
AVC ( H.264 ) ማለት ADVANCED VIDEO CODING ሲሆን ይሄም ከ 4×4 pixel እስከ 16×16 pixel የሆኑ Video ብቻ የሚያጫውትልን ሲሆን ከዛ በላይ የሆኑ Video ምስሎችን ምስል ማሳየት አይችልም ለዛም ነው ድምፅ ብቻ እየሰማን ምስል ማናየው!

HEVC H.265 ምንድነው?
HEVC H.265 ማለት HIGH EFFICIENCY VIDEO CODING ይሄም ከ 4×4 pixel አስከ 64×64 pixel ድረስ ማጫወት ስለሚችል ማንኛውንም VIDEO CODING ማጫወት ይችላል!


አብዛኛ ሰው በተለይ AMOS ተጠቃሚ ስለሪሴቨሮቹ ከመጠየቅ ይልቅ ነፃ ሰርቨር አለው ሲባል ብቻ ተሯርጠው ከገዙት በዋላ በገዛ ብራቸው ይቃጠላሉ!

ETHIOSAT ተጠቃሚዎች ደግሞ HD ሪሴቨር መሆኑን ብቻ አይተው ይገዛሉ! ከገዙት በዋላ በሪሴቨሩ መበጥበጥ ነው!

ሪሴቨሩ ዋነኛ የሚበጠብጠው!
1ኛ ድምፅ እያሰማ ምስል አላሳይ ማለት
2ኛ ምስል እያሳየ ድምፅ አላመጣ ማለት ናቸው


ሪሴቨር ሲገዙ ማወቅ ያለቦት ዋና ዋና ነገሮች!
ሪሴቨሩ HEVC H.265 መሆኑን
ሪሴቨሩ Dolby Digital Plus sound Support ማድረጉ
ሪሴቨሩ ቶሎ ቶሎ SOFTWARE እንደሚለቀቅለት ማወቅ
ሪሴቨሩ መለዋወጫ እንዳለው ማወቅ

አቡላ ዲሽ