Get Mystery Box with random crypto!

በታንዛኒያ በእስር ቤቶች የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ለመመለስ ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር እየተሰራ መሆ | Abbay TV

በታንዛኒያ በእስር ቤቶች የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ለመመለስ ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ::

በታንዛንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሽብሩ ማሞ በሕገ ወጥ ደላሎች ተታልለው በታንዛኒያ በእስር ቤቶች የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ለመመለስ ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

አምባሳደሩ እንደገለጹት በተለያዩ ጊዜያት በታንዛኒያ በኩል አድርገው በማላዊ ድንበር ወደ ደቡብ አፍሪካ በሕገ-ወጥ መንገድ ለመሻገር ሲንቀሳቀሱ የተገኙ 5 ሺሕ ኢትዮጵያዊያን በታንዛንያ መንግስት በቁጥጥር ሥር ውለው ለእስር መዳረጋቸውን አስታውሰዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ከዓለም አቀፍ የፍልሰት ድርጅት ጋር በመተባበር በተያዘው ዓመት 1 ሺሕ 99 የሚሆኑትን ከታንዛኒያ እስር ቤቶች ወደ አገር ቤት መመለሱን ገልጸዋል።

በቀጣይም መንግስት በታንዛኒያ በእርስ ቤቶች የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ለመመለስ ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን በዘላቂነት ለመግታት በኬንያና ኢትዮጵያ እንዲሁም በኬንያና በታንዛንያ ድንበር አካባቢ ጠካራ የቁጥጥር ሥራ ለመስራት አገራቱ መስማማታቸውን ገልጸዋል።

@Abbay_Tv