Get Mystery Box with random crypto!

የመገላለጥ ስልጣኔ ሴት ልጅ ከወንድ የተለየና ክብሯን የሚጠብቅ ሰፋ፣ ረዘም፣ ወፈር ያለና በራ | channel 0

የመገላለጥ ስልጣኔ

ሴት ልጅ ከወንድ የተለየና ክብሯን የሚጠብቅ ሰፋ፣ ረዘም፣ ወፈር ያለና በራሱ ጌጥ ሆኖ ወንድን የማይስብ ልብስ እንድትለብስ ኢስላም ያዛታል።
ሙስሊም መሆን ማለትም ለአላህ እጅና እግርን ሰጥቶ መኖር ማለት ነው፤ልብስ ደግሞ የማንነት መገለጫም ጭምር ነው።
ትክክለኛ አማኝ ሴት አለባበሷ ኢስላማዊ መስፈርትን ያሟላና ከቀደምት አማኝ ሴቶች ጋር የሚመሳሰል እንዲሆን ጥረት ታደርጋለች፤ልቧ ውስጥ ያለው ኢማን የሳሳና የደከመ ሴት ግን ከላይም ልብሷ ስሥ እና አጭር ይሆናል።
በስሥና አጫጭር ልብሶች መገላለጧም እሷ እና ሆን ብለው የሚመለከቷት ወንዶች ላይ የአላህን ቁጣና እርግማን ያመጣል፤ለዝሙትና ለብልግናም ይጋብዛል።
ሴት ልጅ በታዘዘቸው መሰረት ከባዕድ ወንድ እይታ የሚከልላትን ልብስ ስትለብስ ክብሯን ትጠብቃለች፣ ብዙዎች ወንጀል ላይ እንዳይወድቁም እገዛ ታደርጋለች።
የራስንና የሌሎችን ጥቅምና ደህንነት ማወቅና መጠበቅም ትልቅ ስልጣኔና አርቆ አሳቢነት ነው።
መገላለጥና እርቃን መሄድ ስልጣኔ ቢሆን ኖሮ ከእንስሳት የበለጠ የሰለጠነ አይኖርም ነበር!
እህቴ ሆይ! አርዓያሽን እወቂ፤ ልብስ የዲን አካል መሆኑን ተረድተሽ እንደነሱ የምትሰግጂና የምትጾሚ ሰሓባዎችን አይነት ልብስ ልበሺ።
ከፊሉን አምኖ ከፊሉን መካድ ዱኒያ ላይ ያዋርዳል፤ አኼራ ላይም ለከባድ ቅጣት ይዳርጋልና።

ኡስታዝ አህመድ ሸይኽ አደም
21/12/1443ዓ.ሂ
-------------//--------------
@ዛዱል መዓድ

በተጨማሪም የተለያዩ
ትምህርቶችን ለማግኜት
ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ

https://telegram.me/ahmedadem
~
የኪታብ ደርሶችን ብቻ ለማግኜት
https://t.me/zad_qirat
~~~~
https://www.facebook.com/yenegew/
~~~~
http://www.youtube.com/c/ZadulMaad

አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል:-
{وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ وَاتَّقُونِ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ}
"ስንቅ ያዙ፤ ከስንቆች ሁሉ በላጩ አላህን መፍራት ነው፤ የአእምሮ/ የልብ ባለቤቶች ሆይ ፍሩኝ" ሱረቱል በቀራ /197