አማርራለሁ @ሀይማኖት(የዲማው) ስትበደል ስትገፋ፡ ስትጠላ ስትከፋ፡ ህይወት መሰናክሏ፡ሲጨምር በእጥፍ፤ እንዳታማርር፡ ተመስገን ስትል ነው ፡ የችግር ተክልህ፡ቶሎ የሚቀጠፍ፤ ይለኛል መካሪ፡ የምስጋናን ፀጋ አጉልቶና አግኖ፤ እኔ ግን እላለሁ በችግር ላይ ቁስል፡ ከመደረብ ሌላ፡ እስቲ ምን አገኘ፡እዮብ አመስግኖ?፤ ያለውን ሲነጠቅ፡ በደዌ ሲመታ፡ ከማመስገን ይልቅ፡ቢያማርረው ኖሮ፡ የአምላኩን ስልጣን፤ እልህ ባልተጋባ፡ ከእዮብ አናት ላይ፡የሰፈረው ሰይጣን። @a1hay @a1hay @a1hay 170 views𝑯𝒂𝒚𝒎𝒂𝒏𝒐𝒕 𝙽𝚒𝚐𝚞𝚜𝚒𝚎, 18:00