Get Mystery Box with random crypto!

ቤት የፈረሰባቸውን ሰዎች ለማነጋገር የሄዱ የዓባይ ቴሌቪዥን የቀረጻ ባለሙያዎች ታሰሩ:: በአዲስ | Abbay TV

ቤት የፈረሰባቸውን ሰዎች ለማነጋገር የሄዱ የዓባይ ቴሌቪዥን የቀረጻ ባለሙያዎች ታሰሩ::

በአዲስ አበባ ከተማ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ቤት የፈረሰባቸውን አቤቱታ አቅራቢዎች ለማነጋገር የሄዱ የዓባይ ቴሌቪዥን የቀረጻ ባለሙያዎች ከእነአቤቱታ አቅራቢዎች ዛሬ ረፋዱን አምስት ሰዓት አካባቢ መታሰራቸውን የዓባይ ቴሌቪዥን ባለደረቦች አረጋግጠዋል፡፡

ዛሬ ጠዋት በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ቤት ፈረሰብን ያሉ አቤቱታ አቅራቢዎችን ሁኔታ በአካል ለመመልከትና ዘገባ ለመስራት በስፍራው የደረሱት የዓባይ ቴሌቪዥን ካሜራ ማንና ባልደረባው ቀረጻውን ተከልክለው በጸጥታ ሃይሎች መወሰዳቸውን ካሜራ ማኑ እስሩ በተፈጸመበት ወቅት ወደ ቢሮ በመደወል አሳውቋል፡፡

ነገር ግን መታሰራቸውንና ወደ ጣቢያ እየወሰዷቸው እንደሆነ ካሳወቀ በኋላ የጸጥታ ሃይሎች ስልኩን ስለተቀበሉት ወዲያውኑ እንደተዘጋና እንደማይሰራ የጣቢያው ባልደረቦች አስረድተዋል፡፡

ከዚያ በኋላ በተደረገ ማጣራት የታሰሩት የሚዲያው ባልደረቦች የካ አባዶ አካበቢ ወረዳ አስራ ሶስት ፖሊስ ጣቢያ እንደሚገኙ ማወቅ እንደቻሉ የሚዲያው ሃላፊዎች ተናግረዋል፡፡

@Abbay_Tv